Page 1 of 1

ጉራጌ ክልል መሆን የፈለገው ለፌዴራል ባጀት ድጎማ አይደለም! የክልል ባጀት ክርክር ብልጽግና ውስጥ! ሺመልስ የከተሞች ዌልፌር ተቃወመ!!

Posted: 28 Sep 2022, 23:05
by Horus
እዚህ ስብሰባ ውስጥ በጣም ጥሩ ጥሩ ጥያቄዎች ተነስተዋል ።
(1) አንድ ክልል እራሱን ችሎ እራሱን ማልማት አለበት? አው! ጉራጌ ክልል ከሆነ ጉራጌ እራሱን ይገዛል፣ የራሱን ክልል የማልማት ሃላፊነት አለበት!
(2) ከገጠር ገብሬ የተሰበሰ ግብር ከተማ መገምቢያ መሆን የለበትም ። ከተማ ራሱን መቻል አለበት ከተባለ ደሞ እንደ ክልል ራሱን መግዛት አለልበት ። አዲስ አበባ ከኦሮሚያ ነጻ መሆን አለበት ።
(3) በስፋት በንግድና ኢንዱስትሪ የተሰማሩት የጉራጌ ብሄር አባላት ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ሆነው እነሱ ግ ን የፖለቲካ ህልውናም፣ ራስገዝነትም ተነፍገው የሌሎችን ክልልና ከተማ አልሚዎች ናቸው። ይህ ኢፍትሃዊ ስር ዓት መለወጥ አለበት።
(4) የመሬት ግብር መሬት የግል ሳይሆን ፍትሃዊ ሲስተም አይደለም



Re: ጉራጌ ክልል መሆን የፈለገው ለፌዴራል ባጀት ድጎማ አይደለም

Posted: 28 Sep 2022, 23:38
by Horus
ብዛሬይቱ ኢትዮጵያ ያሉት ሁለት የዴቨሎፕመንት ጂኦግራፊዎች ክልልና ከተማ ናቸው ። ክልል እንዴት እራሱን ፋይናንስ አድርጎ ይበልጽግ እና አንድ ከተማ በማን ፋይናንስ እራሱን ያሳድግ የሚሉት ጥያቄዎች እጅግ ቁልፍ ናቸው ። ፌዴራል ሲስተም ማለት ይህ ነው ። ከተማ ራስ ገዝ ነው። ክልል ራስ ገዝ ነው። እስቴት ራስ ገዝ ነው ። ስለዚህ መጀምሪያ እያንዳንዱ ከተማ ራሱን የሚገዛ ኤንቲቲ መሆን አለበት ። ክልልም እንዲሁ ። ጉራጌ የራሴንክ ክልል አሳድጋለሁ ብሏል። ስለዚህ መጀምሪያ ያንን መብት ማክበር አለበጥ ከዚያ በኋል ነው አንድ ክልል ምን አይነት ፌዴራል ባጀት ማግኘት ወይም አለማኘት ድርድር የሚደረገው ። ገና ለገና አንድ አዲስ ክልል ባጀት ይጠይቃል በሚል ፍርሃት የህዝቦችን የፖለቲካ መብት መግፈፍ ክልክል ነው ።