Page 1 of 1

የደቡብ አፍሪካው አቺ ቢቺቺ ፤ ትጥቅ ፍታ v. ተኩስ አቁም

Posted: 29 Oct 2022, 16:58
by Horus
የ6 ቀኑ "ድርድር" አቺ ቢቺቺ ይባላል! ያም ፋይዳ ቢስ ቺት ቻት ማለት ነው!

አንደኛ፣
በጦር ሜዳ ዉጊያ እያሸነፈ ያለ ተከራካሪ ቀድሞ ተኩስ አያቆምም!

ሁለተኛ፣
የኢትዮጵያ አላማ የትግሬን ጦር ማክሰም እንጂ ትህነግን ከሞት አድኖ የዛሬ አመት ሌላ ጦርነት ለመዋጋት አይደለም ። ይህን የሚፈልግ አሜሪካ ነው !

ሶስተኛ፣
ነገ በደቡብ አፍሪካ ምንም አይወሰንም !

አራተኛ፣
ሌላ ቀን በጦር ሜዳው ካለው የሃይል ሚዛን ጋር ተመጣጣኝ የሆነ አዲስ የዲማንድ ሊስት ወጥቶ ለሌላ አቺ ቢቺቺ ቀጠሮ ይደረጋል ።

አምስተኛ።
እስከዚያ የኢትዮጵያ ጦር የትግሬን ሕዝብ ነጻ ማውጣቱን ይቀጥላል!

በአመጽ የሚካሄደው ፖለቲካ በኢትዮጵያ አሸናፊነት ላይ እያለ ለምንድን ነው ኢትዮጵያ በክርክር በሚካሄደው ፖለቲካ እንደትሸነፍ የሚሰበከው፣ አሜሪካ በሉ ወላ አውሮፓ? ገዋ አደረጉን እንዴ :?: :idea: :idea:

Re: የደቡብ አፍሪካው አቺ ቢቺቺ ፤ ትጥቅ ፍታ v. ተኩስ አቁም

Posted: 29 Oct 2022, 17:19
by Sam Ebalalehu
የ ኢትዮጵያ መንግሥት በ ተኩስ ማቆሙ ተስማምቶአል እኔ እንደምረዳው። ህወሓት ትጥቅ ይፍታ ENDF አንድ ጥይት አይተኩስም ነው ያለው።
ፋይዳ ለሌለው ነገር የሚጠላሉ ፖለቲከኞችን አንድ ቦታ አጉሮ ማነታረክ ምን ይባላል። አሜሪካኖቹም ለዛ ይመስላል አስቀድመው የትእቢት ጅራፋቸውን ያጮሁት። የUN ተወካያቸው መከራ እንደምናይ ነው የሰበከቸው ስምምነት ካልተደረሰ። ትርጉም የስንዴ እቀባ እናረጋለን ነው።
I have news for her. ሰውየው ለራሳችን በቂ ስንዴ ኖሮን ለውጭ አገራት በመጪው ጥቂት አመታት እንሸጣለን እያለ ነው።

Re: የደቡብ አፍሪካው አቺ ቢቺቺ ፤ ትጥቅ ፍታ v. ተኩስ አቁም

Posted: 29 Oct 2022, 17:21
by Horus
ይህው ከ4 ደቂቃ ጀምራችሁ ስሙ! የኢትዮጵያ ጦር አላማ ምን እንደ ሆነ!!!

Re: የደቡብ አፍሪካው አቺ ቢቺቺ ፤ ትጥቅ ፍታ v. ተኩስ አቁም

Posted: 29 Oct 2022, 17:34
by Horus
Sam Ebalalehu wrote:
29 Oct 2022, 17:19
የ ኢትዮጵያ መንግሥት በ ተኩስ ማቆሙ ተስማምቶአል እኔ እንደምረዳው። ህወሓት ትጥቅ ይፍታ ENDF አንድ ጥይት አይተኩስም ነው ያለው።
ፋይዳ ለሌለው ነገር የሚጠላሉ ፖለቲከኞችን አንድ ቦታ አጉሮ ማነታረክ ምን ይባላል። አሜሪካኖቹም ለዛ ይመስላል አስቀድመው የትእቢት ጅራፋቸውን ያጮሁት። የUN ተወካያቸው መከራ እንደምናይ ነው የሰበከቸው ስምምነት ካልተደረሰ። ትርጉም የስንዴ እቀባ እናረጋለን ነው።
I have news for her. ሰውየው ለራሳችን በቂ ስንዴ ኖሮን ለውጭ አገራት በመጪው ጥቂት አመታት እንሸጣለን እያለ ነው።
በፕሪንሲፕል አው ኢትዮጵያ ተኩስ አቁም መች እምቢ ታውቃለች?!

እኔ ሌላ ቦታ ብዬዋለሁ፤ በዚህ ጉዳይ ያሉት ሁለት ድርድሮች ናቸው! አንዱ በኢትዮጵያ መንግስትና በትግሬ ተገንጣዮች መሃል ያለው ትንሹ ድርድር ነው!

ትልቁ እጅግ ግዙፉ ክርክር በልዑል ኢትዮጵያና በሃያሉ አሜሪካ መካከል ያለው ዋናው፣ እጅግ ዋናው ትግል ነው!

ይህን ዋነኛ ረጅም ያሜሪካ ጥቃት ለመቋቋም ብልጽግና አሁን በያዘው የጎሳና የሙስና ቁመና አይችልም! ይህ መሆን አለበት የሁላችን ትልቅ ፍርሃት!

Re: የደቡብ አፍሪካው አቺ ቢቺቺ ፤ ትጥቅ ፍታ v. ተኩስ አቁም

Posted: 30 Oct 2022, 12:24
by Horus
ሆረስ ዐይነ ብርሃን ካህነ አተን ነኝ! ዛሬ የዋሽንግተን ፖስት ይህን አለ! "The outcome of the talks hinges on whether Prime Minister Abiy Ahmed is prepared to give up the momentum achieved by his troops since fighting resumed in late August." እኔ የዛሬ ሳምንት ያልኩት ያን ነበር! ከድርድሩ በፊት! ኢትዮጵያ ፖለቲካውን በጦር ሜዳ እያሸነፈች እያለች፣ በጠረጴዛ ዙሪያ ለመሸነፍ አትደራደርም ብዬ ነበር ። በቃ! ሃተታ ቢበዛ ባህያ አይጫንም!