Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42893
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የብልጽግና ፓርቲ የጋርዮሽ ተላላነት (Collective Illusion)

Post by Horus » 08 Sep 2022, 22:08

የትህነግ ኮሌክቲቭ ኢሉዥን! የጋርዮሽ ተላላነት እና የብልጽኛ ፓርቲ ኮሌክቲቭ ኢሉዥን! የጋርዮሽ ተላላነት ምን ማለት ነው። ድሮ ፕሉራሊስቲክ ኢግኖራንስ ወይም የብዙሃን ድንቁርና ይባል ነበር ። የጋርዮሽ ድንቁርና እና የጋርዮሽ ተላላነት አንድ ነገር አይደሉም። የጋርዮሽ ተላላነት አንድ በግለሰብ ደረጃ ስህተት ነው ብለው የምናምነውን ነገር በጋርዮሽ ትክክል ነው ብለን ስናምን ነው።

ለምሳሌ በግለሰብ ደረጃ አንድ ሰው ካልሰራ እራሱን መመገብ እንደ ማይችል ያምናል ። ነገር በጋርዮሽ ተላላነት እምነት መንግስት ወይም የተባበሩት መንግስታት ህዝቡን ይመግባል ብሎ ማመን ነው።

የጋርዮሽ ተላላነት ግለሰቦች ለራሳቸው እንዳያስቡ፣ ለራሳቸው እንዳያውቁ፣ ለራሳቸው እንዳይወስኑ ትክክለኛ አመለካከታቸውን በመታለልና በዉሸት የሚተኩበት የሶሾያ ሳኮሊጂ ችግር ነው።

ለምሳሌ የህዝባዊ ማዕበል ጦርነት እጅግ ትልቁ ኮሌክቲቭ ኢሉዥን ወይም የጋርዮሽ ተላላነት ነው። በግለሰብ ደረጃ እነዚህ ጂንስ ለብሰው ባዶ እጃችውን ከሰለጠነ ጦር ጋር የሚጋጠሙት የትግሬ ወጣቶች እንደሚገደሉ ያውቃሉ። አንድ ተራ ግለሰብ በዚያ መልክ ጦርነት መሄድ እንደሌለበት ያውቃል።
ነገር ግን በትህነግ ኮሌክቲቭ ኢሉዥን ወይም የጋርዮሽ ተላላነት መሰረት 200 ሺ በባዶ እጅ ተዋጊ መንጋ ጦርነት ያሸንፋል በሚል ዉሸት ወይም መታለል ያምናል ። ይህ ነው የኮሌክቲቭ ኢሉዥን ሶሺያል ሳይኮሎጂ የሚባለው ።

ብልጽግናም በየብሄሩና የማያውቃቸው ህዝብ ውስጥ እየገባ ከህዝቡ ይበልጥ ስለህዝቡ ፍላጎት የማውቅ እኔ ፓርቲው ነኝ እያለ ማታለልና ዉሸት እንደ ሪያሊቲ በህዝብ ላይ እየጫነ ነው። ትህነግና ብልጽግና አንድ የሚያደርጋቸው ይህ የተሸከሙት የጋርዮሽ ተላላነት፤ ኮሌክቲቭ ኢሉዥን ነው ።

አሁን ልብ በሉ በትግሬ ለ50 አመት የገነነው ኮሌክቲቭ ኢሉዥን ዛሬ እጅግ ተዳክሞ በሚንኮታኮትበት ዘመን አዲስ መደመር የሚባል የብልጽግና ፓርቲ የጋርዮሽ ተላላነት ፣ ኮሌክቲቭ ኢሉዥን እየተሰበከ ነው ። ብልጽግና የሚለው ቃል እራሱ ኢሉዥን ነው ። ተፈጥሮና ሳይንስ እንደሚያረጋግጠው የሚሰሩ፣ ሃብትና ንብረት ሌላም እሴት የሚፈጥሩ ግለሰቦች ናቸው ። ፓርቲ ተብለው በቀን 8 ሰዓት የሚሰበሰቡ፣ ቢሮ የሚቀመጡ ፓራሳይት ግለሰቦችን ብልጽግና አምጪዎች የሚለው አፍዝዝ አደንግዝ ማታለያ ዉሸትን ነው የሶሺያል ሳይኮሎጂ ሳይንስ ኮሌክቲቭ ኢሉሽን ብሎ የሚጠራው የጋርዮሽ ተላላነት!

እግዚአብሄር ፣ አላህ ፈጣሪ ጎይታ ከኢህአዴግና ከብልጽግና ኮሌክቲቭ ኢሉዥን ኢትዮጵያን ይጠብቅ !

የኬር አክራሚ! የፍስሃ መስቅል ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይሁን !

Last edited by Horus on 09 Sep 2022, 13:42, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 42893
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የጋርዮሽ ተላላነት (Collective Illusion)

Post by Horus » 09 Sep 2022, 01:43

The problem of all elites in power - group-think aka collective illusions! Groups such as PP party populated by mediocre office seekers is the perfect muddy marsh where collective illusions flourish! Keep your eyes open!!!

Horus
Senior Member+
Posts: 42893
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የጋርዮሽ ተላላነት (Collective Illusion)

Post by Horus » 09 Sep 2022, 13:36

ልብ በሉ፣ ዛሬ የትግሬ የጋርዮሽ ተላላነት (ኮሌክቲቭ ኢሉዥን) እጅግ አስከፊ በሆነ መልኩ ለ50 አመት ህዝቡን አውሮ ለዛሬ ውድቀት ስላበቃቸው ሰው ሁሉ ስለ ትግሬ ኢሉዥን ነው የሚተቸው ። ነገር ግን አይን የራሱን ጉድፍ አያይም ይባላል። ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውንና ውሎ አድሮ ልክ እንደ ትህነግ ግዙፍ ውድቀት የሚሆነውን ከ10 ሚሊዮን በላይ ያልበሰለ የፒፒ አድር ባይ የንኡስ ከበርቴ ግሩፒ እየሰበከ ያለውን አዲስ ጥንቆላ፣ አዲስ ኮሌክቲቭ ኢሉዥንን ማስተዋል ያልቻለ አበሻ ኋላ ማዘኑ አይቀርም።

ብልጽግና በማን እና በየትኛው ጎዳናና ፋና እየተጓዘ ነው? ልጓዝ በኢአዴግ ጎዳና በወደቀው ትህነግ ፋና! ያ ነው በአቢይ ፒፒ የሚጠፈጠፈው ናዕት የጋርዮሽ ተላላነት ኮሌክቲቭ ኢሉዥን!

Wedi
Member+
Posts: 8649
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: የብልጽግና ፓርቲ የጋርዮሽ ተላላነት (Collective Illusion)

Post by Wedi » 09 Sep 2022, 14:20

PP being the brain child of EPRDF, the problems that PP and EPRDF possess are the same.

IIn both PP and EPRDF, there is no accountabilty as long as you are cadre or loyal puppet, you can lot public resources and public money as much as you can. infact most loters are good friends of PP/EPRDF.

You become an enmy of PP or EPRDF only if your political ideology is different from them. In that case they will jail you the next day for no reason.

Post Reply