Page 1 of 1

የጉራጌ ወጣቶች ሚስ (ወይዘሪት) አዳብና የልጃገረዶች ቁንጅና ውድድር ሊጀምሩ ነው!!

Posted: 10 Oct 2022, 01:37
by Horus
አንድ ሕዝብ ጥሩ ወይም መልካም ካልቸር ካለው ያ ካልቸር ቢያንስ አራት ትላልቅ ይዘቶች ይኖሩታል ።

አንደኛ ያ ካልቸር የህዝቡን የኑሮ ዘዬ በሁሉም መልኩ ይገልጻል፣ ያንጸባርቃል፣ እነዚያን ዘዬዎች ይጠብቃል፣ ይንከባከባል!

ሁለተኛ ያ ካልቸራር ኢኮሎጂካል መሆን አለበት ። ያ ካልቸር ሕዝቡንና ኢንቫይሮንሜንቱን እንደ አንደ ተደጋጋፊዎች በማሰር ሕዝቡ እንደ ባህል አፈሩን፣ አየሩን፣ እንሰሳውን፣ እጸዋቱን እንደ ባለቤት ሃላፊ ሆነው መንከባከብ አለባቸው ። ይህን የማያደርግ ካልቸር ጥሩ ሊባል አይቻልም።

ሶስተኛው ያ ካልቸር መንፈሳዊነትን ማካተት አለበት ።

አራተኛ ያካልቸር ፈጠራን፣ ለውጥን፣ እድገትን የሚቆሰቁስ፣ የሚረዳ፣ የሚያበረታታና ዲማንድ እሚያደርግ መሆን አለበት ።

ይህን ሁሉ ለማለት የጎተጎተኝ ባህላዊው የመስቀል አዳብና የወጣት ወንድና ሴት መተዋወቂያና መተጫጫ በሆነው ባህል ዙሪያ ሚስ (ወይዘሪት) አዳብና የሚባል የልጃገረዶች የቁንጅና ውድድር ሊጀመር መሆኑን አንብቤ ነው ። በቃ ይህ ነው ካልቸራል ኢኖቬሽን፣ ፈጠራ ። ክሬቲቪትና አንድን ባህል ከዘመኑ ጋር ማዘመን ማለት!!!



Re: የጉራጌ ወጣቶች ሚስ (ወይዘሪት) አዳብና የልጃገረዶች ቁንጅና ውድድር ሊጀምሩ ነው!!

Posted: 10 Oct 2022, 01:52
by Horus