በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደውን የመከላከል ርምጃ በተመለከተ በኢትዮጵያ መንግስት የተሰጠ መግለጫ!!! WEEY GUUD !!!
Posted: 17 Oct 2022, 08:57

በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደውን የመከላከል ርምጃ በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ
በአሁኑ ወቅት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረው ግጭት፤ ሕወሐት ነሐሴ 18 ቀን 2014 ዓ.ም በሙሉ ዐቅሙ የከፈተውን ጥቃት ተከትሎ የመጣ መሆኑን ማስታወስ ተገቢ ነው። ይህም የኢትዮጵያ መንግሥት በሚያዝያ ወር ያወጀውን በሰብአዊነት ላይ የተመሠረተ የተኩስ አቁም የጣሰ ነው። የመንግሥት ጥረት ምንም ዋጋ ስላልተሰጠው፣ ሕወሐት በሁለት ዓመት ውስጥ ሀገሪቱን ለሦስተኛ ጊዜ ወደ ግጭት አስገብቷታል።
ሕወሐት ሦስተኛውን ግጭት የከፈተው በአፍሪካ ኅብረት በኩል በሚደረገው የሰላም ንግግር፣ ያለ ቅድመ ሁኔታ በየትኛውም ጊዜና ቦታ ላይ ለመነጋገር የኢትዮጵያ መንግሥት ዝግጅነቱን ከገለጠ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ለልዩ መልእክተኞችና መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ላደረጉ ዲፕሎማቶች ጥቃት ለመሠንዘር ሕወሐት ያለውን ዝግጁነት አመልክቶ ነበር።
ሕወሐት ለተለያዩ ዓለም አቀፍ አካላት በበተነው ደብዳቤ ላይ ይሄንን ጥቃት የመክፈት ፍላጎቱን በግልጽ አመልክቷል። በመሆኑም አሁን ለተፈጠረው ችግር ሁሉ ብቸኛ ተጠያቂው ሕወሐት መሆኑ የተረጋገጠ ነው። ጊዜና ቦታ ከተሰጠውም ሌላ ዙር ግጭት እንደሚፈጥር ከሰሞኑ መግለጫዎቹ ለመረዳት ይቻላል።
