3m ·
በህውሃት ተንኳሽነት ከቀናት በፊት በአፋር እና በአማራ ክልል አዋሳኝ ድንበሮች አንድ የተባለው ጦርነት እየተጋጋለ እና እየተፋፋመ ሂዶ ዛሬ ላይ ደርሷል ።
በዚህም አይበገሬው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከአሸባሪው የህውሃት ሃይል የተሰነዘረውን ጥቃት በከፍተኛ ወኔ እየመከተ እና እየተከላከለ ሃገራዊ እና ህዝባዊ ግዴታውን በአግባቡ እየተወጣ ይገኛል።
ታድያ የምስራቅ አማራ ፋኖወች እና ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ከመከላከያ ጎን በመሆን ድጋፍ ለመስጠት በዘመቱበት በራያ ግንባር በራማ በኩል የወገንን ሃይል ለመቁረጥ አስቦ ተሹለክልኮ ወደ ውስጥ ገብቶ የነበረ አንድ ክፍል ጦር የህወሃት ኮማንዶ ቀለበት ውስጥ በማስገባት በጀግናው ህዝባዊ ሃይል አመድ መደረጉን ከግንባር የተገኙ መረጃወች ያስረዳሉ።
ለመሆኑ የውጊያ ታክቲክ ጠበብቶች ነን ባዮች የጁንታው ሰዎች ማታ ማታ በድሃው የትግራይ ምስኪን ወጣት ደም የተጠመቀ ውስኪያቸው ላይ በስላቅ አለማቸውን ሲቀጩ እና ሲንፈላሰሱ አምሽተው ታከቲኩን በወል ለጀሌወቻቸው ሳያሳዩ እና የጥንቃቄ መልክት ሳያስተላለፉ ረስተው ይሆን የሚል የግርምት ጥያቄን አጭሯል።
ታድያ ቀድሞ የኮማንዶው አላማ ተደብቆ ገብቶ ወገንን ከጀርባ መምታት እንደነበረ መረጃ የደረሳቸው የጀግናው መከላከያ ሰራዊት አመራሮች ሁኔታውን በጥንቃቄ ሲከታተሉ ከቆዩ በኋላ ጠላት ወደ ውስጥ አሰልፈው ከጀርባ በቆረጣ አብዛኛውን የኮማንዶ ሃይል መደምሰሳቸው ተገልጿል፤የቀሩትን የፈረጠጡ የጁንታው ታጣቂወች ከነ ነፍሳቸው በቁጥጥር ለማዋል በአካባቢው ሰፊ አሰሳ እየተካሄደ እንደሚገኝም ተሰምቷል ።
ኢትዮጵያን የነካ ፤በእሳት የተጫወተ መሆኑን ለሌሎች የውች እና የሃገር ውስጥ ጠላቶች በተግባር እየታየ በመሆኑ የአሸባሪው የህውሃት ጦር እኔን ያየ ይቀጣ እያለ ይገኛል። See less
