Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"በቆቦ የአንድ የማውቃቸው ቤተሰብ ልጆች እናት፣ ከአራቱ ልጆቿ ከሁለቱ ጋር በቤትዋ እያለች በድሮን ጥቃት ህይወቷ አልፏል፡፡" ግርማ ካሳ

Post by sarcasm » 08 Sep 2022, 18:32

በግርማ ካሳ

እጅግ በጣም ያዘንኩበት ዜና፣ የድሮን ጥቃት በቆቦ #ግርማካሳ

በቆቦ ከተማ ሁለት ቤተሰቦች አሉ፡፡ በግል የማውቃቸው፡፡ አባቶቻቸው በህልውናው ትግል ለአገርና ለሕዝብ ውድ ሕይወታቸውን አሳልፈው የሰጡ ናቸው፡፡ ከአንድ አመት በፊት በተደረገው ጦርነት፡፡

ወያኔ በቅርቡ ቆቦን ከመያዟ በፊት በስልክ ደህንነታቸውን ጠይቀውን ነግረውን ነበር፡፡ ወያኔ ቆቦን ስትይዝ፣ ግንኙነት እንዳይኖር የአብይ መንግስት ኔትዎርኩን በመዝጋቱ ዳግም ሲደወልላቸው ሊገኙ አልቻሉም፡፡

ዛሬ እጅግ በጣም አሳዛኝ ዜና ሰማሁ፡፡ የአንዱ ቤተሰብ ልጆች እናት፣ ከአራቱ ልጆቿ ከሁለቱ ጋር በቤትዋ እያለች በድሮን ጥቃት ህይወቷ አልፏል፡፡ ባሏ ከወያኔ ጋር ሲዋደቅ ሕይወቱ አለፈ፡፡ እርሷ ደግሞ በመከላከያ እጅ ሕይወቷ አለፈ፡፡

የአብይ መንግስት ፣ "ከቆቦ ለቅቄ የወጣሁት፣ የቆቦ ሕዝብ አደጋ ላይ እንዳይወድቅ ነው፣ በከተማ ውስጥ ጦርነት እንዳይደረግ ነው" ገሚል ነበር፡፡ ታዲያ ድሮን ቆቦ ከተማ መካከል መተኮስ ምንድን ነው የሚባለው ?????? ይሄ እጅግ በጣም አሳዛኝ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ የአብይ መንግስት እነ ፑቲን ማሪዮፖላን እናደረጉት ቆቦን እንዳያወድሙ እፈራለሁ፡፡ እነርሱ አውድመው፣ ወያኔ ነው ብለውም ወንጀላቸውን ሊደብቁም ይችላሉ፡፡
Please wait, video is loading...