Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42903
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ሰደህ ማሳደድ ካማረህ ዶሮህን በቆቅ ለውጣት! እጸ ደራርቱ የኦሮሙማ በሽታ መድሃኒት!

Post by Horus » 28 Jul 2022, 13:17

በጸረ ኢትዮጵያዊነት በሽታ የተለከፉ፣ በጸረ ኢትዮጵያ አረቄ የሰከሩ ጂሎች ላለፈው 50 አመት ኢትዮጵያ ምትባል አገር ካልፈረሰች፣ ካልሞተች፣ ካልደደቀች እያሉ ሲሞቱ፣ ሲዋጉ፣ ሲሰደዱ፣ ሰንደቋን ሲረግጡ፣ ሲያቃጥሉ የነበሩ ሁሉ ዛሬ ኢትዮጵያዊነትን መልሶ ለማግኘትና ለመሆን ሌት ተቀን ሲለፉ ሲባክኑ እንደ ማየት አስገራሚ ነገር የለም ። አበሻ እንደሚለው እዩኝ እዩኝ ያለ ደብቁኝ ደብቁኝ ይላል! ጸረ ኢትዮጵያዊ የዘመኑ ጂል እንጂ ኢትዮጵያ የትም አትሄድም።

ስለሆነም ብልጽግና የምትባሉ የአቢይ አህመድ ጂሎች የውነተኛዋ ኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ መልሱልን! ሕዝቧን መከፋፈልና ማጋደል አቁሙ! ታሪክ ሺ ግዜ ያረጋግጣል! ብልጽግና ይፈርሳል፣ ይበተናል እንጂ ኢትዮጵያ የትም አትሄድም! ትግሬ ሄደ፣ ኦሮሞ መጣ፤ ተረኛ ሄደ ተረኛ መጣ ነው! ስልቻ ቀልቀሎ!

አቢይ አህመድ የዛሬ 4 አመት ተነግሮት ነበር! የትግሬ ተገንጣዮች የጠፈጠፉት ናዕት ቂጣ እንኳን ለዕራት ለቁርስም አይበቃም! ወደ ኢትዮጵያዊነት ተመለስ ተብሎ ነበር። አሻፈረኝ ብሎ ለ4 አመት በኢህአደጋዊ የጎሳ ጥንቆላ ግዜና ጉልበቱን አባክኖ ዛሬ ያለው አሳዛኝ ምዕራፍ ላይ አርፏል።

ብርሌ ከነቃ አይሆንም እቃ! የአቢይና የብልጽግና አስተዳደር አሁን 'የተመታ አስተዳድር' ሆኖዋል! ፈረንጆች እንደ ሚሉት 'It is all an up hill battle'!