Page 1 of 1

"ጦርነት ለማንም የማይጠቅም ነው:: በወንድማማች መካከል ሲሆን ደግሞ የበለጠ ያቆስላል::" ዲ/ን ሄኖክ ኃይለ (FB post with 20k likes)

Posted: 22 Sep 2022, 19:39
by sarcasm
ጦርነት ለማንም የማይጠቅም ነው:: በወንድማማች መካከል ሲሆን ደግሞ የበለጠ ያቆስላል::

ጦርነት ለማንም የማይጠቅም ነው:: በወንድማማች መካከል ሲሆን ደግሞ የበለጠ ያቆስላል:: እንደ ዲያቆን ዶ/ር ቢንያም ያሉ ወጣት ወንድሞችን ሊያሳጣንም እንደሚችል ማየት ደግሞ ልብ ይሰብራል:: ዲያቆን ቢንያም ጦርነቱ እንዳይመጣ ያልፈነቀለው ድንጋይ አልነበረም::

ከዲያቆን ዶክተር ቢንያም ጋር ከጦርነቱ በፊት በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ከጦርነቱ ጀምሮ ደግሞ መንገድ እስከተዘጋ ድረስ በበጎ አድራጎት ሥራዎች አብረን ነበርን:: በመከራ ውስጥ ሆኖ ሰብእናውና በእግዚአብሔር ላይ ያለው እምነት ያልተናወጸ ውድ የቤተ ክርስቲያን ልጅ ነው::
አሁንም ቤተሰቦቹን አጥቶና ተጎድቶ ትሕትናው አልተለወጠም::

ውድ ወንድሜ አስተዋይ ጓደኛዬ ቢኒ መትረፍህን በቪድዮ እስካይ ድረስ እጅግ ተጨንቄ ነበር:: ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለ "ለሞት እንኳ ቀርቦ ነበርና፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ማረው፥ ኀዘን በኀዘን ላይ እንዳይጨመርብኝ ለእኔ ደግሞ እንጂ ለእርሱ ብቻ አይደለም" እንዳለው እግዚአብሔር ለአንተ ብቻ ሳይሆን እኛንም ከማንጽናናው ኀዘን ጠበቀን:: (ፊልጵ. 2:27)

የምናውቀውን ተናገርን እንጂ የማናውቃቸው ለሀገር ብዙ ነገር የሚያበረክቱ ውድ ልጆችን በየሰዓቱ እያጣን ነው::


ጦርነቱን ማስቆም የሚችሉ ሁሉ ይህንን ጥፋት እንዲገቱልን ከተጀመረበት ዕለት ጀምሮ እንደተማጸንነው አሁንም እንለምናለን::
እግዚአብሔር እሳቱን ያብርድልን:: ልባቸው የተሰበረውን ይጠግንልን::

"አቤቱ ስለ ምን ለዘላለም ትረሳናለህ?
ስለ ምንስ ለረጅም ዘመን ትተወናለህ?
አቤቱ፥ ወደ አንተ መልሰን እኛም እንመለሳለን፤
ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድስ" ሰ.ኤር. 5:21

Please wait, video is loading...