ይህ ርዕስ ለኣንትሮፖሎጂ ጥናት እና ምርምር ፍላጎት ላላቸዉ ነዉ።
መመለስ ያቃተኝ ኣጭር ጥያቄ ኣለኝ። የሰዉ ልጅ መጻፍ ሲጀምር የቃላት መለዋወጥን ኣስከትሏል? ስለዚህ ርዕስ ምንም ዕዉቀት የለኝም።
በቅርቡ ጎልማሳ ይቀጣል ሲባል ሰምቶ ልጅ ተነስቶ መቀጥቀጥ ጀመረ ኣልኩኝ። መቅጣት እና መቀጥቀጥ ለየብቻ ስለሆኑ። ከዛም መቀጥቀጥ ከመወጥወጥ ጋር ተመሳሰለብኝ።
ያ ደግሞ ሌላ ትዉስታ ኣመጣ። ወጢ፣ በኣማርኛ ወጥ፣ የኣፋን ኦሮሞ ቃል ኣይዴለም የሚል። ኣላሳመነኝም። ከዛ ባላይ በምትኩ እቶ ይባላል የሚለዉ የበለጠ ኣላሳመነኝም። ወጢ ሌሎች ተወራራሽ ቃላት ኣሉት። ወጤ፣ ወጤ (ለወንድ እና ሴት የተለያየ አጠራር ኣለዉ)፣ ወጠወጤ።
ከቀጠቀጠ በላይ ወጠወጠ ድርጊቱ ጉልህ ሆኖ ይታየኛል። ስለዚህ መጻፍ ሲጀመር የ ቀ እና ወ ተመሳሳይነት ወጠወጠን ወደ ቀጠቀጠ ቀይሮት ሊሆን ይችላል? መልሱን ኣላዉቅም።
ላሞች የሚታለቡበት ቤት ስለኣደኩኝ ከወተት የተለያየ ኣይነት ስሞችን ጠንቅቄ ኣዉቃለሁ። ሃነን፣ ኣዬቱ፣ እትቱ፣ እቶ፣ ዸዻ፣ ባዱ፣ ዸመ፣ ሻሜተ። እትቱ እና እቶ ተመሳሳይ ኣጠራር ኣላቸዉ። ስለዚህ እቶ ከነዚህ ሁሉ ተነጥሎ የወጢን ስም ተክቶ እንጠቀም የሚለዉ ኣላሳመነኝም።
ይህን ሳሰላስል ሰንብቼ በቅርቡ ደግሞ ቄስ እና ቃሉን ኣንድ ላይ ስማቸዉን ስጽፍ ሁለቱም ቃላት ትንሽ ተመሳሰሉብኝ። ቃሉ ከሚለዉ ስም ጋር በርካታ የተያያዙ ቃላት ኣሉ። ቄስ ቃሉን ሰማሁ እንጂ ሌሎች ተወራራሽ ቃላት እንዳሉት ኣላዉቅም። ኣሁን ያለኝ ጥያቄ ቃሉ እና ቄሲ የመጻፍ መጀመር ተጽዕኖ ሊኖርባቸዉ ይችላል ወይ? ለዚህም መልስ የለኝም።
እንደነዚህ ኣይነት ተጽዕኖዎች መጻፍ መጀመር ያመጣቸዉ ከሆነ ኢትዮጵያ ዉስጥ ስለ መጻፍ መጀመር ታሪክ ራሱ ግዙፍ ምዕራፍ ተከፈተ ማለት የሚቻል ይመስለኛል።
ዕዉቀቱን ያላችሁ ምን ትላላችሁ?
Re: ቃሉ፣ ቄሲ፣ ቄስ፣ ወጥ፣ ወጠወጠ፣ ቀጠቀጠ፣ እና መጻፍ መጀመር
ካልተሳሳትኩ ኢትዮጵያ ዉስጥ መጤ እና መጤ ያልሆኑ ሃይማኖቶች የሚል ክርክር የሰነበተ ነዉ። የኦርቶዶክስ ሃይማኖት የፕሮቴስታንት ሃይማኖትን መጤ ሲል የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ደግሞ ኦርቶዶክስም መጤ ነዉ የሚል ክርክር ነበር።
በቅርቡም እዚህ መድረክ ላይ ይህ ክርከር ተነስቶ ጥያቄዉ የትኛዉ ነዉ የበለጠ ሃገራዊ መሰራት ያለዉ ብሎ መጠየቅ ነዉ ማለትን ኣስታዉሳለሁ።
ይህ በኦርቶዶክስ እና ፕሮቴስታንት ሃይማኖቶች መሃል የነበረ ክርክር እዚህ መድረክ ላይም ለረጅም ጊዜ ይንጸባረቅ ነበር።
ኢትዮጵያ ኣንድ ቀን የፕሮቴስታንት ኣማኝ ከስራ በሁዋላ ሰራተኞች ቢራ ፉት የሚሉበት ላዉንጅ ዉስጥ ቤተክርስትያናቸዉ እንሂድ ስለኝ ሃይማኖት ከሆነ ኣንተ ለምን የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ኣትሄድም ብለዉ ተመለሰ። እዉነተኛ ታሪክ ነዉ።
ከዚህ ሁሉ ክርክር በሁዋላ ቃሉ የሚለዉን ቃል እና የተያያዙ ቃላትን ሳስብ ይህ ቃል ብቻ የትኛዉ ሃይማኖት የበለጠ ሃገራዊ መሰረት እንዳለዉ ኣይመልስም ወይ ብዬ እጠይቃላሁ። የሚመልስ ይመስለኛል። ከመለሰ የሚደንቅ ነዉ።
ስለ ቃሉ እና ሌሎች ተመሳሳይ ቃላት (ቃል፣ ቀሌ፣ ቃላ፣ ቅሌ፣ እና የኢንግሊዘኛዉ ኪል) እዚህ መድረክ ላይ መጻፌን ኣስታዉሳለሁ። ለጊዜዉ ፈልጌ ኣላገኘሁትም።