Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
tarik
Senior Member+
Posts: 37268
Joined: 26 Feb 2016, 13:04

(((ኣዲስ መረጃ))):ታሪክ የማይረሳው ተጋድሎ:-ኣሸባሪ-ህወሓት በራያ ግንባር እስካሁን ባለው መረጃ ከሁለት መቶ ሺህ የማያንስ ኃይል ይዞ መጥቷል!!! WEEY GUUD !!!

Post by tarik » 30 Aug 2022, 13:29

Natnael Mekonnen

ታዳ መች ሰላም ሰጡን

ታሪክ የማይረሳው ተጋድሎ!
ህወሓት ወያኔ በራያ ግንባር እስካሁን ባለው መረጃ ከሁለት መቶ ሺህ የማያንስ ኃይል ይዞ መጥቷል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ የምስራቅ አማራ ፋኖ እና ሚሊሻው የታገለው ከዚህ ኃይል ጋር ነው። ባለፈው ቆቦን፣ ትናንት ወልዲያን ለመያዝ የአሸባሪው ቡድን ብዙ ኃይል አልቆበታል። በህዝብ መአበል የጀመረው ጦርነት ለወገን ጦር ከፍተኛ ግፊት የፈጠረ ቢሆንም በጀግንነት ሲፋለም ከርሟል።
ፌስቡከኛው ሰግቶ የሸሸ ወገናችን ፎቶ ይለጥፋል እንጅ ብዙ የሚነገርለት ጀግናም ሞልቷል። ለሰራዊቱ ደጀን የሆኑ ወጣቶች፣ ምግብ እያበሰሉ የሚያቀርቡ እናቶች፣ ሰብሉን ትቶ ከሰራዊቱ ጎን የተሰለፈው አርሶ አደራችን ታሪክም በደማቅ ታሪክ የሚፃፍ ነው። እነዚህ ጀግኖች ለክብራችን ተዋድቀዋል። ሌላው ህዝባችን እንዳይጎዳ በርካታ ዋጋ ከፍለውልናል።
በአካል፣ በስልክ፣ በፌስቡክ የማውቃቸውን የራያ፣ የወልዲያ አካባቢ ወገኖች ደውዬ አነጋግሬያለሁ። ብርታታቸው የሚገርም ነው። ቤተሰቦቻቸው የተገደሉባቸው፣ የተዘረፉባቸው፣ ቤተሰቦቻቸው ይሙቱ ይኑሩ የማያውቁ ናቸው። ብዙ ነገሮችን እምቅ አድርገው ችለው መንፈሳቸውን ያበረቱ ጀግኖች ናቸው። የቤሰተቦቻቸውን ሕመምና ስጋት በሚገባ ያልተረዳናቸው፣ ነገር ግን በርካታ ፅኑ ወገኖች አሉን። አሉባልታና ወሬ፣ ሰበርና አሳዛኝ ዜና ከሚለጠፈው በላይ የእነዚህ ጀግኖቻችን ፅናት ብዙ ትርጉም ነበረው። ለእኛ ሲሉ በየጥሻው ትህነግ ጋር ተናንቀው መስዋዕትነት የከፈሉ ጀግኖች፣ በአካባቢው ንቅንቅ ሳይል ለሰራዊቱ ደጀን የሆነው በርካታ ሕዝባችን ፅናት ሊያስተምረን፣ ላላወቀው ልናሳውቅ ሲገባ እንቶፈንቶው ሊያጨቃጭቀን አይገባም ነበር።
ጌታቸው ሽፈራው