ወንድሜ #አላህ ምትክህን ይስጠን !!
የአጎቴ ልጅ ኮሎኔል አጣህር መሀመድ ወደ ውትድርና የገባው ገና በለጋ እድሜው የወጣትነት ህይወቱን አጣጥሞ ሳይጨርስ የሟች አጎቱ አሳቢር አለሚን ፈለግ በመከተል በ1989 ዓ.ም ወደ ሀገር መከላከያ ሠራዊት በትንሽ እድሜ የተቀላቀለ ጀግና ነበር።
ወንድሜ ሀገራችንን ኢትዮጵያ በወራሪው የኤርትራ መንግስት በተወረረችበት ወቅት ሀገሩን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል በታማኝነት ያገለገለ ጀግናም ነበር።
አሁን ምንም ማድረግ አይቻልም ይኸው ቀኑ ደርሶ ወደ ማይቀረው ዓለም ከተሰናበተን 2 ሳምንታት ማስቆጠሩን በዛሬው እለት የደረሰኝ መረጃ እጅጉን ደንግጫለሁ፣ አዝኛለሁ አልቅሻለሁም።
ይሁን እንጂ ስለወንድማችን ህልፈተ ህይወት ሲያውቁ የነበሩት የቅርብ ሰዎች ጉዳዩን በሚስጥር ለመያዝ ተገዷል።
ምክንያቱም ውዷ ባለቤቱና የልጆቹ እናት የሆነችው ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል የከፍተኛ ትምህርት መሰናዶ ፈተና ላይ ስለነበረች ፈተናውን ተረጋግታ እንዳትሰራ በማሰብና በትናንትናው እለት ፈተናዋን በማጠናቀቋ በዛሬው እለት የወንድማችን ህልፈተ ህይወት ለውዷ ባለቤቱና ለመላው ቤተሰቡ ይፋ ለማድረግ ተችሏል።
አልሃምዱሊላህ


