Page 1 of 1

^^^{{{JUST IN}}}^^^Video Of አበቃ:መላ የተረገመት-ሜሬትና-ህዝብ-ትግራይ በጥምር ጦሩ እጅ እየገባች ነው:-መንግስት ሀቁን ተናገረ!!! WEEY GUUD !!!

Posted: 17 Oct 2022, 10:19
by tarik

------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/

መንግሥት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ያስተላለፋቸው ዋና ዋና መልዕክቶች‼️
👉ሕወሐት በሙሉ ዐቅሙ ጥቃት ከመክፈቱ በፊት የኢትዮጵያን የአየር ክልል ደጋፊዎቹ በሆኑ የኢትዮጵያ የውጭ ጠላቶች ሲያስደፍር ቆይቷል፤
👉በዚህም የተነሣ የኢትዮጵያ መንግሥት የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት የመጠበቅ ግዴታውን እንዲወጣ አስገድዶታል፤
👉ስለሆነም የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ለማስከበር የኢትዮጵያ መንግሥት የአውሮፕላን ማረፊያዎችን፣ የፌዴራል ተቋማትንና ታላላቅ መሠረተ ልማቶችን የግድ መጠበቅ አለበት ማለት ነው፤
👉የኢትዮጵያመንግሥት የሚወስዳቸው ርምጃዎች የግድ አስፈላጊ የሆኑት በሕወሐት ተደጋጋሚ ጥቃት የተነሣ ብቻ ሳይሆን ከሀገሪቱ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ተቀናጅቶ በሚፈጽማቸው ተግባራት ምክንያት ጭምር ነው፤
👉ይህም የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት በተለይም የአየር ክልልን በሚገባ ከማስከበር አንጻር መጠበቅን የግድ አድርጎታል፤
👉እነዚህ ተግባራት መፈጸሙ መንግሥት ሰብአዊ ርዳታን ለተረጂዎች በተገቢው ሁኔታ እንዲያሣልጥ የሚረዳው ይሆናል፤
👉በአንድ በኩል እነዚህን ዓላማዎች እያስፈጸመ በሌላ በኩል ደግሞ በአፍሪካ ኅብረት አማካኝነት ለሚካሄደው የሰላም ውይይት ዝግጁ መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥት በድጋሚ ያረጋግጣል፤
👉ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ሁለንተናዊና በንግግር ላይ የተመሠረተ ስምምነት አስፈላጊ መሆኑን መንግሥት ያምናል፤
👉የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አግባብነት ባላቸዉ አሠራሮችና በዓለም አቀፍ የሰብአዊ ሕጎች በጽኑ የሚገዛ መሆኑን መንግሥት ግልጽ ለማድረግ ይፈልጋል፤
👉ንጹሐን እንዳይጎዱ ለመከላከል እንዲቻል የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ጦርነቱ በከተሞች ውስጥ እንዳይደረግ ጥንቃቄ እያደረገ ይገኛል፤
👉ይሄንን በጽኑ ለመፈጸም እንዲቻልም ለሁሉም ተዋጊ አሐዶች ጥብቅ መመሪያ ተላልፏል፤
👉ከዚህም ባሻገር በመንግሥት ቁጥጥር ሥር በሆኑ አካባቢዎች ሰብአዊ ርዳታ በተሻለ መንገድ መቅረብ እንዲችልና የርዳታ ሠራተኞች ደኅንነት የተጠበቀ እንዲሆን መንግሥት ከርዳታ ድርጅቶች ጋር አብሮ ለመሥራት ዝግጁ ነው፤
👉ሕወሐት ንጹሐንን እንደ ጦር መከላከያ የመጠቀምና ሲቪል ተቋማትን ለወታደራዊ ሠፈርነት የመጠቀም የቆየ ልማድ አለው፤
👉ስለሆነም ሕዝቡና የርዳታ ሠራተኞች ራሳቸውን ከሕወሐት ወታደራዊ ተቋማት እንዲያርቁ የኢትዮጵያ መንግሥት ጥሪ ያደርጋል፤
👉የርዳታ ሠራተኞችን ጨምሮ በሲቪሎችን ላይ ለሚደርሰው ማንኛውም ጉዳት መንግሥት ኀዘኑን በዚህ አጋጣሚ ይገልጣል፤
👉እውነቱን ለማወቅና ያልተገደበ የርዳታ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እንዲቻል ጉዳቶች ከተከሠቱ የሚያጣራ ይሆናል፤
👉በትግራይ ክልል የሚገኙ ዜጎቹን ደኅንነት ለመጠበቅ በሕግ የተሰጠውን ሕገ መንግሥታዊ ግዴታውን ለመወጣት የኢትዮጵያ መንግሥት ያለውን ዝግጁነት ያረጋግጣል፤