Page 1 of 1

በዚህ ጦርነት ያለአግባብ ተደጋግመው የሚነሱ ሁለት ቃላቶች(Misused and abused words): 1) ጠጉረ-ልውጥ 2) ድርድር

Posted: 15 Sep 2022, 15:36
by Abere
በዚህ ጦርነት ያለአግባብ ተደጋግመው የሚነሱ ሁለት ቃላቶች(Misused and abused words): 1) ጠጉረ-ልውጥ 2) ድርድር

እነኝህ ሁለት ቃላቶች ያለአግባቡ አንድም በተለምዶ ወይ በስህተት ወይ በተንኮል ካልሆነ በስተቀር አሁን ያለውን ግጭት እና የግጭቱ ተዋንያንን ባህርይ ይሁን ማንነት አየገልጹም።

1ኛ) ጠጉረ-ልውጥ የሚገልጸው የሰውን ዘር አይነት ሲሆን በጣልያን ወረራ ጊዜ ፈረንጅ እና የጥቁር አበሻ ግጭት ስለነበረ። ይህን ኮድ ተጠቅመውበታል። አርበኞቹ በሰፈራቸው ወይም በአካባቢው ጠጉረ-ልውጥ ሰው ታይቷል ወይስ አልታየም ብሎ በማጣራት በጥላት ላይ አደጋ ይጥላሉ ወይም እራሳቸውን ይጠብቃሉ። ይህ ቃል አንድ ዘር እና አንድ አይነት ህዝብ ለሆነ ግን ገላጭ አይደለም። ያለ አዋቂ አይሁን። ወያኔን በጥጉር ሳይሆን በግብር ነው መለየት የሚቻለው።

ለምሳሌ አውቶብስ ተሳፍረው ከደሴ ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ ወሎየዎች ጠጉረ-ልውጥ ከሆኑ ጠጉራቸው ምን አይነት ቀለም ነበር? ዐይጥ ወያኔን ለማሳደድ ክምሩ በሙሉ መቃጠል አለበት ወይ? ወይስ የእስራኤሉ ንጉስ ሄሮድስ ህጻኑን እየሱስን ንግስናውን እንዳይቀማው ለመግደል ሲል በአገሪቱ የሚገኙ ወንዶች ህጻናትን በሙሉ እንደጨፈጨፈው አሁንም የኦሮሙማው መንግስት የዛሬ 2,000 አመታት በፊት የነበረውን ስልጣኔ እየተከተለ ነው። ለመሆኑ አዲስ አበባ ያለ ትግሬ ጠጉ- ልውጥ ወያኔ ለመሆን ከፈለገ ከሚፈለገው በላይ እኮ ነው። ይህ የፈረደበት ወሎ 1ኛ ደረጃ ገፈት ቀማሽ ነው።ልበ-ልውጥ እንጅ ጠጉረ ልውጥ ሰው በኢትዮጵያ የለም - ከውጭ አገር ዜጋ ወይም ፈረንጅ በስተቀር። ደርግ እንኳን ይጠቀምበት የነበረው ገላጭ ቃላቶች ባንዳ፤ ወንበደ፤ የእናት ጡት ነካሽ ነበሩ።

2ኛ) ድርድር የሚለው ቃል በፍጹም የወያኔ እና የአብይ አህመድን ኦነግ-ብልጽግና መካከል ያለውን ሁኔታ አይገልጽም። ውይይት ቢባል ይሻላል። ምክንያቱም መሰረታዊ ቅራኔ የላቸውም።