WHAT the announcer didn't pickup is the Gudaf tsegay and Letesenbet Gidey Mistake start way back.......ሁለቱ ፊት ለፊት ሲሮጡ ሲደክማቸው እየተቀያየሩ ማንም አልደገፋቸውም ነበር ሁሉም ከነሱ ስር ተደብቆ ይሮጡ ነበር ። በተለይ ሲፋን መጨረሻ ነበር የምትሮጠው ስለዚህ የኛዎቹ ከደከሙ በኋላ ሲፋን ወጥታ ትልቅ ወድ ደር አካይዳብናለች ። ከዚህ በፊት ከምሩፅ ጀምሮ እስከሐይሌ ድረስ በፍፁም ፊት ለፊት ሮጠው አያውቁም ነበር ። አሁን ግዜ እነገንዘቤም ፣ እነአልማዝም የተሽወዱት ፊት ለፊት በመሮጥ ነው።
ይህ ፊት ለፊት መሮጡ ብቻ ሳይሆን ሩጫው ቀዝቃዛ ከሆነ ፍጥነት ከሌለው ። በመጨረሻ የሚያሽንፈው በጣም ፈጣኑ ሩዋጭ ነው ። ስለዚህ እንደለተስንበት ያላቸው አማራጭ ሩጫውን ማፍጠን ነው። ጥለውም መሄድ ያዋጣቸዋል እንጂ ሩጫውን ካቀዘቀዙት ፈጣን ሩዋጮች ያሽንፋሉ ማለት ነው። ይህንን የግል ችሎታ ማወቅ ያስፈልጋል ይህኑ ነበር ጋዜጠኛው ደጋግሞ ደጋግሞ ሲናገር የነበርው እንዴት የኛ አስልጣኝ ይህንን አላስተማራቸውም በተለይ ለተስንበት ትንሽ ደፈር ማለት አለባት ሁለተኛ እራሱዋን ተማምና ብቻዋን እንደሚሮጥ ስው መሮጥ አለባት ወደ ዋላ ሳታይና ይሉኝታ ተስምቶዋት ምንም ለሩዋጮቹ ቦታ ስት ስጥ ። እንዴ የውስጥን መስመር ከያዙ እንዴት ላለማስለቀቅ መሮጥ እንዳለባቸው መለማመድ አለባቸው ከዋላ ያለው ከፈለገ ለተስንበትን ዞሮ ይለፍ ። አሁን እኮ ስፋንን ከፊቱዋ ካለች ስፋንን ለማለፍ እሱዋን ዞሮ ማለፍ አለባት ማለት ነው። ግን መጀመሪያውንም ቦታዋን ባትለቅ ይህ ሁሉ ባኖረ ነበር እንዳታልፋት በርትታ ብትሮጥ ነበር ። እንግዲህ የማወራው ሁሉም ለነብሱ በሚሮጥበት በመጨረሻው ስዓት ላይ ነው ይህን እያልኩ ያለሁት እንጂ አስር ዙር ሲቀረው አይደለም
ስለዚህ ሩጫው በቀዘቀዝ ቁጥር እንደለተ ያሉት ሩዎጮች አፈትልከው በርቅት መሮጥ አለባቸው አራትና ሶስት ዙር ሲቀረው አለበለዚያ እስከመጨረሻው ከጠበቀች መሽነፍ ይመጣል።
የወንዶችን አምስት ሺህ አይቼው ነበር ነጩ በእውነት አሽንፎዋል ሁለቱ ኢትዬዽያኖች ከዋላ ሲከተሉ ሩጫውን የረሱት ይመስል ነበር በግዜ ነበር ወደ ፊት መቀላቀል የነበረባቸው ሳይቀላቀሉ ቅሩ ተሽንፉ ምንም ምክን ያት ማብዛት የለባቸውም ። እንኩዋንም ተሽነፉ ለምን ቢባል በሚቀጥለው ዙር ምድረ ነጭ ይህንን ነጭ ለማየት ሲመጣ የዛን ግዜ በጥሩ ብር ያሽንፉታል