ናይጄሪያዊው << ዩኒቨርስቲዬ ዲግሪዬን ወስዶ ብሬን ይመልስልኝ>> እየለ ነው። በአገሩ የጎሳ ፓለቲካ ፓርቲ የለም እንደ የካድሬ አባል ሁኖ ብር የማያፍሰው? እባካችሁ ብልጽግናዎች ምክር ስጡ
Posted: 17 Sep 2022, 10:44
ናይጄሪያዊው << ዩኒቨርስቲዬ ዲግሪዬን ወስዶ ብሬን ይመልስልኝ>> እየለ ነው። በአገሩ የጎሳ ፓለቲካ ፓርቲ የለም እንደ የካድሬ አባል ሁኖ ብር የማያፍሰው? እባካችሁ ብልጽግናዎች ምክር ስጡት።
አንድ የ36 ዓመት ናይጄሪያዊ ተመርቆ ሥራ ማጣቱ አበሳጭቶት ለተማረበት ዩኒቨርስቲ ያልተመለደ ጥያቄ አቅርቧል።
ኦሉዳሬ አላባ የተባለው ይህ ሰው ለዩኒቨርስቲው ያቀረበው ጥያቄ ለትምህርት የከፈለው ገንዘብ እንዲመለስለት ነው።
በፈረንጆቹ 2015 የተመረቀው ይህ ግለሰብ ዲግሪውን ይዞ ሥራ ለማግኘት ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም።
ሆኖም ዲግሪው ሥራ ሊያስገኝለት ስላልቻለ 'በቃ እንዲያውም ዲግሪውን ወስዳችሁ ብሬን መልሱልኝ' ብሏል።
ይህ ናይጄሪያዊ ለ5 ዓመታት ተምሮ ዲግሪ ያገኘው በእርሻና የገጠር ልማት ዘርፍ ነበር።
ይህ ያልተመለደ ጥያቄ የቀረበለት ዩኒቨርስቲ ለጊዜው ምላሽ ባይሰጥም የኦሉዳሬ አላባ ጥያቄ የብዙዎችን ስሜት በመንካቱ በማኅበራዊ ሚዲያ ገንዘብ እየተዋጣለት ይገኛል።
ባለፈው ሳምንት ይህ ናይጄሪያዊ ባለ ዲግሪ ወደተማረበት የመንግሥት ዩኒቨርስቲ ሲያቀና በቪዲዮ ተቀርጾ ነበር።
በደቡብ ምዕራብ ናይጄሪያ የሚገኘው ላዶኬ አኪንቶላ የሚባለው ዩኒቨርስቲ ተመልሶ በመግባት አስተምራችሁ የጫናችሁልኝ ዲግሪ ምንም አልረባኝም፤ ዲግሪውን ውሰዱ ብሬን መልሱ ብሏል።
ይህ ያልተመለደ ጥያቄ በማኅበራዊ ሚዲያ ከተጋራ በኋላ ሰፊ መነጋገሪያ ሆኖ ብዙዎች ለሥራ አጡ ከንፈር መጠውለታል።
ከንፈር መምጠጥ ብቻም ሳይሆን ገንዘብ ተዋጥቶለታል።
ይህ ባለ ዲግሪ ኋላ ላይ ለቢቢሲ ዩሩባ እንደተናገረው ዲግሪውን ለማግኘት 5 ዓመታት እንደለፋና ብዙ የብድር ገንዘብ እንደከሰከሰ አብራርቷል።