Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

ሸገር የዳቦ ፋብሪካ በአንድ ዳቦ 36 ሳንቲም እየከሰረ ለገበያ እያቀረበ መሆኑ ተገለጸ - በሕወሓት ጊዜ 36 ሳንቲም የአንድ ዳቦ ዋጋ ነበር

Post by sarcasm » 07 Oct 2022, 20:18

ሸገር የዳቦ ፋብሪካ በአንድ ዳቦ 36 ሳንቲም እየከሰረ ለገበያ እያቀረበ መሆኑ ተገለጸ
እሱባለው ጋሻው



ሸገር ዳቦ ፋብሪካ በአንድ ዳቦ 36 ሳንቲም እየከሰረ ለተጠቃሚዎቹ እንደሚያቀርብ የሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የምርት ዘርፍ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ አካለወልድ አድማሱ ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል።

የሜድሮክ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አባል በሆነው ሆራይዘን ፕላንቴሽን ኩባንያ የሚመራው ሸገር ዳቦ ፋብሪካ በ2012 ተመርቆ ሥራ የጀመረ ሲሆን፣ በቀን 1.3 ሚሊዮን ዳቦ ለተጠቃሚዎች እንደሚያደርስና ለተጠቃሚዎች የሚያደርሰው እያንዳንዱ ዳቦ 36 ሳንቲም እንደሚያከስረው አካለወልድ ተናግረዋል። ሸገር ዳቦ ፋብሪካ ለትርፍ ያልተቋቋመ መሆኑን ሥራ አስፈጻሚው ጠቁመው፣ መጀመሪያ ከነበረው የዳቦ መሸጫ የዋጋ ማስተካከያ ከተደረገም በኋላ ይህ ኪሳራ ቀጥሏል ብለዋል።

ፋብሪካው ከተያያዥ ኪሳራና የግብዓት አቅርቦት ችግሮች ጋር በተያያዘ ለአንድ ወር የምርት ሂደቱን አቋረጦ ነበር። ከዛም በኋላ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአንድ ዳቦ የሚያደርገውን ድጎማ እስከ አንድ ብር ከአስራ አራት ሳንቲም ድረስ ከፍ ማድረጉን ተከትሎ፤ አንዱ ዳቦ ይሸጥ ከነበረበት የአንድ ብር ከኻያ ሳንቲም ዋጋ ወደ ኹለት ብር ከአስር ሳንቲም ዋጋ ከፍ ማለቱ የሚታወስ ነው። ኪሳራውም በዚህ ዋጋ ከሚሸጠው ዳቦ ላይ መሆኑ ታውቋል።

Continue reading https://www.addismaleda.com/archives/31966