Page 1 of 1

ቅኔ ድሮ እና ዘንድሮ፤ ያለኳስ ጫወታ

Posted: 07 Sep 2022, 17:18
by Naga Tuma
የድሮ ሰዉ የሰዉ ቅኔ ይጠቅስልሃል።

ኣንዳንዱ የዘንድሮ ሰዉ ቅኔ ጥቀስ ሲባል እኔዉ እቀኝልሃለሁ ይላል። በጀ። ይለምልም። እንዴት ባህል እንደሆነ ኣላዉቅም። መክማክሳም ተመሳሳይ ይመስለኛል።

የድሮ ቅኔ መቼ እንደተቀኘ በሰፊዉ የተመዘገበ ኣይመስለኝም። አለቃ ገብረሃና ብሻን እንጠጣለን፣ ብሻን እንበላለን ብሎ ነበር ባይ እንጂ የቀጠነዉ ወጥ ማን ቤት እና መቼ እንደነበረ የተመዘገበ ኣይመስለኝም።

የዘንድሮ ቀኚዎች ቅኔዎቻችሁን ለመጪዉ ትዉልድ ብትመዘግቡ ምን ይመስላችሁዋል?

ከኣሁን በፊት ሰዉ በቁሙ ከመሞት ለምን ቆሞ ኣይሞትም ብዬ ኣልፌኣለሁ። ኣሁን ኣንድ ቅኔን ለኣንድ ባልደረባዬ ማስረዳት ኣስቸግሮኛል።

ኳስ ሳይይዝ ሜዳ ገብቶ ልጫወት ባይ ባልደረባዬን ቅኔ ማስተማር ኣስቸገረኝ። እስከኣሁን ሰማንያ ስምንት ጊዜ ያህል ያለኳስ ሜዳ ገብቶ ጫወታ የለም እና እንካ ኳስ ብዬዋለሁ። ያጋኛትን ኳስ ወድያዉ ይጦልዛል። በእግሩ ሳይሆን በኣፉ። ከዛ ኣሁንም መጥቶ ተጦለዝኩ ይለኛል። በዚህ ያሳዝናኛል። እንካ ያልኩህ ኳስ እንዴት ሽዉ ይላል ብዬ ኣፍእላፊ እንዳልናገረዉ ሰጋሁ። ጋጠወጥ ብሎ ይሸሸል ብዬ። ምን ይሻላል እያልኩ ኣየዋለሁ። ኳስ ፈልገህ ያዝ፣ እንደኳስ ኣትጦለዝ ብሎት የሚሰማዉ በተገኘ።