Page 1 of 1

ብርንዶ ትመትሪ በበሰር እንጨ! የጉራጌ እንሺታተ

Posted: 05 Aug 2022, 02:24
by Horus
እነዚህ በውጭ አገር የሚኖሩ ሴቶች ከሞላ ጎደል ባህላቸውም ቋንቋቸውም ድንቅ ነው ። ነገሩን በጣም ትክክል እናድርገው ካልን መታረም ያለበት ...

ክትፎ አማርኛ ሲሆን ጉራጌ ብርንዶ ይለዋል! ብርንዶም ኧዎዱ ስልስ ነብስንዲ ይባላል! ቀይ ክትፎ ብርንዶ ነው ።

በሰር ስጋ ማለት ሲሆን በአረብኛም በሰር ነው ። መክተፍ ወምትር ይባል ። በሰር ይመትሩት ፣ ስጋ ይከትፋል! ማዘጋጀት አማርኛ ነው ። ዋክላልት፣ ዋባልት፣ ወሸክት ፣ ማዘጋጀት፣ ማሳመር፣ መስራ ነው።

ትልቁ ነገር ግን ህዝባችን ባለበት መሰብሰቡ አንድ መሆኑ ነው ። የቀረው ሁሉ ቀጥሎ የሚመጣ ነው ። መሰብሰብ ሃይል ነው!


Re: ብርንዶ ትመትሪ በበሰር እንጨ! የጉራጌ እንሺታተ

Posted: 05 Aug 2022, 02:59
by Horus
እንሾሽላ! የጉራጌ ቤተሰብ ሴት ልጁን ከሰርጓ 3 ቀን ቀደም ብሎ በክብር የሚሰናበትበት እጅግ ስሜታዊና ፍቅር የተሞላበት የደህና ሁኚ በአል!