Page 1 of 1

(((ሰበር ዘና))):በማይካድራ ንጹሃንን ጨፍጭፎ ሱዳን የሸሸው የኣሸባሪ-ህወሓት የሳምሪ ቡድን ሰርጎ በመግባት በመተማ ወረዳ በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት ኣደረሰ!!! WEEY GUUD !!!

Posted: 12 Jul 2022, 08:46
by tarik
Natnael Mekonnen

በአማራ ክልል በምዕራብ ጎንደር ዞን በመተማ ወረዳ ሹመት መንዶካ በሚባል ከተማ በሱዳን በመሰልጠን ላይ የሚገኘው ፅንፈኛዉ የሳምሪ ቡድን ሰርጎ በመግባት የሰው ህይወት ማጥፋቱን እንዲሁም በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን የምዕራብ ጎንደር ዞን አስታውቋል ።

ባሳለፍነው ቅዳሜ ከሌሊቱ 7 ሰዓት ገደማ ሰርጎ የገባው ፅንፈኛው የሳምሪ ቡድን ቁጥሩ በመጣራት ላይ የሚገኝ የሰው ህይወት ሲቀጥፍ በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል። በተጨማሪም የቁም እንስሳት ዘርፎ መሄዱን የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ የሆኑት አ/ቶ ቢክስ ወርቄ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።

የጉዳቱ መጠን ለማወቅ ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ እናሳውቃለን በማለት ተናግረዋል ።ይህ ሳምሪ የተባለው ፅንፈኛ ቡድን በማይካድራ ከተማ የሚኖሩ በርካታ ንፁሃንን ጨፍጭፎ ወደ ሱዳን መሸሹ የሚታወስ ነዉ ።

ዞኑ ከሱዳን የሚያዋስን በመሆኑ የክረምት ወቅቱን ተከትሎ የእርሻ ስራ እንዳይከናወን ተደጋጋሚ ትንኮሳ እንደሚደርስ እና ከሰሞኑን ትንኮሳው መጠነኛ መሻሻል አሳይቶ እንደነበር ብስራት ሬዲዮ መዘገቡ ይታወሳል ።