Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42852
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የደቡብ አፍሪካው አቺ ቢቺቺ!

Post by Horus » 28 Oct 2022, 13:53

አቺ ቢቺቺ የጉራጌኛ ቃል ነው፤ እሱም ቺት ቻት ማለት ነው። አቺ ቢቺቺ በሁለት ወይም በብዙ ሰዎች መሃል የሚደረግ ፋይዳ ሚስ ንግግር ወይም ወሬ ማውራት ነው። እኔ በደቡብ አፍሪካ በአቢይ መንግስትና ትህነግ መሃል የሚደረገው ክርክር (ድርድር አይደለም) አቺ ቢቺቺ እለዋለሁ ። የዚህ አቺ ቢቺቺ ምስጢር ያለው ትግሬ ውስጥ በሚካሄደው የጦር ፍልሚያ ነው ።

ትህነግ መሳሪያ አውርዶ ትኩስ ሊቆም አይችልም ። ከዚህ ጦርነት የተረፈው ትህነግ የሆነ ትግሬ ዋሻ ውስጥ ሄዶ ጎሬላ ዉጊያ ይጀምራል። ያ ነው የሚሆነው ።

እውነተኛው ጂኦፖለቲካዊ ጦርነት እየተደረገ ያለው ባሜሪካና ኢትዮጵያ መሃል ነው (አውሮፓና ተመድ ጨምሮ)። አፍሪካ ውስጥ ያሉ ያሜርካ አሽከር አገሮችም አሉ ። ይህ ትግል ወይም ክርክር እየተገረገ ያለው ካናዳ ውስጥ ነው ። የአቢይ መንግስትና ያሜሪካው ባይደን መንግስት አይተማመኑም፤ ኢትዮጵያና አውሮፓ አንድነትም አይተማመኑም። ለዚህ ነው ሁለተኛውና እውነተኛው ድርድር ወይም ክርክር ወደ ካናዳ የተወሰደው ።

አሜሪካ ትህነግ ን ለማዳን አይደለም ይህን ሁሉ የምትፈድለው፤ ሩሲያና ቻይናን ለመታገል፣ ከኢትዮጵያ ለማስወጣት ነው ። ስለዚህ አቢይ አህመድ ከጌታቸው ረዳ ምናምን ጋር አይደለም ያለበት ትልቅ ትግል ከቶኒ ብሊንከር ጋር ነው ። ያን ድራማ ነው በቅርበት መከታተል ያለብን እንጂ ትግሬ ውስጥ ያለው ዉጊያ የሚነዳው በሌላ ሎጂክ በጦርነት ሎጂክ ነው ።


Horus
Senior Member+
Posts: 42852
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የደቡብ አፍሪካው አቺ ቢቺቺ!

Post by Horus » 28 Oct 2022, 14:14


Horus
Senior Member+
Posts: 42852
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የደቡብ አፍሪካው አቺ ቢቺቺ!

Post by Horus » 28 Oct 2022, 14:47


Horus
Senior Member+
Posts: 42852
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የደቡብ አፍሪካው አቺ ቢቺቺ!

Post by Horus » 28 Oct 2022, 15:00


Horus
Senior Member+
Posts: 42852
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የደቡብ አፍሪካው አቺ ቢቺቺ!

Post by Horus » 30 Oct 2022, 12:38


Post Reply