Natnael Mekonnen
እልፍ አእላፍ ገደልኩ፣ ማረኩ እያለች ስትፎክር የነበረች ጁንታ የድረሱልኝ ጩኸቷን ታቀልጠው ጀምራለች ። ጭፍራዎቿንና ተከፋይ ባዕዳን ጋሻ ጃግሬዎቿን ጩሁልኝ፣ ድረሱልኝ እንዲያው ቢቻል የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ተጥሶ ቢሆን ከበረራ ነፃ ቀጣና ካልተፈጠረ እስትንፋሴ ሊቋረጥ ነው ማለት ጀምራለች። በመሰረቱ ከቀቢፀ ተስፋ የመነጨ ፍላጎት እንጂ ይህ እንደማይሆን እሷም አጫፋሪዎቿም ያውቁታል። ነገሩስ የቸገረው... ሆነና ነው። የጨነቀ ለት!
ይህ ጊዜ የደርግ ዘመን አይደለም። በባዕዳን ጀርባ ታዝሎ አገር አምሶ ስልጣን መቆናጠጥ የተበላ ዕቁብ ነው። ይልቅ ሕዝብ አታስጨርሱ። የትግራይ ሕዝብም ከክፍለ ዘመን እንግልት በኋላ እፎይ ይበልበት። ኢትዮጵያችንም ከቦርቧሪ ሰርሳሪ ባንዳ ውጋት ትገላገል።
አርፋችሁ እጃችሁን ስጡ!!!