Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

Do you know the Lion of Judah (ሞዓ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ) is the King of the World?

Poll ended at 30 Sep 2022, 11:59

1) Yes
23
79%
2) No
6
21%
 
Total votes: 29

Abere
Senior Member
Posts: 15478
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: Do you know the Lion of Judah (ሞዓ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ) is the King of the World?

Post by Abere » 20 Sep 2022, 20:18

Glad to learn how knowledgeable and informed about the Lion of Judah (ሞዓ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ) in fact is the King of the World.

Union

Re: Do you know the Lion of Judah (ሞዓ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ) is the King of the World?

Post by Union » 20 Sep 2022, 22:30

Yes, Jesus himself is the lion of Judah.

All of our 225 kings are the lion of Judah! Our 1st king being "ቀዳማዊ ምኒልክ"!! He was appointed to transfer the power of God back to Ethiopia by bringing the Ark of the covenant!

Ethiopia is the spritual and historical leader of the world! Has always been!

Naga Tuma
Member+
Posts: 7423
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: Do you know the Lion of Judah (ሞዓ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ) is the King of the World?

Post by Naga Tuma » 21 Sep 2022, 10:55

Abere,

I am guessing that you translated the Ge’ez/Amharic expression ንጉሠ ነገሥት into King of the World.

I remember another Ethiopian on this forum calling him Emperor, which also didn’t sound right because ንጉሠ ነገሥት doesn’t mean Emperor. If my limited reading of history serves me right, he was locally known as ዓፄ or ንጉሠ ነገሥት። I understand that is also how he wanted to be known in local languages.

Most of us are speakers of English as a second or third language. Then we pick up English words like King and Emperor and impose them on local languages, instead of going around the other way, which is to understand local languages well enough and translate correctly the words and expressions in local languages into other languages.

In this case, what could be the correct translation of ንጉሠ ነገሥት into the English language? I do not know. I reacted to using Emperor then in passant. For well over a week now, after hearing the expression Imperial Family for the first time, I have been asking myself what the correct translation of ንጉሠ ነገሥት into the English language could be. Moreover, I have been wondering if he had ever expressed a sentiment like this anytime during his entire lifetime.

I have been trying to come up with a translation of ንጉሠ ነገሥት into the English language. King of Kings wouldn’t do fairly. I feel something amiss in translating ንጉሥ to King. Royal of the Royalties. Chancellor of the Royals? In the larger scale that you say here, Counsel or Chancellor of the Sovereigns?

May be with his expertise in the meanings of local words, Horus can shed some light on ንጉሠ ነገሥት as well as its context in ክብረ ነገሥት and ፍትሃ ነገሥት። That may in turn shed some light on why language matters and aged languages are like aged wines.

Abere
Senior Member
Posts: 15478
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: Do you know the Lion of Judah (ሞዓ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ) is the King of the World?

Post by Abere » 21 Sep 2022, 12:02

ወንድም ነጋ ቱማ፤

--እነኝህ ያነሳኸቸው ስያሜዎች ለምሳሌ ንጉስ፤ ዐጼ፥ንጉስ-ነግስት፥ ግርማዊ(ት)፤ ወዘተ የመሳሰሉት ትርጉም ማወቅ ተገቢ ነው። በተለምዶ ግን እንጠቀምባቸዋለን። የፈረንጆቹም ቢሆን ከእኛ አርፍደው ቢጀምሩት እንጅ ቀዳማዊ አይመስለኝም። ፈረንጆቹ ከመሬት መስፋፋት እና ግዛት አንጻር ነው ባይ ነኝ - ያአገረ ገዥነት አይነት። በካርታ ክፍፍሎሽ ላይ የተመሰረተ -የስልጣን ምንጩ የጉልበት የበላይነት ነው። የኢትዮጵያ ነገስታት ግን የስልጣን ምንጫቸው የተለየ ነው - ስዩመ እግዚአብሄር ነው። ብልጫው እና ልዩነቱ ከዚህ ላይ ነው። የፈረንጆች በካርታ ተከፍሎ የኢትዮጵያዊያን ግን ሉል እንኳን የሚገድበው አየደለም።

---አንተ እንዳልከው ወንድማችን ሆረስ ከቻለ ቢያብራራልን ዕውቀት ወደ ትውልድ ይተላለፋል።

--- ስለ ሞዓ አንበሳ ንጉሰ አጠቃቀም እና ትርጎሜ ወንስማችን አንድነት (Union) በጣም ግልጽ በሆነ ሁኔታ አስቀምጦታል። የኢትዮጵያዊያን ንግስና ከሰማይ የተወረሰ ነው እንጅ በጉልበት በሰው አይደለም። ቅብዐ ንግስናዊ ከሰማያዊ ህያው እግዜር የተወረሰ ነው።

--- << ሞዓ አንበሳ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ ሥርው ለዳዊት>> የሚለው < የዳዊት ዘር ሥር ከሆነው ከይሁዳ ነገድ የተወለደው አንበሳ አሸነፈ> ተብሎ የተነገረለት እየሱስ ክርስቶስ ነው። ይህ ከዳዊት ወገብ ዘር የወጣው እየሱስ ክርስቶስ የቀዳማዊ ምኒልክ ዘር ከሚመዘዝበት ነው። ይህ ማለት የኢትዮጵያ ንጉሳን ወይም ንግስት ስዩመ እግዚአብሄር ናቸው።

--- በአለም እስከ ዛሬ ሳያቋርጥ ሰባት ሺ አምስት መቶ አመታት በላይ ህያው የሆነ አምልኮተ እግዚአብሄር እና የነጻነት ታሪክ ቅርስ ይዞ የሚገኘው የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ነው። ዛሬ በኢትዮጵያ የምናየው ግጭት እና ጦርነት ይህን መለኮታዊ ስጦታ እና ታሪክ ለማጥፋት የሚደረግ የሰይጣናት ተግባር ነው። ጽድቅ ባለበት ሁሉ ኩነኔ ወይም ኃጥያት ይበዛሉ እንዳለው መጽሀፍ ቅዱስ በዚች አገረ አምላክ በሆነችው ኢትዮጵያ እጅግ ክፉ ነገር በዝቷል።

Naga Tuma wrote:
21 Sep 2022, 10:55
Abere,

I am guessing that you translated the Ge’ez/Amharic expression ንጉሠ ነገሥት into King of the World.

I remember another Ethiopian on this forum calling him Emperor, which also didn’t sound right because ንጉሠ ነገሥት doesn’t mean Emperor. If my limited reading of history serves me right, he was locally known as ዓፄ or ንጉሠ ነገሥት። I understand that is also how he wanted to be known in local languages.

Most of us are speakers of English as a second or third language. Then we pick up English words like King and Emperor and impose them on local languages, instead of going around the other way, which is to understand local languages well enough and translate correctly the words and expressions in local languages into other languages.

In this case, what could be the correct translation of ንጉሠ ነገሥት into the English language? I do not know. I reacted to using Emperor then in passant. For well over a week now, after hearing the expression Imperial Family for the first time, I have been asking myself what the correct translation of ንጉሠ ነገሥት into the English language could be. Moreover, I have been wondering if he had ever expressed a sentiment like this anytime during his entire lifetime.

I have been trying to come up with a translation of ንጉሠ ነገሥት into the English language. King of Kings wouldn’t do fairly. I feel something amiss in translating ንጉሥ to King. Royal of the Royalties. Chancellor of the Royals? In the larger scale that you say here, Counsel or Chancellor of the Sovereigns?

May be with his expertise in the meanings of local words, Horus can shed some light on ንጉሠ ነገሥት as well as its context in ክብረ ነገሥት and ፍትሃ ነገሥት። That may in turn shed some light on why language matters and aged languages are like aged wines.

Naga Tuma
Member+
Posts: 7423
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: Do you know the Lion of Judah (ሞዓ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ) is the King of the World?

Post by Naga Tuma » 21 Sep 2022, 19:03

ወንድም አበረ፤

ለማብራርያህ ኣመሰግናለሁ። የሃገራችን የቅኔ ኣርትስቱ የፍጥረት በር፣ ዞሮ መጀመርያ ብሏል።

የዳዊት ታሪክ ድንቅ ነዉ። የሙሴም እራሱን የቻለ ድንቅ ይመስለኛል። እሱም ሞኣ ኣይዴለም? ካልተሳሳትኩ የእሱ ቶራ ከዳዊት ታሪክ ይቀድማል። ያም ለላ ዞሮ መጀመርያ ይመስላኛል።

Horus
Senior Member+
Posts: 42883
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: Do you know the Lion of Judah (ሞዓ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ) is the King of the World?

Post by Horus » 21 Sep 2022, 20:42

ናጋ ቱማ ና አበረ፣
በችኮላ አንድ ሁለት ነገር ልበል።

አዲስ የወጣ መጽሃፍ Accidental Gods: On Men Unwittingly Turned Divine by Anna Della Subin (2021) አንብቡት፣ አበረ ከሚለው ጋር የተያያዘ ።

ናጋ ቱማ
የንጉስ ስረ ቃል ካ (Ka) ነው። የትንታዊ ግብጽ ቃል ሲሆን አጠቃላት ትርጉሙ ሃይል ማለት ነው ። ዛሬ የህዝብ ገዢ ሃይልም፣ የፈጣሪ ህይልም ትርጉም ከዚህ ስረቃል ይቀዳል ።
በግዕዝ ጋዝ፣ ገዥ፣ አጋዝ፣ አበጋዝ፣ ናጋዝ፣ ነጋዝ፣ ነጋሲ፣ ንጉስ፣ ንግስት እያለ ይረባል ። ለምሳሌ በፋርሲ እንዳለ ካን ሻ ሻህ ይሉታል ፣ ሻሃንሻ (ካህንካ) ማለት የንጉስ ንጉስ ማለት ነው። ነገስት የንጉስ ብዙ ስም ነው ። መጻፍ መጻህፍት እንደምንለው። ንጉስች ማለት ነው ፣ ንጉሰ ነገስት ማለት የንጉሶች ንጉስ ማለት ነው ። ጌታ፣ ጎይታ የሚለውም ስረቃሉ ካ (ጋ) ነው ።

ብክረነገስት የሚለው ዘ ግሎሪ ኦፍ ኪንግስ በትንሹ የተበላሸ ትርጉም ነው። አከበረ ማለት ወደ ላይ ከፍ አደረገ፣ አተለቀ፣ ማለቅ አደረገ፣ አመለከ ማለት ነው ። ማለቅ ማተለቅ ማለት ሲሆን ባረብኛና በጉራጌኛ ንጉስ ማለት ነው ። አረብ አል ማልክ ይለዋል ። ስለዚህ ክብረ ነገስት ማለት ንገስታትን የማንገሻ ስርዓት ማለት ነው እንጂ ዝም ብሎ አንድን ንጉስ ግልሪፍይ ማድረጊያ ማመስገኛ አይደለም። የኢትዮጵያ ነገስታት አሿሿም ሰርዓት ማለት ነው ። ለምሳሌ አንድ ሰው ንጉስ ለመሆን የሰለሞን ዘር መሆን አለበት፣ የመጀምሪያ ልጅ መሆን አለበት ፣ ካልሆነ ቀጥሎ ማን እንደሚሆን ፣ የማዕረኛ የበትረ መንግስት፣ የዘውድ አይነትና ስልጣም ወዘተርፈ። ባብዛኛው ከግብጽ ነገስታት የመጣ ነው ።

ስለ ቸኮልኩ እዚህ ላቁም! የኬር መስቀል!

ethiopianunity
Senior Member
Posts: 10982
Joined: 30 Apr 2007, 17:38

Re: Do you know the Lion of Judah (ሞዓ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ) is the King of the World?

Post by ethiopianunity » 22 Sep 2022, 12:42

The arc of the covenant is stolen in Tigray, why do you think Tigrayans act this way the devil is upon them. The anti christ will soon resurrect in Jerusalem, Israel.

Abere
Senior Member
Posts: 15478
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: Do you know the Lion of Judah (ሞዓ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ) is the King of the World?

Post by Abere » 22 Sep 2022, 12:44

ወንድማችን ሆረስ፤

ስለ ሰጠኸን ማብራርያ እጅግ እናመሰግናለን። እንድህ ፍንትው አድርጎ ዕውቀት እና ታሪክ የሚያካፍል ሰው መኖሩ ድንቅ ነው። አባቶቻችን ከሞኝ ደጅ ሞፈር ይቆረጣል እንደሚሉት፤ አንድ ነገር ከባህር ማዶ ካልመጣ በስተቀር ጥራቱን እና እውነትነቱን እንጠራጠረዋለን። ግን የእራሳችን ባህር ማዶ ተጠልፎ ወይም ተግዞ ሂዶ እንደ ገና ወደኛ መምጣቱን ማወቅ ይሳነናል። እኔ እንኳን የታሪክ ባለሙያ አይደለሁም ግን የአገሬ ታሪክ እጅግ ያስደንቀኛል - ለማወቅ ጉጉት አለኝ። ብዙው እውነትነት እንዳለው በፍጹም አምናለሁ።

ይህ ትውልድ አስተማሪ ይፈልጋል። እረኛ ያጣ የበግ መንጋ ነው። ተንኮለኞች በመንጋው መሃል የሃሰት ታሪክ እየፈጠሩ ( የዲስኩር መጽሃፍም እያሳተሙ) ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊ የሆነውን ትውፊት እና ታሪክ እያጠፉ ነው። የጥፋት ሃውልትም አቁመዋል። ዛሬ በሚልዮኖች የሚሞቱት በዚህ የሃሰት ተረት ነው። ፈረንጆች የእራሳቸውን ነገሥታ ታሪክ እና ገድል ጠብቀው ይዘው አበሻ የእራሱን የነገሰታት ስርዐት አፈራርሶ የሌሎች ንጉስ ለቅሶ ሊደርስ ይሄዳል። የሰላም እና የደህንነት አውታር የሆነውን ስርዐት በቅናት በማፈራረሱ ለ50 አመታት ቸነፈር፤ጦርነት፥ በሽታ (ኤድስ ወዘተ)፤ ስደት፤ልመና፥ ወዘተ በኢትዮጵያ ዘንድ ጎጆ አይደለም አዳራሽ እና እልፊኝ ሰርተዋል። በአጭሩ የአለፉት 4 አመታት ብቻ ይህ ትውልድ የሆነውን ሁሉ ላለመየት በህይወት ባይኖር መልካም ነበር። ኢትዮጵያ የመጨረሻ የሞት ሞት የሞተችበት ዘመን ቢኖር ይህ ዘመን ነው። 225 ነገስታት አልፈዋል በማንም ዘመን ይህ አልተፈጸመም። በኢንግላንድ እና በብሪታንያ ከ1200 አመታት ወድህ ብቻ 61 ነገስታት ነበር።ኢትዮጵያ ከአገር በፊት አገር የነበረች አሁን የእራሷን አጥታ የሰው ትቀላውጣለች። ይህ ትውልድ የታሪክ ቀላዋጭ ትውልድ መሆኑ ያሳዝናል። አንድ ወጥ አገራዊ ታሪክ እያለን ዛሬ ግን አስር አይነት ትርግም በሃሰተኞች ተሰጥቶት ሚልዮኖች እያለቁ ነው። እውነትን የተራበ ትውልድ በሀሰት ስካር የሚያልቅ

Horus wrote:
21 Sep 2022, 20:42
ናጋ ቱማ ና አበረ፣
በችኮላ አንድ ሁለት ነገር ልበል።

አዲስ የወጣ መጽሃፍ Accidental Gods: On Men Unwittingly Turned Divine by Anna Della Subin (2021) አንብቡት፣ አበረ ከሚለው ጋር የተያያዘ ።

ናጋ ቱማ
የንጉስ ስረ ቃል ካ (Ka) ነው። የትንታዊ ግብጽ ቃል ሲሆን አጠቃላት ትርጉሙ ሃይል ማለት ነው ። ዛሬ የህዝብ ገዢ ሃይልም፣ የፈጣሪ ህይልም ትርጉም ከዚህ ስረቃል ይቀዳል ።
በግዕዝ ጋዝ፣ ገዥ፣ አጋዝ፣ አበጋዝ፣ ናጋዝ፣ ነጋዝ፣ ነጋሲ፣ ንጉስ፣ ንግስት እያለ ይረባል ። ለምሳሌ በፋርሲ እንዳለ ካን ሻ ሻህ ይሉታል ፣ ሻሃንሻ (ካህንካ) ማለት የንጉስ ንጉስ ማለት ነው። ነገስት የንጉስ ብዙ ስም ነው ። መጻፍ መጻህፍት እንደምንለው። ንጉስች ማለት ነው ፣ ንጉሰ ነገስት ማለት የንጉሶች ንጉስ ማለት ነው ። ጌታ፣ ጎይታ የሚለውም ስረቃሉ ካ (ጋ) ነው ።

ብክረነገስት የሚለው ዘ ግሎሪ ኦፍ ኪንግስ በትንሹ የተበላሸ ትርጉም ነው። አከበረ ማለት ወደ ላይ ከፍ አደረገ፣ አተለቀ፣ ማለቅ አደረገ፣ አመለከ ማለት ነው ። ማለቅ ማተለቅ ማለት ሲሆን ባረብኛና በጉራጌኛ ንጉስ ማለት ነው ። አረብ አል ማልክ ይለዋል ። ስለዚህ ክብረ ነገስት ማለት ንገስታትን የማንገሻ ስርዓት ማለት ነው እንጂ ዝም ብሎ አንድን ንጉስ ግልሪፍይ ማድረጊያ ማመስገኛ አይደለም። የኢትዮጵያ ነገስታት አሿሿም ሰርዓት ማለት ነው ። ለምሳሌ አንድ ሰው ንጉስ ለመሆን የሰለሞን ዘር መሆን አለበት፣ የመጀምሪያ ልጅ መሆን አለበት ፣ ካልሆነ ቀጥሎ ማን እንደሚሆን ፣ የማዕረኛ የበትረ መንግስት፣ የዘውድ አይነትና ስልጣም ወዘተርፈ። ባብዛኛው ከግብጽ ነገስታት የመጣ ነው ።

ስለ ቸኮልኩ እዚህ ላቁም! የኬር መስቀል!

Horus
Senior Member+
Posts: 42883
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: Do you know the Lion of Judah (ሞዓ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ) is the King of the World?

Post by Horus » 22 Sep 2022, 14:47

አበረ፣
በትክክል። የጥንታዊት ግብጽ የ5 ወይም 6 ሺ ዘመን ስልጣኔ አካል የነበሩት ሁዋላም ግብጽ ስትፈርስና ህዝቧም ሲበተን የዚያን ቅርስ ይዘው እስከ ዛሬ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ናቸው። ከዘመን ርዝመት እና ልክ ባልከው የዘመናት ጦርነትና ውድመት ሕዝባችን ታሪኩን ፈጽሞ ረስቶ ወደ ድንቁርናና ጭለማ ዘመን ስለገባ አይደለም የ5 ሺ አመት የ5 መቶ አመት ታሪካችን አናውቅም ። አንድ ጥያቄ ልተውልህ! በረጅሙ የግብጽ ስልጣኔ ሁሉ አባይ (ያባይ ወንዝን አባይ ያሉት ግብጾች ናቸው! Hapi አንዱ ህይወት ሰጭ አምላካቸው ነበርና) እንደ እግዚአብሄር ሲያመልኩት የኢትዮጵያና ግብጽ ግንኙነት ምን ሊሆን ይችል ነበር?

አንድ የቅርብ ምሳሌ ልስጥህና ላቁም ።
በ1510 ዓም በፈረንጆቹ የሮማ የቫቲካን ካህናት ኢየሩሳሌም ይመጣሉ ። ያኔ ኢትዮጵያ ከአንድ በላይ ገዳማት በኢየሩሳለምና በምድረ ፍልስቴም ነበሯት ። ታዲያ እኒያ የቫቲካን ቄሶች በኢትዮጵያ መነኩሴዎች እጅ የነበሩት የመጻህፍት ብዛት ማመን አቃታቸው ። ልብ በል! ይህ ፋክት ነው ። በሜዲኢቫል አውሮፓ መላ ያውሮፓ ሞናስተሪዎች ተደምረው ከነበራቸው መጻህፍት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናት ይበልጥ ነበራቸው ። 1500 ኦርቶዶክስ እስከ ዛሬ ጂቡቲ እነ ባሌ፣ እነአሩሲ መላ ዳሞት ሸዋ ታች ድረስ ነበር ። ልብ በል ዝቋል አቦ፣ ያርባ ምንጭ አቦ ነበር ። ያ ሁሉ ግራኝ መጥቶ ከማቃጠሉ በፊት ።

እናም እነዚያ የቫቲካን ቄሶች የናንተን ጥበብ ላውሮፓ አስተምሩልን ብለው ሁለት መነኩሴዎችን መጻሃፍት አሲዘው ወደ ሮማ ወሰዷቸውና እዚያ ቫቲካ ነዋሪ ሆነው የላቲን ቋንቋ ተምረው የላቲና ግዕዝ መዝገበ ቃላት እንዲሰሩ አደረጉ ። በዚያም ምክኛት ዛሬ ማንም ስራዬ ብሎ ያላጠናው ምናልባትም እስከ 30% የላቲን ቃላት ኢቲሞሎጂ ግዕዝ ነው ። መነኩሴዎቹም እዚያው ኖረው እዚያ የተቀበሩ ይመስለኛል ። ጀርመኖችም እንዲሁ ግዕዝን በብዛት ቋንቋቸው ውስጥ ወስደዋል። እርግጥ ዛሬ ባውሮፓም በካናዳም ግዕዝ በግራጁዌ እስኩል ደረጃ ይሰጣል ።

እንግዲህ የጥንታዊ ግብጽ ቋንቋ የት ገባ ካልከኝ ወደ ሴም ቋንቋ ተለወጠ ! ጥንታዊ የሴም ቋንቋ ግዕዝ ነው ። የሴም ቋንቋ አባት ማነው? ካልክ ቀምጥ ወይም ጥንታዊ ግብጽ ነው። ሌላ የሴም ቋንቋ አባት የለም!!!!! ያበሻ ዘር ይህን ሁሉ ምስጢር ይዞ ነው በድንቁርና እርስ በርሱ ሲባላና የምራብ ለማኝ ሆኖ የቀረው!! እግጅ እጅግ የሚያሳዝን ታሪክ ነው በውስጣችን ያለው!
ኬር

Naga Tuma
Member+
Posts: 7423
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: Do you know the Lion of Judah (ሞዓ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ) is the King of the World?

Post by Naga Tuma » 23 Sep 2022, 15:33

ሆረስ፤

ወደዚህ ርዕስ ኣሁን መመለሴ ነዉ። ለማብራርያህ ኣመሰግናለሁ።

ስለቃላቱ የበለጠ ሳነብ ተጨማሪ ጥያቄዎች ይመጣሉ። እነዚህን ጥያቄዎች በሰፊዉ መመለስ የሚችሉት የመሠረት፣ ስደት፣ እና ጉብኝት ታሪኮችን በጥልቀት ማወቅ ይመስላኛል።

ስለእነሱ እያሰላሰልኩ ሰንብቼ የአበረን የእኛዉ ከባህር ማዶ ተግዞ መመለስ ኣገላለጽ ሳነብ ተገረምኩኝ። የቶራ ኣባት ራሱ ሙሴ ጥንታዊ ኢትዮጵያዊ የነበረ ከሆነ የሰለሞንስ ዘር ማን ነበር ሊባል ነዉ?

የንጉስ ቃል መሠረት ካ ከሆነ በሰፊዉ ያልተረሳ ነዉ ማለት የሚቻል ይመስለኛል። ካልተሳሳትኩ ንጉስ እና ነጋሳ የተቀራረበ ትርጉም ኣላቸዉ፣ ተመሳሳይ ካልሆኑ። ነጋሳ እና ነጋ ደግሞ ተወራራሽነት ያላቸዉ ይመስለኛል። ነጋ ሰላም ማለት ነዉ።

ንግስና የሰላም አበጋዝነት መንፈስ ያለዉ ይሆን? ንጉሠ ነገሥት የንጉሦች ንጉሥ ከማለት ይልቅ ስለንግስና ስርዓት ይሁን ብዬ እጠይቃለሁ። ስለክብረ ነገሥት እና ንጉሠ ነገሥት በድምር እያሰላሰልኩ።

ክብር የሚለዉ ቃል ጋር ተመሳሳይ በርካታ ቃላትን እኔም ኣስተዉያለሁ። ከፍ፣ ካሳ፣ ኪሲ፣ ኩሳ፣ ኮሲ።

ይህ ደግሞ መሠረታዊ ወደ ሆነዉ የጥንት ጊዜ ዕፅዋትን እና ኣህዛብን ማለማመድ ይመልሰናል። እነሱም የኢትዮጵያ ሌሎች ታሪካዊ እሴቶች ናቸዉ።

ስለኢትዮጵያ ገዳማት መጻህፍት ከተነሳ የተቃጠለዉ የኣሌክሳንድርያ ቤተ መጻህፍት ዉስጥ ጋሊልዮ የደረሰበት ዕዉቀት ነበረ የሚባል ታሪክ ሰምተሃል? ዕዉነት ይሁን ኣይሁን ኣላዉቅም።

Post Reply