ተመድ በሱዳን የስደተኞች መጠለያ ወታደራዊ ምልመላ ይደረግ እንደነበረ መረጃው አለኝ አለ!
የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ኢትዮጵያውያን ተፈናቃዮች በነበሩባቸው የሱዳን የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የግዳጅ የውትድርና ምልመላ ይካሄድ እንደነበረ መረጃው ነበረኝ አለ።የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ተቋም እንዳለው ከወራት በፊት ከስደተኞቹ መካከል አንዳንድ ጊዜ በኃይል ጭምር ተዋጊዎችን ለመመልመል የሚደረጉ ጥረቶች እንደነበሩ “ተአማኒ ሪፖርቶች” ደርሶት እንደነበር ለቢቢሲ ገልጿል።በጥቅምት ወር ማብቂያ 2013 ዓ.ም. ላይ ትግራይ ውስጥ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ድንበር ተሻግረው ወደ ምሥራቅ ሱዳን መግባታቸው ይታወሳል።
የስደተኞቹ ከፍተኛ ኮሚሽን ወታደራዊ ምልመላ መኖሩን እንደተገነዘበ ጉዳዩን በተመለከተ ለሱዳን ማዕከላዊ መንግሥት እና ለአካባቢ ባለሥልጣናት ስጋቱን መግለጹን አመልክቷል።ይህንንም ተከትሎ ሁኔታዎች የተሻሻሉ ይመስሉ እንደነበር የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ተቋም ለቢቢሲ በኢሜይል በሰጠው ምላሽ ገልጿል።ደርጅቱ “ወታደራዊ ምልመላውን ለማካሄድ ከኢትዮጵያ የሚመጡ ሰዎች እንደነበሩ” ከስደተኞች መረዳቱን የገለጸ ቢሆንም፤ የትኛው ወገን ምልመላውን እንዳካሄድ ግን “ማረጋገጥ አልቻልኩም” ብሏል።ድርጅቱ ይህን ይበል እንጂ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት በተደጋጋሚ በሱዳን በስደተኝነት የተመዘገቡ ሰዎች ድንበር ተሻግረው ከትግራይ ኃይሎች ጋር በመወገን ሲዋጉ ነበር በማለት ሲከስ ቆይቷል።
ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ: https://bbc.in/3Bjmm8s
