ጉራጌ በካልቸሩ ትንሳኤ እየፈነዳ ነው!! A True Cultural Reanissance Underway!!
ይህን የአርትና ካልቸር ፍንዳታ አዲስ እድገት በሉት ትንሳኤ (ሬነሳንስ) በሁሉም መስክ በስነ ጽሁፍ፣ ሙዚቃ፣ ቲያትር ፣ እስፖርት፣ ባህላዊ ወግና ዘዪዎች ከላይ እስከ ታች በያንድንዱ ቤተ ጉራጌ ይህ ነው የማይባል ፈጠራና ትዕይንት እያበበ ነው። ይህ ሕዝባዊ መንሳት ምክኛቱ ምን እንደ ሆነ ገና በጥናት ላይ የተመሰረት እውቀት ባይኖርም የአቢይ መንግስት የጉራጌን ሕዝብ ክልልነት መብት ከመንፈግና ጉራጌን ለማዳከም ከማክሰም ለሚከሰቱ የጠላት አላማዎች ምላሽ ጋራ ሊያያዝ ይችላል ። በጉራጌ ህልውና ላይ ካንዣበበው አደጋ የመነጨ ሊሆን ይችላል!!!
Re: ጉራጌ በካልቸሩ ትንሳኤ እየፈነዳ ነው!! A True Cultural Reanissance Underway!!
በያመቱ ከመስቀል እስከ ጥቅምት አምስት የሚዘልቀው የውጣቶች መተጫጫ አዳብና ባህል አሁን Miss Adabina ወይዘሪት አዳብና የተባለ የቁንጅና ውድድር ማድረግ ጀምሯል ፣ ይህም ውድድር አገር አቀፍ ሊያደርጉት እያሰቡ ነው። የፈረስ ጉግስ ክለቦች መቋቋም ጀምረዋል። የገና ጨዋታም ወደ ቶርናመንት ሊያሳድግይ ይስባሉ !! ድንቅ ነው !