የክስታኔ ምጅር ሴራ በዳሙ አውራጃ! የክስታኔ ጉራጌ ደመራ ስርዓት በዳሙ
Posted: 25 Sep 2022, 00:46
የቃላት ትግሩም፤ ምጅር = ደመራ፣ ገድራ = ችቦ፣ ዪቦ ዬቦ = ይሁን ይሁን አሜን አሜን ! ቦ (ግዕዝ) = ሆነ ። ዬቦ ላል = በላይ ይሁን! ታላቅ ይሁን ። የመጀመሪያው ገዳራ (ችቦ) በአያት ወይም አባት ወይም በትልቅ ሽማግሌ ቤት ውስጥ ተሎክሶ የወጣና የቀሩት የቤተሰብ አባላት ሁሉ እንደ እድሚያቸው ካባታቸው ወይም ከታላቃቸው በመሎከስ ደመራው ድረስ ዬቦ ዬቦ ዬቦ እያሉ ይሄዱና አያት /አባት ደመራውን ከወጋ በኋላ ሁሉም ችቦውን ይወጋል ። እዚህ ቪድዮ የምታዩት ያ ሴራ ነው ! ዳሙ ብዙ የክስታኔ ምሁራን እነ ፍቃዱ ገዳሙን አይነት ያፈራ አገር ነው ። ባልሳሳት ይህ ታቦር የሚባለው ተራራ መሰለኝ ! የኬር መስቀል ለኢትዮጵያ !!!