Page 1 of 1
"ኢትዮዽያ ታመስግን" ... ታሪካዊ ቀልድ!
Posted: 27 Jul 2022, 09:28
by Assegid S.
ኢትዮዽያን የምታመሰግነው፦ በጎሳና በሀይማኖት ምርጫ በከፍተኛ ቢሮ ተደላድላ የተቀመጠችው፣ ያረገዘችውን ፅንስ በውዳጅ ዘመድ ብቻ ሳይሆን በፌደራል ልዩ ሀይል ጥበቃ ጭምር ተከባ፣ ቢያሻት ኣውሮፓ ቢያሻት አሜሪካ ተጉዛ በስፔሻሊስት ሀኪሞች ዕርዳታ የምትገላገለው ወይዘሮ አዳነች አበቤና ወይዘሮ ሰላማዊት ካሳ እንጂ፥ የዘረኛ ስለት ፅንሱዋን ያፈሰሰው፣ የ 6 ወር ጨቅላ ህፃኗን አንገት በጥሶ የጣለው፣ "
ኢትዮጵያዊ ነኝ" ማለትዋ ነውር ሆኖ በግሬደር አፈር የለበሰችው አማራዋ እናትና ልጅ ወዳጅ ዘመዶችና ሩህሩህ አሳቢዎች አይደሉም።
በእርግጥ የሚበላው አጥቶ ከርሱ ያልጎደለ፦ ስልብና ገባር ኣማራ ማመስገን አይደለም በንፁሃን ደምና አስክሬን ላይ እንዲህ ሊውረገረግ ይችላል። በዚህ ፌዝ ላይ ብስጭቴን አስታግሼ በሰፊው እመለስበታለሁ። እውነት ነው ገና ጥቂት ቀን አለ ... የዛሬ ዳንኪረኞችና ባለስልጣኖች የእጃቸውን ብቻ ሳይሆን የእግራቸውንም ጭምር የሚያገኙበት፣ አንድ በኣንድ የሚንጠባጠቡበት ጊዜ ሩቅ አይደለም። ያኔ ኣማራ
ኢትዮጵያንም ባይሆን ፈጣሪውን ያመሰግናል።
Re: "ኢትዮዽያ ታመስግን" ... ታሪካዊ ቀልድ!
Posted: 27 Jul 2022, 17:26
by Ethoash
Assegid S.
አንተ ጥንብ ሽማግሌ እነ አዳነች አበቤና ወይዘሮ ሰላማዊት ካሳ አገር አልከዱም እንዳንተ ፣ ያንተ ሚስት ምነው አሜሪካ አገር ውስጥ ቤቱዋ ነው ወይ የወለደችው ፣ ለምን ድህነትን ለስላማዊት ትመኛለች እሱዋ በሃያ እና በስላሳ አመት ውስጥ ያለች ወጣት አገር ገንቢ ናት አንተ ደግሞ የስባ አመት ሽማግሌ ነህ ምን አርገሀል ለአገርህ፣ እስቲ እራስ ህን ጠይቅ አገርህን ከድተህ ለአሜሪካኖች ታክሲ ከመንዳት በስተቀር ምን ለአገርህ ጥቅም አርገሀል። የሚያረጉትን ከመሳደብ በስተቀር፣ ምን አርጊ ነው ይምትላት እንዳንተ እኮ ኮብልላ ሪቪጂ ሆና ልጁዋን መገላገል ትችላለች አሜሪካ ስለዚህ ምን ቁም ነገር አለው ፣ አሜሪካ መገላገል ደግሞም አሜሪካ መገላገል ከፈለገች የኢትዬዽያ መንግስት ነው የሚከፍልላት አንተ ምን ያገባሀል ። አሜሪካ አገር ፋብሪካ ውስጥ ብት ስራ ባንክ ቤት ውስጥ ብት ስራ እንደተማሩት ያው ፋብሪካው ወይም ባንክ ህ ኢንሹራንስ ስላለው ኢንሹራንሱ ይከፍልልህ ነበር ግን አታውቅም ታክሲ ስለምትነዳ፣ እነአበቤ እና ስላማዊት ተምረው ነው ድረጃቸውን የያዙት ቆንጅናዋ ብቻ ይበቃት ነበር ግን በተማረችበት አገሩዋን እያገለገለች ነው።
ይህ ኬክ በላች ጫዋት በሐይሌ ስላሴ ግዜ ኬካቸው ከፈረንሳይ መጣ ብለን ነበር አገር የገለበጥነው ። እንዴት ኬክ ከፈረንሳይ ሳይበላሽ አዲስ አበባ ይደርሳል አትጠይቀኝ ፣ ሁለተኛ ንጉስ ኬክ በላ የተሻለ ጮማ ቆረጠ ብለን አገር አንገለብጥም ታድያ ጮማ ላይቆርጥ ነው ወይ ንጉስ እና ሚኒስተርነት ደረጃ ደርሶ ለአንድ ሆዳቸው ጮማ ቀርቶባቸው ሽሮ ብቻ ቢበሉ ያተረፍነው ገንዘብ ከነሱ ሆድ አገሪቱን ይገነባል ውይ ፣ ቡዳነት ካልሆነ ብስተቀር የምን መቀላውጭ ነው።
ኦባማም እኮ ንጉስ በነበረበት ስዓት ዘንጦ ነበር የሚኖረው አሁንም እስከሚሞት ድረስ ልጆቹና እሱ ቢሊዬን ዶላር ውጪ ሆኖለት ነው በጥበቃ የሚኖረው ። ስለዚህ ተራ ስው አይደለም የአገር መሪ ነው ልዩነቱ ይግባህ ከአንተ ጋራ አታወዳድረው። ይህቺ ልጆ እንድትሞትብን አንፈልግም ጨረቃ ላይ እክምና ቢኖር ኖሮ ልክን አሳክመን ማትረፍ አለብን ልክ እንደንብ ንግስቲቱዋን እንደሚጠብቁ እኛ ሁላችን ዘብ እንቆማለን ለመሪዎቻችን፣ አንድ ቀን እኮ ያለመሪ መቆየት አንችልም ለምን ሊቢያን ፣ ሱማሌንና ሲሪያን አታይም ቢሊዬን ዶላር ይከፍላሉ መሪያቸውን ለማግኘት ካሉበት ጣጣ ደህና ስንብት ከገባህ ይግባህ እንግዲህ
look the power of ወይዘሮ ሰላማዊት ካሳ
Re: "ኢትዮዽያ ታመስግን" ... ታሪካዊ ቀልድ!
Posted: 28 Jul 2022, 14:59
by Assegid S.
በዚህ ታሪካዊ ቀልድ ዙሪያ ... የአቶ ዳንኤል ክብረትን ነገር ስታዘብ ከዓመታት በፊት ያየሁት የአቶ ክበበው ገዳ ቀልድ ትዝ አለኝ። የኢትዮዽያ ህዝብ ለ"
አሙቁልኝ" ተፈልጓል።
ነገሩን እንዲህ ተመልከቱት ... አቶ ዳንኤል ክብረት "
አሙቁልኝ" ፈልጎ ግራ ወደተጋባው የኢትዮዽያ ህዝብ (ወደ ክበበው ገዳ) ዘንድ መጥቷል ... ። አቧራውም ... "
ካጣነው ይልቅ ያገኘነው በዝቷል" የተባለው በረከት ነው፥ ሰማይ የደረሰው ... ሙሽሪትን ከሙሽራው የለያየው። እናም የኢትዮዽያ ህዝብ ይጠይቃል ..." አቧራው ግን ከእኛ ነው ወይንስ ከእርሶ? አቶ ዳንኤል ክብረት?"