Page 1 of 1

የኬር ኢኮሎጂ ካልቸር! ቅሙጬ ሕዝብ፣ ቅዱስ ባህል!

Posted: 25 Jul 2022, 13:05
by Horus


Re: የኬር ኢኮሎጂ ካልቸር! ቅሙጬ ሕዝብ፣ ቅዱስ ባህል!

Posted: 25 Jul 2022, 13:26
by Horus
ይህ የአበሽጌ ቀበሌ ልክ ችግኝ በተተከለ ማግስት ባገር ሴራ ተሰብስቦ ከብቱን ወደ ችግኝ ውስጥ የለቀቀን ሰው በከብት 500 ብር መቀጮ (አፈላማ) ለመቅጣት ወሰኑ ። ሴራ ያለው ሕዝብ ማለት ይህ ነው ። ይህ ነው የጉራጌ ሴራ የሚባለው ። ማንኛውም ነገር መወሰኛና መፈጸሚያ ሴራ አለው ጉራጌ! ሴራ ማለት ስርዓት ማለት ነው። እጸዋት ልክ እንደ እንሰሳት ኬር ይደረግላቸዋል! እንሰሳም እንደ ሰው! ይህ ነው ቅዱስ ኢኮሎጂካል ካልቸር ማለት!

Re: የኬር ኢኮሎጂ ካልቸር! ቅሙጬ ሕዝብ፣ ቅዱስ ባህል!

Posted: 25 Jul 2022, 14:35
by Ethoash


ይህ እንዴት የጥደ ዛፍ እንደሚተከል የሚያሳይ ቪድዬ ነው። እንግዲህ ቅጠሎቹን በሙሉ መልምሎ እንጨቱ ብቻ መቅረት አለበት ለምን ቢባል ብዙ ውሃ ይፈልጋል ቅጠሎቹ ካሉ ፣ ለምን ቅጠሎቹ ብዙ ውሃ ስለሚያተኑ ብዙ ውሃ ግንዱ ይፈልጋል ማለት ነው። ግን ግንዱ ብቻ ከሆነ ብዙ ግዜውን እራሱን ለመደገፍና ለማደግ ስሮቹንም በደንብ ለማንስራራት ይጠቀማል ማለት ነው ሽክም ሲቀልለት ። ደግሞ አካፋውን ተመልከቱ እንዴት ቀላል እንደሆን በቀን ሺህ ችግኞች መትከል ይቻላል ማለት ነው። ለዚህ ነው አንድ ስወ ብቻ ምርታማ የሚሆነው ደግሞም የተተከለው ችግኝ ብዙ ውሃ ካልፈለገ ደግሞ ችግኙ የማደግ እድሉ በጣም ይጭምራል ማለት ነው። ለዚህ ነው ብዙ የተከልናቸው ችግኞች የምይፅድቁልን ከነቀጠላቸው ስለምንተክላቸው ነው።

Re: የኬር ኢኮሎጂ ካልቸር! ቅሙጬ ሕዝብ፣ ቅዱስ ባህል!

Posted: 25 Jul 2022, 22:15
by Horus
Ethoash wrote:
25 Jul 2022, 14:35


ይህ እንዴት የጥደ ዛፍ እንደሚተከል የሚያሳይ ቪድዬ ነው። እንግዲህ ቅጠሎቹን በሙሉ መልምሎ እንጨቱ ብቻ መቅረት አለበት ለምን ቢባል ብዙ ውሃ ይፈልጋል ቅጠሎቹ ካሉ ፣ ለምን ቅጠሎቹ ብዙ ውሃ ስለሚያተኑ ብዙ ውሃ ግንዱ ይፈልጋል ማለት ነው። ግን ግንዱ ብቻ ከሆነ ብዙ ግዜውን እራሱን ለመደገፍና ለማደግ ስሮቹንም በደንብ ለማንስራራት ይጠቀማል ማለት ነው ሽክም ሲቀልለት ። ደግሞ አካፋውን ተመልከቱ እንዴት ቀላል እንደሆን በቀን ሺህ ችግኞች መትከል ይቻላል ማለት ነው። ለዚህ ነው አንድ ስወ ብቻ ምርታማ የሚሆነው ደግሞም የተተከለው ችግኝ ብዙ ውሃ ካልፈለገ ደግሞ ችግኙ የማደግ እድሉ በጣም ይጭምራል ማለት ነው። ለዚህ ነው ብዙ የተከልናቸው ችግኞች የምይፅድቁልን ከነቀጠላቸው ስለምንተክላቸው ነው።
73 ሚሊዮን ችግኝ ተተክሎ 85% ጻዲቅ በጣም ጥሩ ስኬት ነው! አቶ አቶአሽ መቼ ነው ትግሬ ችግኝ መትከል የሚጀምረው :?: :idea: :lol: :lol:




Re: የኬር ኢኮሎጂ ካልቸር! ቅሙጬ ሕዝብ፣ ቅዱስ ባህል!

Posted: 27 Jul 2022, 14:26
by Ethoash
በትግሬዎቹ ዘመን መንግስትና የእርዳታ ድርጅቶች ሕዝባችን ሆ ብሎ ነበር ተነስቶ አረንጎዴ አብዬትን የተቀላቀለው። ይህንን ቪድዬ ተመልከት በደንብ ያሳይሀል እንዴት በረሀ የነበረ መሬት ወደ ለም መሬት እንደሚመለስ። እንግዲህ ጉራጌ መጀመሪያውም ለም ትመስላለች ግን ዛፎች በሚሊዬንና በቢሊዬን መተከል ከፈለግን መሳሪያ መጠቀም አለብን ለማለት ነው ። ያንትኑ ድካም ለመደገፍ ነው ። ይሄው አንድ የአረንጎዴ አብዬት ቪድዬ ለጥፌልሀለሁ በደንብ የዛፎችን መትከል ጥቅሙን በሙሉ በደንብ የሚያሳይ ፎቶ ነው። ትንሽ የሚቀረው ነገር ቢኖር ደግሞ ሁለተኛ ዛፍ ለማገዶ እንዳይቆርጡ የባዬ ጋዝ አብዬት መጀመር አለበት ። የወልቅጤ ዩኒቨሪስቲ ሚሊዬን የረዳው ቴክኖለጂውንም ያስተዋወቀው እኮ መለስ ዩኒቨሪስቲውን ስርቶ ባጀት ስለመደበለት ነው። ይሁን ቪዲዬውን ተመልክት ፣ ትግሬዎች ደግሞ ከዚህ በበለጠ ነው የአረንጎዴውን አብዬት ተሳትፈው ትልቅ ለውጥ ያመጡት ። በአብይ ግዜ ገበሬዎን ጠመንጃ አንሳ ሆ በል ይሉታል በወርቃሞቹ ዘመን ግን መሬት ህን ለማልማት ተነስ ነበር የሚሉት ፈገግታቸው ብቻ ይበቃል።


እንዳልኩት አንድ ገበሬ ሶስት ጎደኞቹን ይዞ ሚሊዬን የምግብ ዛፎችን ለመትከል ከፈለገ ሳይደክማቸው በቀላሉ ዛፎቹን የሚተክሉበት ዜዴ ያስፈልጋል ። ይሄው ይህ ቀላል ቴክኖለጂ አለ። ማንም ሊስራው የሚችል ። እንግዲህ አንዱ ከፊት ለፊት እየሄደ ጉድጎዱን ይምሳል፣ ሌላው ደግሞ የምግብ ዛፎን ይተክላል፣ ሌላው ደግሞ ፕላሲቲኩን ቀዶ ስሮቹን በምላጩ በመስንጠቅ ከፋፍቶ ያስጋጃል። እዚህ ቪድዬ ላይ ከፕላስቲኩ ቀዶ ብቻ ነው የሚተክለው ግን ስሮቹን ለመከፋፈት ስሮቹን የያዘውን አፈር በምላጩ ጫር ጫር እያረጉ መከፋፈት ያስፈልጋል። ይሄ ስሮቹን ይጎዳል ብለው ብዙ ሰዎች ያስባሉ ግን ስሮቹ ከታስሩበት ፍታ ብለው ወደ መሬት ዘልቀው እንዲገቡ እድል ይስጣል።



ይህ ደግሞ ጎንበስ ሳትል የምትፈልገውን ችግኞችን መትከል የሚያስችልህ መሳሪያ ነው ይህም ቢሆን አንዴ የገራችን በረት ስሪዎች ካዩት አገር ውስጥ ለመስራት በጣም ቀላል የሆነ መሳሪያ ነው። ቤንዚን፣ ኤሌትሪክ አይፈልግ በጣም ፈጣን ችግኞችንን በተርታ በተመሳሳይ ርቀት እንድትተክል ጎንበስ ወይም ቁጭ ሳትል ይህንን አይነቱን ቀላላል መሳሪያዎች ስንጠቀም ብቻ ነው ለማደግ የምንችለው> carrot, Tomato, Potato, Corn, Peanuts, Chilli, Garlic , Onion planted faster and making them cheaper


Re: የኬር ኢኮሎጂ ካልቸር! ቅሙጬ ሕዝብ፣ ቅዱስ ባህል!

Posted: 27 Jul 2022, 14:50
by Horus
ኢቶአሽ

ዛፍ መትከል፣ ወርቅ ሳይሆን ዉሃ መቆፈር፣ አረንጓዴ ካልቸር ፣ ጦርነት ሳይሆን እጸዋትና እንሰሳትን በመንከባከብ ላይ ግዜና ሃብት ማባከን ነው ትግሬ መጠመድ የነበረበትና ያለብት! የኢኮሎጂ ካልቸር ከጉራጌ የልቅ የሚያስፈልገው ትግሪው ነው ። ስለዚህ ነው መቼ ነው ትግሬ ዛፍ ወደ መትከል የሚዞረው ያልኩት!

Re: የኬር ኢኮሎጂ ካልቸር! ቅሙጬ ሕዝብ፣ ቅዱስ ባህል!

Posted: 27 Jul 2022, 15:29
by Ethoash
Horus wrote:
27 Jul 2022, 14:50
ኢቶአሽ

ዛፍ መትከል፣ ወርቅ ሳይሆን ዉሃ መቆፈር፣ አረንጓዴ ካልቸር ፣ ጦርነት ሳይሆን እጸዋትና እንሰሳትን በመንከባከብ ላይ ግዜና ሃብት ማባከን ነው ትግሬ መጠመድ የነበረበትና ያለብት! የኢኮሎጂ ካልቸር ከጉራጌ የልቅ የሚያስፈልገው ትግሪው ነው ። ስለዚህ ነው መቼ ነው ትግሬ ዛፍ ወደ መትከል የሚዞረው ያልኩት!
እየነገርኩህ ትግሬዎችን አትችላቸውም ፣ አሁን ምን አመጣው ስለትግሬዎች ማንሳት ለኔ ጉራጌዎችም ያው እንደትግሬዎች የምወዳቸው ሕዝብ ናቸው ስለዚህ አሁን እኔ ስራዬ ብዬ ፖለቲካውን ትቼ ስለጉራጌ የማወራው በትግሬ ብቻ ተውስን የምትለኝ ከሆነ ደግሞ ይሄው ቪድዬውን ለጥፌልሀለሁ ። ነገር ግን መጀመሪያ የለጠፍኩት ቪድዬ በደንብ ያሳያለ አንድ ሁለት እያለ እንዴት በረሀማ መሬት እንደሚለውጥ በደንብ ያላየኸው ይመስለኛል።

i move the video to where they speak about Golden region how the transformed the land



now as the first video about the green revolution show how the river comeback ...አየህ ዛፍ እና ሳር ሲተከል የዝናብ ውሃ ወድ መሬት ስርጎ ይገባል ። መሬትን ልክ እንደ ትልቅ በርሜል ውስዳት፣ ዝናቡ ወድ መሬት ዘልቆ ከገባ ውንዝ ጋ መሄድ እያስፈልግህም ቤት ህ አጠገብ መሬቱን ብትቆፍረው ውሃ ታገኛለህ ለምን ዛፎች ውሃውን ወደ መሬት በማስረግ ያ ውሃ ቀላል ቦታ ስያገኝ አንተ የቆፈርክበት ቦታ ላይ ይመነጫል ማለት ነው። ስለዚህ ሕበረተስቡ በየቤቱ ውሃውን ስለሚያገኝ ውንዝ ሄዶ ልብሱንና ገላውን በሳሙና እየታጠበ ወንዙን መበከል አያስፈልገውም እዛው ስፈሩ ላይ ውሃ ስላለለት ማለት ነው። እንዳልኩህ ባዬ ጋዝ ቴክኖሎጂ ከገባለት ሁለተኛ ዛፎቹን አይቆርጥም ከዚያ ደግሞ የልብስ ማጠብያ ይገባለታል። ይህ ብቻ አይደለም ወንዙን በመገደብ አሳ ያረባል ኤሌትሪክም ማመንጀት ይችላል በትንሽ ትርባይን ።



look how u can dig for water using very small machine .. up to 60 m depth... the machine might cost u 3000 dollar but look how many time u can use it .. u can dig next to your house instead of going to river now tell me why should u ask me about Golden ? all i care is who ever listen to me take my advice and use it that all.

Re: የኬር ኢኮሎጂ ካልቸር! ቅሙጬ ሕዝብ፣ ቅዱስ ባህል!

Posted: 30 Jul 2022, 19:44
by Horus
የኬር ካልቸር ባህልም እምነትም ነው ፣ ኬርነት መልካምነት ማለት ነ። የዚያ ካልቸር ቁ 1 ጽንስ የኢኮሎጂ ኬርነት ነው። እሱም ማለት የአፈሩ፣ የአየሩ፣ የውሃው፣ የእንሰሳው፣ የእጸዋቱ ሁሉ ጤንነት ማለት ነው ። ሚዛናዊ የሰው ልጅ መህበረሰብ በኢኮሎጂያዊ ኬርነት ላይ ብቻ የቆመ ነው ! ኤቦ የዚህ ዊዝደም ባለቤት ለሆናችሁ ሕዝብ ሁሉ!!

ጉራጌ ክልል ነው! ኬር ለኢትዮጵያ! ሰብኛ ማለቅ ዬሁን!