ENDF‘s attention is required!!! ራያግንባር ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ
Posted: 29 Aug 2022, 09:52
ሕወሓት በራያ ግንባር ጦርነት ከጀመረበት ዕለት ጀምሮ ከፋኖዎች ጋር በምሽግ ውስጥ ነበረኩ ። ጦርነቱ በየደቂቃው ተለዋዋጭ በመሆኑ አንድ የጠራ ምስል እስካገኝ ድረስ ከመፃፍ ታቅቤ ቆይቻለሁ።
ፋኖ ፣ መከላከያ ፣ የአማራ ልዩ ሀይል እና ሚሊሻ ከራማ ኪዳነ ምህረት እስከ ጎብዬ ፣ በላጎ እና ቃሊም ድረስ የሞት ሽረት ውጊያ እያደረገ ነው።
ይሁን እንጅ አሁን በዚህ ሰአት የሕወሓት ታጣቂ ቡድን የተወሰነው ሾልኮ ከጎብዬ በእስከ ደቡብ ምዕራብ በኩል ዱርለበስ በሚባለው አካባቢ የአልውሃን ወንዝ ለመሻገር እየተንደረደረ ነው። ይህ አቅጣጫ በማመጫ ድጎ ኢየሱስ አድርጎ ወደ ወልዲያ የሚያስገባውን ዋሻው ለመዝጋት ነው።
ጥምር ጦሩ ዋሻውን ቀድሞ ቢይዝ ወልዲያን ማዳን ይቻላል የሚል መልዕክት አለኝ።
ባሳለፍነው ዓመትም የሕወሓት ቡድን ይህንኑ መስመር ተከትሎ ወልዲያ መግባቱ የሚታወስ ነው። አማራ ብቻ ሳይሆን መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሕወሓት ሕዝባዊ ሆኖ እንደመጣው ሁሉ ሕዝባዊ ሆኖ ካልተነሳ በስተቀር አንድ ቀን ጧት በራችንን ስንከፍት ደጃፋችን ላይ እናገኛቸዋለን።
ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ
@Fanotv24