e
የኦሮሞ ድርጅቶችን ፖለቲካ ጨፍላቂነትን ማሳያ ፣ ናዝሬት #ግርማካሳ
የኦሮሞ ድርጅቶች ፖለቲካ ህዝብን የሚያከብር ፖለቲካ አይደለም ያላቸው፡፡ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ይላሉ፡፡ ሌላዉን በአሃዳዊነት ይከሳሉ፡፡ ግን በዋናነት የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት የሚረግጡት፣ በኦሮሞ ክልል ደረጃ “አሃዳዊ” የሆኑት እነርሱ ናቸው፡፡ በአዲስ አበባ፣ በሃረር፣ በድሬዳዋ በመሳሰሉት የኦሮሞ መብት መከበር አለበት ይላሉ፡፡ ግን በኦሮሞ ክልል እነርሱ የሌላውን መብት ይጨፈልቃሉ፡፡ ለነርሱ ለኦሮሞ መቆም ማለት ሌላውን መጨፍለቅ ማለት ነው፡፡
ለምሳሌ ወደ ናዝሬት እንምጣ፡፡ የናዝሬት ሕዝብ የራሱን እድል በራሱ እንዲወስን፣ የራሱን ከንቲባዎች እንዲመርጥ አይፈልጉም፡፡ እኛ የኦሮሞ መብት አይከበር አላልንም፡፡ እኛ የናዝሬት ነዋሪዎች፣ ኦሮሞ ይሁኑ ሌላ ፣ እንደ ናዝሬት ሕዝብ፣ እኩል መብታቸው ይከበር፣ ሁሉም አንድ ላይ ሆነው የፈለጉት ይሹሙ፣ የማይፈለጉት ይሻሩ ባዮች ነን፡፡ ያን በማለታችን እነርሱ ኝ ኦሮሞፎቢክ(የኦሮሞ ተላት ) ይልናል፡፡ እንዴት ነው የናዝሬት ሕዝብ የራሱን እድል ይወስን ማለት ፣ ኦሮሞን መጥላት የሚሆነው ?
በናዝሬት ባለፈው ኦፌሳላዊ የሕዝብ ቆጠራ መሰረት ፣ 74% የሚሆኑት ነዋሪዎች ኦሮምኛ ተናጋሪ አይደሉም። ሆኖም በከተማዋ አስተዳደር ፣ በቀበሌዎች የሚቀጠሩት፣ ኦሮምኛ ተናጋሪ ኦሮሞዎች ብቻ ናቸው። የከተማዎ ፓሊስ ሆነው የሚሰሩት አብዛኞቹ የናዝሬት ተወላጆች አይደሉም፡፡ ከሌላ ቦታ የመጡ ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ናቸው፡፡ ኦሮሞዎችም ኦሮምኛ የማይናገሩ ከሆነ በከተማዋ ቦታ የላቸውም፡፡ በከተማ የስራ እድሎች ካሉ ማስታወቂያ የሚወጣው በናዝሬት ሳይሆን በነ ወለጋ፣ አርሲና ባሌ በመሳሰሉት ነው፡፡
የናዝሬት ከንቲባዎችን ብንመለከት፣ አቶ አብርሃም አዶሌ፣ አቶ በከር ሻሌ፣ አቶ ሲሳይ ነጋሽ፣ አቶ ጉቱ፣ አቶ ጀማል አባስ፣ አቶ ሀብታሙ ሃይለሚካኤል፣ ወ/ሮ አዳነች አበቤ፣ አቶ አሰገድ ጌታቸው፣ አቶ ኃይሉ ጃልዴ …ሁሉም የአዳማ ከተማ ከንቲባ ሆነው የሰሩት ኦሮምኛ ተናጋሪ ኦሮሞዎች ናቸው። አንዳቸውም በአዳማ ከተማ ሕዝብ አልተመረጡም። በቀጥታ በኦሮሞ ክልል ርእስ መስተዳደሮች ነው የተሾሙት። አቶ አስገድ ጌታቸውና ከአቶ አሰግድ በፊት የነበሩት ወ/ሮ አዳነች አበቤን የሾሙት አቶ ለማ መገርሳ ሲሆኑ፣ አዮ ኃይሉ ጃልዴ የሾሙት እነ ሺመልስ አብዶሳ ናቸው።
ከነዚህ ከንቲባዎች ደግሞ ጥቅት የማይባሉ ቢያንስ ወደ ስድስት ከንቲባዎች በሙስና በዘረፋ ከሃላፊነታቸው ተነስተዋል። አቶ ጉቱ፣ አቶ ሲሳይ ነጋሽን እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል።
የናዝሬት/አዳማ አብዛኛው ኦሮምኛ የማይናገር ነዋሪ ከከተማዋ መስተዳደር መንግስታዊ አገልግሎት የማግኘት ችግር አለበት። ጉዳዮችን ለማስፈጸም ሰነዶችን ፣ ፎርሞችን ለአስተርጓሚ ከፍሎ አስተርጉሞ ነው የሚያቀርበው፡፡ ደብዳቤዎችን ወደ ላቲን/ቁቤ ለማስቀየር ለተርጓሚዎች በገጽ በሺህ የሚቆጠር ብር ነው የሚክፈለው።
በአጭሩ አነጋገር የናዝሬት ከተማ ሕዝብ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብት የለውም።አንድ በናዝሬት የተወለደ፣ እናቱ አባቱ በናዝሬት የተወለዱ ኦሮምኛ የማይናገር የናዝሬት ነዋሪ ካለው መብት ይልቅ፣ ከአርሲና ወለጋ ከመጡ ስድስት ወራት የሆናቸው ኦሮምኛ ተናጋሪዎች የበለጠ መብት አላቸው። ይሄም በናዝሬት ያለው አሰራር አፓርታይዳዊ አሰራር መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡
እዚህ ጋር ሊሰመርበት የሚገባው ራሱን የለዉጥ ኃይል የሚለው፣ የብልጽግና ፓርቲ እንደ ናዝሬት ባሉ አካባቢዎች ያሉ ኢፍታዊ፣ ዘረኛና የአብዛኛውን ነዋሪን መብት የሚረግጥ አሰራር ያስተካክላል የሚል ግመት በብዙዎች ዘንድ ነበር፡፡ ሆኖም እንኳን ሊያስተክክል እንደዉም በትጋት ዘረኝነቱንና ጭፍለቃውን እያስቀጠለ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡
ናዝሬት ትልቅ ፖቴንሻል ያላት ከተማ ናት። ሕዝብ የመረጠው፣ ለሕዝብ የቆመ የከተማ መስተዳደር ቢሰፍን፣ ህዝብ በፈለገ ጊዜ ለከተማችን አልሰሩም የሚላቸውን መሻርና በምትካቸው ሌሎችን መሾም ቢችል ከተማዋ የትናየት ትደርስ ነበር።
በነገራችን ላይ ናዝሬትን እስራኤል ሄደህ ፈለጋት፣ ያለው አዳማ ነው የሚል አስተያየተ የሚሰጡ ሰዎች ይኖራሉ ብዬ አስባለሁ፡፡ ግድ የለም አንከራከር ነው ለነርሱ መልሴ፡፡ የናዝሬት ህዝብ ፣ የከተማችን ስም አዳማ ይሁን ብሎ ከወሰኑ፣ የራሱን እድለ በራሱ የመወሰን መብቱን ተጠቅሞ፣ ያኔ አዳማ ብዬ እጠራለሁ፡፡ ማንም ተነስቶ ለናዝሮኤት ህዝብ የከተማህ ስም ይሄ ያለውን ኝ ያለመቀበል ሙሉ መብት አለኝ፡፡