Page 1 of 1
ተራራማው፣ ውርጫሙ ታሪካዊው የክስታኔ መሰረት አይመለል በክረምት !! መልካም መስቀል!!
Posted: 24 Sep 2022, 01:21
by Horus
ክስታኔ ጉራጌዎች ቤት አሰራራቸውን ከሳር ወደ ቆርቆሮ እየለወጡ ነው ቅርጹን ሳይለውጡ ! አገሩ በሙሉ ቤተ ክርስቲያን ይመስላል! ደስ ሲል (የግል ቪዲዮ) ይህ እንግዲህ ምንም ስብከት የሌለው ሃቀኛው ባላገር ማለት ነው ! አይመለል የፈረሰኞቹ አገር !
Re: ተራራማው፣ ውርጫሙ ታሪካዊው የክስታኔ መሰረት አይመለል በክረምት !! መልካም መስቀል!!
Posted: 24 Sep 2022, 01:57
by Horus
ቤቱ ወለል ላይ ተነጥፎ፣ ተዘርግቶ ምታዩት በኮባና ቃጫ የተሰራ ምንጣፍ ሲሆን ሶስት አይነት ምንጣፎች አሉ። አንዱ ቅጭቀጨ ይባላል አነስ ያለ አሰራሩ ተራ ሆኖ ከቦታ ቦታ የሚዘረጋ ነው ። ፈረንጆች ኤሪያ ራግ ይሉታል ።
ሁለተኛው እዚያ ያያችሁት ጂበ ይባላል ፣ መደበኛ ምንጣፍ ማለት ነው ። እዚያ ያላያችሁት ለበአልና ለልዩ ቀን የሚወርድ የልፍኝ ምንጣፍ በጣም ረቂቅ ሆኖ ተለቅሞ የሚሰራ አንጮት ይባላል። በማንኛውም ጉርጌ ባላገር ቤት ወለል ዝም ብሎ አፈር ላይ መቀመጥ የለም። ምንጣፍ ከመነጠፉ በፊት ወለሉ በየግዜ ቀይ አፈርና እበት ተቀላቅሎ ይቀባል ። እዚያ ላይ ጂበ ይነጠፋል።
Re: ተራራማው፣ ውርጫሙ ታሪካዊው የክስታኔ መሰረት አይመለል በክረምት !! መልካም መስቀል!!
Posted: 24 Sep 2022, 02:20
by Horus
አሁን ከዚህ በታችህ ያለውን የወለኔ ጉራጌ ሰርግ ደሞ ተመልከቱ ። አይመለል ከምታዩት የክስታኔ ባህል አንድ ነው (10 ደቂቃ ላይ ተመልከቱ) ። የአጋሮ ተወላጅ የሆነው አቢይ ግን ወለኔን ከጉራጌ ለመለየት ብዙ ግዜ ቃላት ወርውሯል ። ዞሮ ዞሮ ይህ ብልጽግና የሚባል የጉራጌ ጠላት መወገድ ያለበት ቡዲን ነው ።