Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
tarik
Senior Member+
Posts: 37256
Joined: 26 Feb 2016, 13:04

New Video Of አላማጣ & ኮረም:ጁንታው ለ2 ዓመት ያዘጋጀውን ምሽግ አስረክቦ ፈርጥጧል 3 ታንኮች ተማርከዋል፤በርካታ የቡድንና የግል መሳሪያዎችም ተይዘዋል!!! WEEY GUUD !!!

Post by tarik » 17 Oct 2022, 14:15

Please wait, video is loading...
Natnael Mekonnen

አላማጣ፣ ኮረም...‼
ጁንታው ለሁለት ዓመት ያዘጋጀውን ምሽግ አስረክቦ ፈርጥጧል ሶስት ታንኮች ተማርከዋል፤ በርካታ የቡድንና የግል መሳሪያዎችም ተይዘዋል‼
በጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን የሚመራው ጥምር ጦር በዛሬው ዕለት አላማጣንና ኮረምን ነፃ አውጥቶ ወደ ማይጨው እየገሰገሰ መሆኑን ምንጮች ገልፀዋል። ጥምር ጦሩ በሰቆጣ በኩል በምትገኘው ዛታ ከተማ መስመር በመግባት አላማጣን የነበረውን የጁንታውን ታጣቂ በመቁረጥ ኮረምን ጨምሮ በአካባቢው ያሉትን ከተሞች ሙሉ በሙሉ ከወያኔ ታጣቂዎች ነፃ አውጥቷል። 
በዚህ ውጊያ በርካታ የወያኔ ታጣቂዎች ተደምስሰዋል። ከፊሎቹም እጅ ሰጥተዋል። ጁንታው ከተሞች መሐል በመሆን መሳሪያ ሲተኩስ የነበረ ሲሆን፤ ጀግኖቻችን ሲቪሎች እንዳይጎዱ ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ፣ ዛሬ ላይ የጁንታውን ታጣቂ ሙሉ ለሙሉ ከከተማ በማስወጣት አካባቢውን ከወያኔ ታጣቂ ነፃ አውጥተዋል። በውጊያው ሶስት የጁንታው ታንኮች፣ በርካታ የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች እንዲሁም ሌሎች የርዳታ ቁሳቁሶች ተይዘዋል። በኮረም የነበረው ምሽግ ለሁለት ዓመታት ጁንታው ያዘጋጀው ሲሆን፤ ነዳጅን ጨምሮ ሌሎች የሎጀስቲክስ አቅርቦቶችንም የያዘ ነበር። አይበገሬዎቻችን ይህን ምሽግ በታላቅ ጀግንነት ደረማምሰው መቆጣጠራቸውን ምንጮቻችን ገልፀዋል‼