ድሞጿ ይንቀጠቀጣል፣እንባዋ ይታገላታል፣ደሞ እኔን ለማናገር ትሰቃያለች!
ምሬት ሰውነቴን ሲቆጣጠረው ተሰማኝ፣ለማን በመቆሙ እንዲህ እንደሚደረግ ገባኝ፣ መድሃኒቱ ትከሻን ማበርታት እንደሆነ ተሰማኝ። "በቃ ዝም በይ ማልቀስ በቃን ! ይታሰር ምን ይሆናል" አልኳት። "እሱን አውቃለሁ ልጆቼ ፊት ሲወስዱት የሆኑትን ብታይ እኮ" አለች አሁንም እንዛዋ እያሸነፋት።"የእኛ ልጆች አለቀሱ ብለን እናወራለን የሚገደሉ ህጻናትም አሉ፣አሳዬ የታሰረው ለሚገደሉት ህጻናት ነው ፤ ለእሱ ልጆች አንች አለሽ በርታ በይ ምንም አይሆንም" አልኳት ስሜቷ ያላመመኝ፣ጭንቀቷ ያልከበደኝ መስዬ!!!!!
ሲጠቃለል አሳዬ ደርቤ በአል ቀን ፣ ከልጆቹ ጉያ ተነጥቆ፣ ሚስቱ እያነባች እስር ቤት ተወርውሯል - ወደ ዝነኛው ሜክሲኮ ማጎሪያ¡¡¡
ይሄው ነው!!!!
Meskerem Abera