Page 1 of 1
Unprecedented flood in Ethiopia
Posted: 02 Aug 2022, 09:32
by Abaymado
Re: Unprecedented flood in Ethiopia
Posted: 02 Aug 2022, 13:19
by Ethoash
Abaymado
ምነው አባጎዶ
ጥራት ያለው ቪድዬ መለጠፍ ጀመርሽ ፣ የነጩ አበሻ ሲገርመኝ ደግሞ ይህ ፣ ሆረር እንዳያይህ አባይ ሞልቶ ስለፈስ ሰ ነው ይልሀል። አንድ ወረኛ አባይ ሶስተኛ ዙር ሞልቶ በግንቡ በላይ ፈስ ስ ብሎት እውነት መስሎት እዚህ ለጥፎ ነበር ።
በተቀረ ይህ ጎርፍን ዝም ብለን በቀላሉ ማየት የለብንም ፣ ጎርፍ የሚመጣው በብዙ ጉዳይ ነው አንደኛ ተራሮች ላይ ዛፎች በመቆረጣቸውና ባዶ ከመሆናቸው ዝናብ ሲመጣ ፍጥነት በማግኘት ወደ መሬት ለመስረግ ግዜ ስለማያገኝ በሙሉ ውሃው ወድ ታች ይንደረደርና ጎርፍ ይፈጥራል። ሌላው ደግሞ የጎርፍ ቱቦዎች በቆሻሻ ስለተደፈኑ፣ የጎርፍ ቱቦዎች በበቂ አለመኖራቸው የመሳስሉት ምክን ያቶች ሊነሱ ይችላሉ ውናው ግን ተራሮቻችንን በዛፍ እና በሳር መሽፈን አለብን ጎርፍን ለመቀነስ ፣ ሌላው ደግሞ ወንዝ የሚያልፉበትን ጎድጎዶች ውሃውን ፍጥነት ለመቀነስ የድንጋይ ካብ በማረግ ግድብ መስራት አለብን የውንዙ ጎድጎድ ውስጥ ስለዚህ ውሃው ፍጥነቱን ይቀንሳል፣
ያለ በለዚያ አንዴ ውሃ ቤት ውስጥ ወይ መኪና ውስጥ ከገባ ሞልድ ያድጋል ሞልድ ደግሞ ለማስለቀቅ በጣም አስቸጋሪ ነገር ነው፣ መኪናውን ወይም ቤት ህን መጣል አለብህ በሙሉ ለማፃዳት ስለዚህ መጀመሪያ መጠንቀቅ ነው። ባለመኪናዎችና ባለሀብታሞች ትንሽ ገንዘብ ከፍለው ከተማውን ማፅዳት አለባቸው ፣ ቱቦዎች በቆሻሻ እንዳይዘጉ ፣
ሌላው ደግሞ የኤሌትሪክና የባዬ ጋዝ ምድጃ በብዛት ማስተዋወቅ አለብን። እንጨት መቁረጥ እንድናቆም። እንደውም የእንጀራ መጋገሪያ መግዢያ ከሌለን የኤሌትሪክ ባለስልጣን በብድር ምድጃ እንዲገዛልን ያስፈልጋል ለምን ቢባል። አንደኛ ባህር ዛፍ ካልተቆረጠ ግድባችን ውሃ ያገኛል፣ ይህ ማለት ብዙ ኤሌትሪክ እናመርታለን ለመሽጥ፣ ይህ ማለት በተዘዋዋሪው የኤሌትሪክ ባለስልጣን ይጠቀማል። ሁለተኛ የእንጀራ ምጣድ ካለን የምጣዱ ኤሌትሪክ ስለምንክፍል እንደገና የኤሌትሪክ ባለስልጣን ተጠቃሚ ይሆናል ማለት ነው።