Page 1 of 1

PM Abiy explains the benefits of opening up the banking sector for foreign competition now

Posted: 03 Sep 2022, 10:54
by sarcasm
Ethiopia adopts new policy that will open up the banking sector for foreign competition. The policy has been approved by the council of ministers today.


የሚኒስትሮች ምክር ቤት የባንክ ዘርፍን ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ለማድረግ የቀረበው ረቂቅ ፖሊሲ በሥራ ላይ እንዲውል ወሰነ

*************************

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባ የባንክ ዘርፍን ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ለማድረግ በቀረበ ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ተወያይቶ ግብዓቶችን በማከል በሥራ ላይ እንዲውል መወሰኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታወቀ።

የባንክ ዘርፍን ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ማድረግ የዘርፉን አገልግሎቶች በእውቀት እና በቴክኖሎጂ ለመደገፍ፤ የአገራችን ኢኮኖሚ ከዓለም አቀፍ ገበያ ጋር ያለውን ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር፣ የፋይናንስ ዘርፉን ተወዳዳሪነት፣ ውጤታማነት እና ቀልጣፋነት በመጨመር በቂ የፋይናንስ አቅርቦት እንዲኖር እና የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት እንዲሳለጥ፣ የሚፈጠረው የሥራ ዕድል እንዲጎለብት እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ውጤታማነትን እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪትን በማረጋገጥ ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት ለማረጋገጥ የሚያስችል ረቂቅ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል።

ምክር ቤቱም በፖሊሲው ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በሥራ ላይ እንዲውል መወሰኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
Please wait, video is loading...