ቴዲ አፍሮ፣ የዚህ ትውልድ ህሊና መለኪያ ቴርሞሜትር! በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የፍቅር ፈላስፋ !!!
Posted: 28 Sep 2022, 02:45
ላለፈው 50 አመት ስልጣን ላይ የወጡ አላዋቂ የፖለቲካ ጂሎች ሁሉም ጦረነትን እያመለኩ፣ ጥላቻን እንደ ታቦት እያነገሱ፣ ለነሱ የማያባራ ጦርነት አዳማቂና አሟሟቂ ዘፋኝና ሙዚቀኛና አርቲስት ሲሾሙ ሲሸልሙ አይ ፍቅር የሚባል አገር ማስተዳደሪያ አይዲዮሎጂ አለ፤ ፍርቅ ያሸንፋል ብሎ ለመጀመሪያ ግዜ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ አዲስ ፓራዳይም ፈልስፎ የፍቅር ፍልስፍናና ቅኔ ለኢትዮጵያ እያስተማረ ያለውን ታላቁ ሊቅ ባለቅኔ ሎሬት ፈላስፋና አርቲስት ቴዲ አፍሮን መንግስት አንድ ቀን እንኳ እውቅና ያልሰጠው ከሟቹ ጫታም መለስ እስከ ልበጩቤው አቢይ ድረስ ሁሉም አላማቸው ሕዝብና ሕዝብ በማፋጀት ለድፍን 50 አመት ያለማቋረጥ በሚሞተው ሕዝብ ህይወትና በሚፈሰው የተራ ሕዝብ ደም እነዚህ ቆሻሻ ገዦች ለስማቸው ፒራሚድ እያስገነቡ ስለሆነ ነው !!መቼ ነው የኢትዮጵያ ሕዝብ በነዚህ የደም ነጋዴዎች ላይ ሆ ብሎ ተነስቶ በቃችሁ ብሎ የፍቅርና ሰላም አይዲዮሎጂ ማንገስ የሚጀምረው?