Z Russian Ambassador 2 Ethiopia & Usa Embassy In My Eritrea Both Condemn & Call Terrorist-Tplf Thieves!!! WEEY GUUD !!!
Posted: 25 Aug 2022, 14:38

"ህወሓት የዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘንን መዝረፉ ተቀባይነት የሌለው አሳፋሪ ተግባር ነው"፦ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር
በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ተረክህ፣ ህወሓት መቐለ ከሚገኘውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን 12 የነዳጅ ታንከሮችን ከ570 ሺህ ሊትር ነዳጅ ጋር መዝረፉ ተቀባይነት የሌለው አሳፋሪ ተግባር ነው ሲሉ አወገዙ።
በህወሓት የተዘረፈው ነዳጅ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች በእጅጉ አስፈላጊ እንደሆነ አምባሳደሩ ገልጸዋል።
የተፈጠረው ሁኔታ በተለያዩ ሰው ሠራሽ እና ተፈጥሮአዊ አደጋዎች ችግር ውስጥ የሚገኙ ንፁሃን የትግራይ ተወላጆችን የበለጠ አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን ነው አምባሳደር ኤቭጌኒ ተረክህ ለኢዜአ የገለጹት።
የበለጠ መጥፎው ነገር ደግሞ እነዚሁ ዘረፋውን የፈፀሙ ሰዎች በትግራይ ሕዝብ ላይ ችግር እና መከራ ተፈጠረ ብለው መጮኻቸው አይቀሬ መሆኑ ነው ብለዋል።
ነገር ግን ተወቃሽ የሚያደርጉት ማንን ይሆናል? ሲሉ ጠይቀዋል።
የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በጉዳዩ ላይ የሰጠው ግብረ-መልስን እንዴት እንደገመገሙ ተጠይቀው፣ ማንም ኅሊና ያለው ሰው ይህን መሰል እኩይ ተግባር ይደግፋል ብለው እንደማያምኑ ገልጸዋል።
በእርግጥ አንዳንዶች ድርጊቱን ከመኮንን እንደሚቆጠቡ እረዳለሁ ያሉት አምባሳደሩ፣ ነገር ግን ሁልጊዜ እውነት አሸናፊ እንደምትሆን እና ሁሉም ሰው የተፈጠረውን እና እየተፈጠረ ያለውን ጉዳይ እንደሚገነዘብ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
=============================================================================================================
