Page 1 of 1

ኢሳት አዲስ አበባ ሌላው ዋልታ ቲቪ!

Posted: 03 Sep 2022, 13:38
by Horus
ሬድዋን ሁሴን ስለ ዲያስፖራ ያወጣውን ሰሚ አልባ ጥሪ እንደ ወረደ ሲያነብ ኢሳት ልክ ኢቲቪ ሆነብኝ! ዲያስፖራ ያሉት 95% ህዝብ ኦሮማ፣ አማራ፣ ጉራጌና ትግሬ ናቸው ። አቢይ አህመድ እነዚህን ሁሉ ጋር ጥብ ጭሮ እያለ አሁን ስለ ዲያስፖራ ከንቱ ጥሪ አያሳፍርምን?

Re: ኢሳት አዲስ አበባ ሌላው ዋልታ ቲቪ!

Posted: 03 Sep 2022, 14:09
by Abere
ሆረስ፤

እኔ እኮ ይህ ድያስፓራ የተግባር ምክርቤት( Council For Diaspora ) ከዐብይ ትዕዛዝ ተቀብለው ሲመጡ፥ ለምን የእኛን መልዕክት አያስተላልፉም? ባለፈው No more ብለው ሂደው እነ ስብሃት እና ጁሃርን አስፈትተው መጡ። መጀመሪያ ውል ያስፈልጋል (contractual agreement)።

1ኛ) የጎሳ ክልል ይፈርሳል አይፈርስም?
2ኛ) ህገ-ወጥ የሆነው ህገ-መንግስት ይቀየራል አይቀየርም?
3ኛ) ተረኝነት ተቋርጦ፤ በዜግነት ይተካል አይተካም?
4ኛ) በአበው ህግጋት መሰረት መስዋዕት ሁነው አሁን እስር ቤት የተዘጉት ፋኖዎች ይለቀቃሉ አይለቀቁም?

አንድ ሰው የአንድ ድርጅት አክስዮን ላይ መዋዕለ ንዋይ ለማፍሰስ ስለድርጅቱ አትራፊነት እና ስነ-ምግባር፤ የአስራር ልማድ በተመለከተ መሰረታዊ አንኳር መረጃ ይፈልጋል። ስለዚህ በአገር ልዑላዊነት ለሚደረገው የህይወት ይሁን የንዋይ መስዋዕትነት እንድሁ ግልጽ አቋም ያስፈልጋል። እነኝህ ዩቲዩቦች አይናቸውን በጨው አጥበው ደግመው ደጋግመው ስህተት እና ውሸት አይሰለቻቸውም። ዐብይ አህመድ እና ድርጅቱ የወያኔ ክልል ቢያፈራርሱ እና ህገ-መንግስት ቢቀይሩ እኔ የአመት ገቢየን እሰጣለሁ። በእርግጠኝነት ብዙ ኢትዮጵያን ይህን ያደርጋሉ - ያለውም የሌለውም። ኢትዮጵያዊ አገሩን እንደ ሚወድ ስለሚያውቁ ነው የሚጫወቱብን ተረኛ ሁሉ እየመጣ።

Re: ኢሳት አዲስ አበባ ሌላው ዋልታ ቲቪ!

Posted: 03 Sep 2022, 20:22
by Horus
Abere wrote:
03 Sep 2022, 14:09
ሆረስ፤

እኔ እኮ ይህ ድያስፓራ የተግባር ምክርቤት( Council For Diaspora ) ከዐብይ ትዕዛዝ ተቀብለው ሲመጡ፥ ለምን የእኛን መልዕክት አያስተላልፉም? ባለፈው No more ብለው ሂደው እነ ስብሃት እና ጁሃርን አስፈትተው መጡ። መጀመሪያ ውል ያስፈልጋል (contractual agreement)።

1ኛ) የጎሳ ክልል ይፈርሳል አይፈርስም?
2ኛ) ህገ-ወጥ የሆነው ህገ-መንግስት ይቀየራል አይቀየርም?
3ኛ) ተረኝነት ተቋርጦ፤ በዜግነት ይተካል አይተካም?
4ኛ) በአበው ህግጋት መሰረት መስዋዕት ሁነው አሁን እስር ቤት የተዘጉት ፋኖዎች ይለቀቃሉ አይለቀቁም?

አንድ ሰው የአንድ ድርጅት አክስዮን ላይ መዋዕለ ንዋይ ለማፍሰስ ስለድርጅቱ አትራፊነት እና ስነ-ምግባር፤ የአስራር ልማድ በተመለከተ መሰረታዊ አንኳር መረጃ ይፈልጋል። ስለዚህ በአገር ልዑላዊነት ለሚደረገው የህይወት ይሁን የንዋይ መስዋዕትነት እንድሁ ግልጽ አቋም ያስፈልጋል። እነኝህ ዩቲዩቦች አይናቸውን በጨው አጥበው ደግመው ደጋግመው ስህተት እና ውሸት አይሰለቻቸውም። ዐብይ አህመድ እና ድርጅቱ የወያኔ ክልል ቢያፈራርሱ እና ህገ-መንግስት ቢቀይሩ እኔ የአመት ገቢየን እሰጣለሁ። በእርግጠኝነት ብዙ ኢትዮጵያን ይህን ያደርጋሉ - ያለውም የሌለውም። ኢትዮጵያዊ አገሩን እንደ ሚወድ ስለሚያውቁ ነው የሚጫወቱብን ተረኛ ሁሉ እየመጣ።
አበረ፣

ከመደራደሪያ ጥያቄዎች አንዱ የዲያስፖራው ደብል ዜግነት መብት ነው ። አቢይ የሚፈልገው እንዳሻው የሚያልበው ያሜሪካ ላም እንጂ እኛ የኢትዮጵያ ዜጋ ሆነን እኩል መብትና ባለቤትነት እንዲኖረን አይፈልግም። ያ ቆሻሻ ተንኮለኛ መለስ ያረቀቀውን የዲያስፖራ ሕግ ይዞ ነው አቢይ ሊያልበን የሚሻው! አይሆንም።

ካላሙዲን ቀጥሎ ያለው የኢትዮጵያ ዲታ የማሞ ካቻ ልጅ፣ ኢዮብ ማሞ ከዚህ ሁሉ ቢሊዮኖች ዶላር ሃብቱ 5 ሳንቲም ኢትዮጵያ አላስገባም ምክንያቱም የብልጽኛ ሌቦች የዛሬ አመት ገና ላይ እንዴት እንደ ዘረፉን ታስታውሳለህ!!!

አንተ ያነሳሃው ጉዳይ ለብዙ አመታት ውይይት ላይ ያለ ነው ። ችግሩ ዲያስፖራው ባሜሪካም አውሮፓም ፣ ቅርብ ምስራቅም እንደ ዲያስፖራ አንድ ድርጅት ወይም ድምጽ የለውም ። የጎሳ ክፍፍሉ እንደ ምታቀው በውጭ የባሰ ነው ። በግለሰብ ደረጃ ቢዝነስ፣ ቴክኖሎጂ ወይም እውቀት ላማስገባት የሞከሩት በጉቦና በዘር አድልዎ ምርር ብለው ተመልሰውዋል ።

ለዚህ ነው ያ ሬድዋን የሚባል ከብት ካድሬ ምድር ላይ ያለውን ሃቅ እንደ ማያውቅ በሌላ አሰልቺ ጥሪና መግለጫ ሙዳችንን የሚያበላሸው ።

በትክክል ብለሃል ዲያስፖራ ድርጅትና ድምጽ ቢኖረን መንግስት ማስለወጥ የሚችል አቅም አለን ። የጎሳ መንግስት ከልፈረሰ ሙሉ እቀባ ብናደርግ ያቢይ ባጀት በቂጡ ይቀመጥ ነበር ። በአመት በትንሹ ከ5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ነው በሬሚታንስ ብቻ ዲያስፖራ የሚያፈሰው ሃብት ። ይህ ሁሉ በሚሊዮኖች ሕዝብ ኢትዮጵያ ውስጥ ሸምቶ በልቶ ሚያድረው ዲያስፖራ በሚልከው ገንዘብ ነው ። ግን አንዳች የፖለቲካ ድምጽ፣ ኢፍሉወንስ የለውም! እጅግ እጅግ ያሳዝናል!!!

ስለዚህም ነው ዛሬ ላይ መንግስት የኢትዮጵያዊነት ከበሮ ለመደልቅ ቢቃጣውም ቄሱም ዝም! መጽሃፉም ዝም የሆነው!!!! አቢይ አህመድ ትምህርቱን አግኝቷል ። ሆድን በጎመን ቢደልሉት ጉልበት በዳገት ይለግማልና አሁን አቢይ ዳገቱን እራሱ ይውጣው!!!!