Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 15459
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

የትግራይ ህዝብ ሁለት ዕድሎች ብቻ በአንድነት አሉት ---> 1ኛ) ቅድመ-ወያኔ የነበረችውን ትግራይ መቀበል እና 2ኛ) ከጎሳ ፌደሬሽን የፀዳች ኢትዮጵያን እውነት ማድረግ።

Post by Abere » 01 Nov 2022, 10:23

የትግራይ ህዝብ ሁለት ዕድሎች ብቻ በአንድነት አሉት ---> 1ኛ) ቅድመ-ወያኔ የነበረችውን ትግራይ መቀበል እና 2ኛ) ከጎሳ ፌደሬሽን የፀዳች ኢትዮጵያን እውነት ማድረግ።

___ከዚህ ውጭ ያለ ምኞት ሊሳካ የማይችል ብቻ ሳይሆን የትግራይን ህዝብ ከሁሉም ኢትዮጵያዊ በተለየ መልኩ የጎሳ ፌደሬሽን ተጎጅ ነው። በእውነት ትግራይ ሊኖር የሚችለው በኢትዮጵያ እንጅ የፍየል ግንባር በምታህለው ትግራይ አይደለም። የመጨረሻ የአእምሮ ስንኩል የሆነው ወያኔ ክልል ሲፈጥር ከእብደት እና አማራ ጠልነት እንድሁም ሁል ጊዜ ትግሬ ስልጣን ላይ ሁኖ ሊሎችን እያስገበረ ይኖራል የሚል የኪራይ ሰብሳቢነት ከንቱ እሳቤ ነው። እውነታው ግን ትግራይ መኖር የምትችለው በኢትዮጵያ ነው። ክልል ለትግሬ ህዝብ እስር ቤት እና ሰቆቃ ነው። በስሜት ብቻ እየተነዱ ክልል የሚባል አፓርታይድ በገዛ ፈቃዳቸው ድህነት፤ርሃብ፤ መገለል፤ እና ፓስፓርት ተሸክመው ወደ አዲስ አበባ መግባትን ፈለጉ። አሁን ደግሞ ገና ወደ ኮረም እና አላማጣ ለመግባት ፓስፓርት ይጠየቃሉ። አይቀርም ይህ ክልል የሚባል እራስን በእራስ ወዶ የማሰር ዕብደት እስካለ ድረስ።

___ስለዚህ ትግሬ ድርድር አይደለም የሚያስፈልገው። ልደራደር ካለም እነኝህ ሁለቱን በአንድነት ሲያገኝ ብቻ ነው። ከዚያ ውጭ ወያኔን ነፍስ አድኘ ከአማራ ክፍላተ ሀገር መሬት ሰርቄ ወስጀ ያልፍልኛል የሚል ቅዠት በእብደት ላይ እብደት ሆናል።የሁመራ፥ወልቃይት እና ራያ ኮረም አላማጣ ቅዠታችሁን አቁሙ ብትፈልጉትም አክትሟል አትችሉም። የምትችሉት ግን የበለጠ የሚጠቅማችሁ ሁለቱ ጉዳዮች ናቸው።