Page 1 of 1

Jaffore (ጀፎረ) The Genius of Gurage Rural Planning Culture

Posted: 01 Aug 2022, 23:59
by Horus
ጀፎረ የሚለው ቃል እጅግ ጥንታዊ የሴም ቃል ሲሆን በሁሉም የጉራጌ ዲያሌክት ውስጥ ያለ ቃል ነው ። በሰባት ቤት ጀፎረ (ጅፈር) ሲባል በክስታኔ ግፈር ገፎረ ይባላል። ቃሉ በሃረሬም ጋፋር ነው ። በአረብኛ ጋፋር (አል ጋፋር) ይባላል ። ትርጉሙ መተው፣ የተተወ ማለት ነው ። በቅዱስ ቁራን ውስጥ አል ጋህፋር ማለት ይቅር ባዩ ፈጣሪ ማለት ነው። በጉራጌ የመሬት ስሪትና የመንደር ፕላን ካልቸር ጀፎረ ማለት ለጋራ ጥቅም የተተወ መሬት ሲሆን ለመንገድ፣ ለሜዳ፣ ለግጦሽ፣ ለመጫወቻ የሚውል ማንም በግሉ የማይደፍረው መንገድና መሬት ። በኢትዮጵያ ጀፎረን የመሰለ የገጠር ፕላን ባህል ያለበት ክልል የለም ። ዛሬ የጉራጌ ከተሞች ሁሉ በጀፎረ ቅየሳ መሰረት ነው ሰፋፊ መንገድ ያላቸው ትናንሽ ከተሞች የሚያድጉት። ጀፎረ ዙሪያ የሚሰሩ የገጠር ቤቶች ሁሉ ልክ እንደ ከተማ ቤቶች በተርታ የሚሰሩት በጀፎረ መንገድ ቅየሳ ሳቢያ ነው ።


Re: Jaffore (ጀፎረ) The Genius of Gurage Rural Planning Culture

Posted: 02 Aug 2022, 01:09
by Horus
እዚህ ቪዲዮ ውስጥ የምታዩት በተርታ ቤቶች መሃል ያለው መንገድና ባዶ ቦታ ነው ጀፎረ የሚባለው ከግቤው ውጭ ማለት ነው