Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42887
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የክስታኔ ጉራጌ የልማት ጀግኖች ታሪክ! ሜጫና ቱለማ መረዳጃ ማህበር ከምን ተጸነሰ?

Post by Horus » 23 Sep 2022, 15:19

ከአለም ገና እስከ ወላይታ ሶዶ የመንገድ ግምባታ ታሪከኞች !! አባታችን ለሱና ለ7 ልጆቹ ብር እያስያዘ ጠቅላይ ቢሮ መርካቶ ማዘጋጃ ቤት ወስደን እንሰጥ ነበር ። የድሮ ጠቅላይ ቢሮ ዛሬ የመርካቶ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ተሰርቶበታል! እኛ ህጻናት ሆነን ስማቸው ገናና የነበሩት ያገር አባቶች ዝርዝር ያስገርማል!!! ከታች ከንጉስ ሃይለ ስላሴ ጋር የምታዩዋት ያስፋ ወሰን ቡና ቤት ባለቤት ጊስቴ ዘምዘም ገርቢ ናት!


Last edited by Horus on 23 Sep 2022, 15:54, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 42887
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የክስታኔ ጉራጌ የልማት ጀግኖች ታሪክ

Post by Horus » 23 Sep 2022, 15:50

ታሪክ ለማታውቁ ኦሮሞች ይህን እወቁ ።

ዛሬ እዚህ የደረሰው የኦሮሞ ብሄረተኝነት የተጸነሰው እዚህ የክስታኔ መንገድ ስራ ድርጅት ውስጥ ነው ። አሁን ሶዶ ጂዳ ኦሮሞ ነኝ ብሎ መለስ ፕሬዚዳንት ያደረገው መቶ አለቃ ግርማ ለዚህ ድርጅት ቅርብ ነበር። ያኔ የዛሬ ሶዶ ጂዳ ኦሮሞች በዚያ ዘመን ክስታኔዎች ነበሩ ። እኛ ላሊጌ ወይም ሰሜኖች እንላቸው ነበር ።

ትንሿ ጉራጌ የህብረት ስራና እድገት ባህል መፍጠርና በመገዱ ዙሪያና ምክኛት በተፈጠረው መነቃቃት እነ ታደሰ ብሩና ሌሎችም ያካባቢው ኦሮሞ ጉምቱዎች ትንሿ ጉራጌ ይህን መስራት ስትችል እኛስ ብለው በቀጥታ የክስታኔ መረዳጃ ሞዴል ቀስመው የሜጫና ቱለማ መረዳጃ ማህበር ብለው አቋቋሙ ።

የዛን ቀና ያኔ የኦሮሞ ብሄረተኘትና ዛሬ የምታዩትን አልፍ አዕላፍ እንደ አሸን የፈላው የኦሮሞ ጉዳይ ስረ መሰረቱ ያ የጉራጌ ድርጅት ነው። ከሜጫና ቱለማ መረዳጃ ማህበር በፊት ምንም አይነት የትም ቦታ የኦሮሞ ንቅናቄ አለነበረም ። ከዚያም እነማሞ መዘምር መሰሎች በየአሩሲው እየዞሩ ለመረዳጃና እድገት የቆመው ሜጫ ቱለማ የፖለቲካ ጉዳይ ሆነ!

ዛሬ ዛሬ እነአባዱላ፣ እነሺመልስ አዱኛ፣ እነአቢይ አህመድ ጉራጌ ክልል አይገባውም ሲሉ እነታደሰ ብሩና ማሞ መዘምር መቃብራቸው ወስጥ ሆነው በሰሙ! ግዜ የማያሳየን ነገር የለም!!!

Post Reply