Page 1 of 1

^^^{{{JUST IN}}}^^^:የትግራይ ህዝብ የኣሸባሪ-ህወሃት ሰላዮችና ጆሮ ጠቢዎች ላይ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል(((GAME OVER)))!!! WEEY GUUD !!!

Posted: 31 Oct 2022, 11:53
by tarik
Natnael Mekonnen
7m ·
የትግራይ ህዝብ የህወሃት ሰላዮችና ጆሮ ጠቢዎች ላይ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል!
ህዝቡ ከተቀረው ኢትዮጵያዊ እህት ወንድሙ ጋር በፍቅርና በመቻቻል ለመኖር የግፈኞችን ስርዓተ ቀብር እያፋጠነው ነው!
ትግራዋይ ለሃምሳ አመታት እንደ መርግ ተጭኖት የኖረው የህወሓት አመለካከትና አገዛዝ ያንገሸገሸው ይመስላል፡፡ የሰሞኑ ጉምጉምታዎችም ይህን ይጠቁማሉ፡፡ አምጠን የወለድናቸው ለፍተን ያሳደግናቸው ልጆች በየጊዜው ለጦርነት ቢማገዱም በምቾት የሚንደላቀቁት ጥቂቶች ናቸው፤ ለልማት የሚውሉ ክንዶቻችን ነፍጥ ተሸክመው ወንድሞቻችንን ሲገድሉ ኖሩ፤ በዙሪያችን ከሚገኙ ሀገራትና ከጎረቤት ሕዝቦች ጋር የነበረን መልካም ግንኙነት እየሻከረ በክፉ አይን መተያየትና ቁርሾ በዛ የሚሉት በርካታ ትግራዋይ ለዚህ ሁሉ የዳረጋቸው ግፈኛው ህወሓት መሆኑን በየጓዳቸው የሚያነሱትና የሚብሰለሰሉበት ጉዳይ ሆኗል፡፡
እነዚህ ትግራዋይ ሰሞኑን ሰላም እንዲወርድ ካደረባቸው ልባዊ መሻት በላይ ለአመታት የተጫናቸው ጥቂት የአድዋ አካባቢ ልሂቃን በበላይነት የሚዘውሩት የህወሓት አገዛዝ እንዲያከትም ፀሎትና ምህላ መያዛቸው እየተነገረ ነው፡፡ ለፅዮን ማርያም ስለት ያስገቡ ጭምር መኖራቸውም መነጋገሪያ ሆኗል፡፡
አብዛኛው የትግራይ ሕዝብ ሰቆቃው ይበቃ ዘንድ በድርድር ስም ወደ ደቡብ አፍሪካ ያቀኑት አመራሮች በዚያው እብስ እንዲሉ፤ በክልሉ መሽገው ዜጎችን እንደ መያዣ የሚጠቀሙትም ብን ብለው እንዲጠፉለት ከልቡ ይመኛል፡፡ መመኘት ብቻ ሳይሆን በየአካባቢው የሚደረጉትን የተቃውሞ እንቅስቃሴዎችንም እያጠናከረ ቀጥሏል፡፡ ይህም የአሸባሪውን ቡድን አመራሮች ልብ በፍርሃት እያራደ ይገኛል፡፡
በተለይ በመቀሌ ዙሪያ በምትገኘው ኩያ፤ በእንደርታ፣በተንቤን ፣ወጂራት፣ ሽሬ እንዳስላሴና በሌሎችም አካባቢዎች ነዋሪዎች የአሸባሪውን ህወሓት ተላላኪዎችና ጆሮ ጠቢዎች እየለዩ እርምጃ መውሰድ መጀመራቸው ፤ በወገን ኃይል በተያዙ አካባቢዎችም ለመሸሸግ የሚሞክሩትን እያጋለጡ ማስረከባቸው ትግራዋይ በጠመንጃ አፈሙዝ ተገዶ መተዳደሩ እንዳስመረረው ይመሰክራል፡፡
ያም ሆነ ይህ በርካታ ስፍራዎችን የተቆጣጠረውን ጥምር ጦር ግስጋሴ የሚያስቆም ምንም ምድራዊ ኃይል እንደሌለ ሰሞኑን ያስመዘገባቸው ወሳኝ ድሎች ያረጋግጣሉ፡፡ የምንከፍለው መስዋዕትነትም የትግራይ ሕዝብ ለአመታት እንደ መርግ የተጫነውን ስርዓት በማስወገድ ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር በነጻነት፣በእኩልነት፣በሰላም፣ በፍቅርና በመቻቻል አዲስ ምዕራፍ የሚጀመርበትን ቀን ለማብሰር ነውና አይቆጭም፤ አያስገርምም፡፡
በርካታ ትግራዋይ ይህን ተገንዝበው መራር ትግል እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ይህ መስዋዕትነታቸው በቅርቡ ፍሬ አፍርቶ በግፈኞች መቃብር ላይ በነጻነት፣በእኩልነትና በሰላም የሚኖሩባትን ኢትዮጵያ የማየት ጉጉታቸው እውን እንደሚሆን አንጠራጠርም