Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

“የሰላም ጥሪ” ለማቅረብ የተሰባሰቡ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋዜጣዊ መግለጫ ከመስጠት ተከለከሉ - Ethiopia Insider

Post by sarcasm » 08 Sep 2022, 19:59

“የሰላም ጥሪ” ለማቅረብ የተሰባሰቡ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋዜጣዊ መግለጫ ከመስጠት ተከለከሉ Ethiopia Insider

የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ “አስቸኳይ የሰላም ጥሪ” ሊያቀርቡ የነበሩ የሀገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች፤ ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳይሰጡ ተከለከሉ። ድርጅቶቹ ዛሬ ማክሰኞ ጷጉሜ 1፤ 2014 ጋዜጣዊ መግለጫውን ሊሰጡ የነበረው በአዲስ አበባው ኢንተርሌግዠሪ ሆቴል ነበር።

ጋዜጣዊ መግለጫ ሊሰጡ የነበሩት ድርጅቶች የተሰባሰቡት፤ የሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ስላሳሰባቸው መሆኑን ለመገናኛ ብዙሃን አስቀድመው በላኩት ደብዳቤ ገልጸው ነበር። ጋዜጣዊ መግለጫው ሊሰጥ በታቀደበት ሆቴል የአዲስ አበባ ፖሊስ የደንብ ልብስ እና ሲቪል የለበሱ የጸጥታ አካላት ነበሩ።

ሲቪል ከለበሱ የጸጥታ አካላት መካከል “ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ነው የመጣሁት” ያለ አንድ ግለሰብ፤ መግለጫውን ለመዘገብ በስፍራው የተገኙ ጋዜጠኞችን ለማናገር ሙከራ ሲያደርግ ተስተውሏል። ይኸው ግለሰብ ጋዜጠኞችን ለምን በሆቴሉ እንደተገኙ እና ከየትኛው መገናኛ ብዙሃን እንደመጡ ሲጠይቅ ነበር።

ግለሰቡ ጋዜጠኞችን ካነጋገራቸው በኋላ የሆቴሉ ሰራተኞች “የአሁኑ ስብሰባ አይኖርም” በማለት ለጋዜጠኞቹ አስታውቀዋል። መግለጫውን ሊሰጡ የነበሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ተወካዮች በተመሳሳይ ጋዜጣዊ መግለጫውን እንዳያደርጉ መከልከላቸውን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ሆኖም ጋዜጣዊ መግለጫውን “ማን እንደከለከለው ሊነግሩን አልፈለጉም” ሲሉ የክልከላውን ውሳኔ ያስተላለፈው አካል ማን እንደሆነ አለማወቃቸውን አስረድተዋል። (በሃሚድ አወል – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)


https://ethiopiainsider.com/2022/8002/


በኢትዮጵያ ያሉ ግጭቶች ቆመው የእርቅ ንግግር እንዲጀመር 35 ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጠየቁ

በሃሚድ አወል

ሰላሳ አምስት ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሰሜን ኢትዮጵያ እና በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች ያሉ ግጭቶች “በአስቸኳይ ቆመው ሐቀኛ እና ሰላማዊ” የእርቅ ንግግሮች እንዲጀመሩ ጥሪ አቀረቡ። ድርጅቶቹ በትግራይ እና ጦርነት ባለባቸው አካባቢዎች የተቋረጡ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ አገልግሎቶች “በአፋጣኝ እንዲጀመሩ” ጠይቀዋል።

የሲቪል ማህበራት ድርጅቶቹ ይህን ጥሪ ያቀረቡት በ“በይነ መረብ” አማካኝነት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። የሰላም ጥሪውን ያቀረቡት በሰብዓዊ መብቶች መከበር፣ በዴሞክራሲያዊ ስርዓት መዘርጋትና በግጭት አፈታት እና ሰላም ግንባታ ስራ ላይ የተሰማሩ ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ናቸው።

ድርጅቶቹ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ ያዘጋጁትን መግለጫ ጋዜጠኞች በተገኙበት ዛሬ ረፋድ ላይ ሊያቀርቡ የነበረው በአዲስ አበባው ኢንተርሌግዠሪ ሆቴል ነበር። ሆኖም ጋዜጣዊ መግለጫው እንዳይደረግ “ተከልክሏል” በመባሉ በተባለው ሰዓት ሳይካሄድ ቀርቷል። ሁነቱ የተስተጓጉለው “ማንነታቸውን ባልገለጹ የመንግስት አካል ነን ባሉ ግለሰቦች” መሆኑን የጋዜጣዊ መግለጫው አዘጋጆች ዛሬ ከሰዓት በኋላ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

Continue reading https://ethiopiainsider.com/2022/8007/

Sam Ebalalehu
Member
Posts: 3639
Joined: 23 Jun 2018, 21:29

Re: “የሰላም ጥሪ” ለማቅረብ የተሰባሰቡ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋዜጣዊ መግለጫ ከመስጠት ተከለከሉ - Ethiopia Insider

Post by Sam Ebalalehu » 08 Sep 2022, 20:14

የኢትዮጵያ መንግሥት ሰላም መምጣቱን ከመቀሌ በቀናት ውሰጥ ሊነግረን ነው የሚለው ግንዛቤየ ቅዠት ነው ነው የምትይው Eden. አብረን ለመጠበቅ ትእግስቱ ይኑረን። እነዚሕ ሰላም ፈላጊዎች ሰላም የሚጠይቁበት ሰአት አይገርምሽም። እኔን ግን አይገርመኝም። የአጎቶችሽን እያንዳንዱን እርምጃ በቅጡ እረዳለሁ።

Post Reply