ሌብነትና የማዐት ስነምግባር
ዛሬ እኛ ኢትዮጵያዊያን የማዐትን ትክክለኛ ትርጉም ለውጠን ከመጥፎ ነገርና መከራ ጋር አያያዝነው እንጂ ድሮ ጽንሰ ሃሳቡን ለፈጠሩት ትንታዊ ግብጾች ማዐት (መዐት) ማለት በእውነትና ፍትህ ሚዛን ላይ መለካት ነበር ። ዛሬ ግሪኮች ፈጠሩት የሚባለው የሞራልና ኤቲክስ ህግጋት ወይም ከዚያ በፊት ለሙሴ ተገለጹ የተባሉት አስርቱ ትዕዛዛት ሁሉ ከቀምጥ የተኮረጁ የ42 ማዐት ህግጋት ናቸው ። ሁሉ ነገር ግንድ አለው ! ሁሉ ነገር ስር አለው! ለመሆኑ ዛሬ ላይ ያለው አበሻ ከሊቅ እስከ ደቂቅ በእውነትና ፍትህ ሚዛን ላይ ቢለካ ስንቱ ሚዛን ይደፋል? አዋቂው ሌባ ነው! ህጻኑ ኮራጂ ነው