Page 1 of 1

የቀድሞው የኢህአደግ ጠቅላይ ሚንስትር ኃ/ማርያም ደሰላኝ የጎሳ ፌዴሬሽን ክልል መፍረስ አለበት ከዚህ በታች ዝቅ እንድንል የሚፈቅድ ህሌና መኖር ይለበትም በለዋል።ዐብይ አህመድስ?

Posted: 13 Sep 2022, 16:35
by Abere
የቀድሞው የኢህአደግ ጠቅላይ ሚንስትር ኃ/ማርያም ደሰላኝ የጎሳ ፌዴሬሽን ክልል መፍረስ አለበት ከዚህ በታች ዝቅ እንድንል የሚፈቅድ ህሌና መኖር ይለበትም በለዋል። ዐብይ አህመድ cosigned አድርጓል?

The most clear inconsistency of Abiy Ahmed and the war he engaged the country is the inconsistency of the ultimate goal of the war. If Abiy Ahmed is a consistent and adherent supporter of the TPLF's illegal constitution and ethnic federation, this war with TPLF is not his war unless it is about keeping his own seat. Ethiopians expect more than this, they want the bad legacy of TPLF be gone. More than 2 million people are could have been dead from this war only because of this ethnic federation and the genocidal constitution. It is insane to die just to keep this genocidal constitution.

Ex-Prime Minster, Hailemariam Desalegn, once again, proved his calm and collected behavior with an intent to rescue the country again. He resigned in the sprit to spare the country from further violence, but unfortunately that opportunity was hijacked and misused. The fact the ex-PM called out the TPLF's ethnic federation is genocidal and the mother of all instabilities i
s commendable and should be listened by all.

Re: የቀድሞው የኢህአደግ ጠቅላይ ሚንስትር ኃ/ማርያም ደሰላኝ የጎሳ ፌዴሬሽን ክልል መፍረስ አለበት ከዚህ በታች ዝቅ እንድንል የሚፈቅድ ህሌና መኖር ይለበትም በለዋል።ዐብይ አህመድስ?

Posted: 13 Sep 2022, 22:07
by Horus
አበረ፣
እኔ ሃይለማሪያም ደሳለኝን የተገነዘብኩት በሌላ መንገድ ነው ። ልብ ካልክ የአቢይ አህመድ አስገዳጅ የጉልበት እጆች ኮማንድ ፖስት የሚባል ዱላ ይዘው ከመግነናቸው ቀደም ብሎ ደቡብ ካሉት 54 ጎሳዎች ውስጥ 11ዱ ክልል ለመሆን ወሰነው ነበር ። ባገሪቱ ሕግ መሰረት ። ከ6 በላይ ዞን ለመሆን ወስነው ነበር ። ከዚህ ውስጥ ከፍተኛ ንቅናቄ አድርጎ 38 በላይ ሰዎች ተገለውበት በሃይል ጸጥ የተደረገው ወላይታ ነው ።

ዛሬ እነዚያ 18 የራሳቸውን ውሳኔ በሃይል የተጨፈለቀባቸው ብሄሮች ሁሉ ያላቸው አመለካከት ወይ የጎሳ ስርዓት ፈርሶ ክልሎች ሁሉ የፍረሱ አለያም የደቡብ ሕዝብ ለሌሎች የተሰጠው መብት ይሰጥ የሚል በጣም ቀጥተኛ የሆነ ህጋዊ ጥያቄ በውስጣቸው እየጋለ ነው ያለው ።

የኦሮሞ ተረኞችና ያማራ ኦሮሙማ አሽከሮች እንደ ሰጎን እራሳቸውን አሸዋ ውስጥ ደብቀው የሚያልፉት ጉዳይ አይደለም ።

ሃይለማሪያም የሌሎችን ክልልና ዉሃ ሲያመላስ ኖሮ የራሱ ብሄር እንኳ የሚጠይቀውን ጥያቄ ማስመለስ ያልቻለ የታሪክ እንግዴ ልጅ ሆኖ የቀረ ሰው መሆኑን ዛሬ የገባው ይመስለኛል።

አሁን ልክ ጉራጌ የሚለውን ቃል ነው እየደገመ ያለው ። ህግ መንግስቱ ወይ ይቀየር ወይ ይከበር! ይህ ነው የደቡብ ሕዝብ ብቸኛ የትግል ጥያቄ! የፌዴሬሽን ምክር ቤት እበቶች ተሰብስበው አንድ ነገረ ወሰኑና ኮማንድ ፖስት ላኩ ማለት ሕዝቡ ተቀበለው ማለት አይደለም! የደቡብ ቀውስና አመጽ ገና መጀምሩ ነው እንጂ ማብቃቱ አይደለም ።

ያ ነው የሃይለማሪያም አዲስ የዜጋ ፖለቲከኛነት አዋጅ! በርግጥም ቢያንስ ያማራ ክልል ብቻ የደቡብን አቋም ቢይዝ ኤትኒክራሲ የሚባለው የትግሬ ቂጣ ፍርስርሱ ይወጣ ነበር! ይህም ሆነ ያ ይህን ቂጣ ጉራጌ እስከ መጨረሻው ይፈትነዋል! ሕገ መንግስቱ ወይ ይቀየራል ! ወይ ይከበራል! በቃ!

Re: የቀድሞው የኢህአደግ ጠቅላይ ሚንስትር ኃ/ማርያም ደሰላኝ የጎሳ ፌዴሬሽን ክልል መፍረስ አለበት ከዚህ በታች ዝቅ እንድንል የሚፈቅድ ህሌና መኖር ይለበትም በለዋል።ዐብይ አህመድስ?

Posted: 14 Sep 2022, 11:44
by Abere
ሆረስ፤

በሰነዘረከው ሃሳብ እስማማለሁ። ኃይለማርያም ደሳለኝ በእርግጥ ወያኔ ስትጠቀምበት የኖረችበት የማዕድ ቤት እቃ ነበር ቢባል ማጋነን አይሆንም። ሲያገለግል የኖረው የአናሳውን የትግሬ ጎሳ እንጅ ሌላውን ኢትዮጵያዊ አልነበረም። ወዶ ፈቅዶ ይሁን ተገዶ እራሱ ብቻ ያውቃል። ብዙ ህዝብ ግን ወዶ ቢጠጋም ፈቅዶ መሄድ አይችልም ነበር - ተገዶ የሚኖር ሎሌ ነበር። ያም ሆነ ይህ ግን ትሻልን ሰድጄ ትብስን አመጣሁ ይሉ ዘንድ ሊያስመሰግነው የሚችል ስራ ሰርቷል - ደም ሳያፋስ ስልጣን ለቋል። ምናልባት እንደ ዛሬዎቹ ወላይታ ተረኛ እንድሆኑ ባለመስራቱ ይሆን ብቻውን ስለቀረ? ወይስ ወያኔ ፍቃድ ሰጥታው? ወይስ ህሌናው ተጸይፎ? የትም ፍጭው ዱቄቱን አምጭው ነው ስልጣኑን ለቆ እንካችሁ ብሎ ለኢትዮጵያዊያን ሰጠ። ችግሩ ምድረ ውታፍ ነቃይ ዲያስፓራ ተብየ ስንት አመት ስትጮህ እንዳልኖረች በአንድ ምሽት ሻንጣዋን ሸክፋ ጉልበት ጫማ እየሳመች አብይ አህመድ ዘንድ አድስ አበባ ገቢ ሆነች እና ነብያቸን የሚል ዜማ ተለቀቀ። ኦሮሙማ ተረኛ የሳማ ቅጠል ሁኖ ብቅ አለ። ውጤቱ አሁን የምናየው ነው። የተቀየረ ነገር የለም - ባሰ እንጅ።

ዕድሜ ስጠኝ ተብሎ ሰው ወደ አምላኩ የሚጸልየው ወደ ሰዋዊ ህሌና ተመልሶ ንስሃ ለመግባት ነው። ተጸጽቶ መመለስ ትልቅ ነገር ነው። ሃይለማርያም ይህን ለማለት መድፈሩ መልካም ነው። በእድሜ ከእርሱ የበለጡ የዛ ትውልድ ተገዳላዮች ይሁኑ ኦነጎች አድስ አበባ የአብይ አህመድ አማካሪ ሁነው ቁጭ ብለው ምንም ወደ በጎ ህሌና ሊመለሱ አልቻሉም። ታዲያ ሃይለማርያም ከእዚህ አኳያ መናገሩ መልካም ነው። በመጨረሻው ሰአት እኮ ንስሃ መግባት እውነትን መናገር እንደ ጽድቅ ይቆጠራል። በክርስቶስ ግራ እና ቀኝ የተሰቀሉት ሁለቱ ወንብደዎች በሞት ሰአት ላይ የግራው ወንበደ ከነትዕቢቱ ሞተ፤ የቀኙ ግን ስለ ክርስቶስ አምላክነት በማመኑ ቀድሞ መንግስተ-ሰማያት ገባ፡፡ ይህ ነገር ፍያታዊ ዘየማን እና ፍያታዊ ዘጸጋ ይመሰላል። በእርግጥ ነው ሃይለማርያም ይህን የመለወጥ አቅም የለውም ግን ትልቅ መልዕክት አለው። ይህ ጦርነት የተረኝነት ጦር=