Page 1 of 1

አቢይና ብልጽግና ለገቡበት የክልሎች ቀውስ ያለው ብቸኛ መፍትሄ

Posted: 11 Jul 2022, 01:58
by Horus
አንድ፣
የደቡብ 54 ጎሳዎች ፍላጎትና ወሳኔ ታሳቢ ያላደረገው የሲዳማ ቶሎ ቶሎ ሩጫ የኦሮሞ ፖለቲከኞችን ቅርቃር ውስጥ ቀርቅሯል ። ለምሳሌ ሲዳማ ክልል ነኝ ይላል እንጂ የደቡብ ዋና ከተማ አሁንም አዋሳ ነው።

ሁለት
አንድ ባንድ እየቆረሱ ይህን ክልል ያን ክልል የሚለው ቅጥ አልባ ጨረባ ፖለቲካ ውጤቱ ችግር መፍታት ሳይሆን መላ ደቡብ ካቢይ መንግስት ጋራ እያጋጨው ነው ።

ሶስት፣
አቢይና አባዱላ መሬት ላይ የሌለ የፖለቲካ ምናብ ትተው ክልልነት ለጠየቁት ወደ 10 ለሚጠጉት ብሄሮች መብታቸውን ማክበር ። በልዩ ዞንነት ራስ ገዝ ሆነው ከሌላ ክልል ጋር አብሮ መኖር የመረጡትን ምርጫውን አክብሮ በአንድ አገር አቀፍ ምርጫ የሁሉንም ክልሎች ጉዳይ መፍታትና ደቡብን ማፍረስ ነው ።

አራት፣
ይህም ቢያንስ 20 ክልሎች ይኖራሉ ማለት ነው ።

አምስት፣
ከዚያም በኢትዮጵያ የዘር ፖለቲካ ለማጥፋት እና ዘመናዊ ፖለቲካ ለመፍጠር አገር አቀፍ ለውጥና ሪፎርም ላይ መላ ኢትዮጵያዊን ሲስማሙ እነዚህ 20 የክልል ድምበሮች በመሻር አዲስ ክለስተር በመቅረጽ በጂኦግራፊና ኢኮኖሚ እና ታሪክዊ ት ስ ስር ላይ የተመሰረተ ጠ/ግዛት ወይም ክፍለ ሃገር ወይም ክልል እስትራክቸር መፍጠር ነው። ቁም ነገሩ ስሙ አይደለል፣ ይዘቱ ነው ።

ስድስት፣
ይህ ሳሆን ቀርቶ አቢይና አባዱላ የነሱን ግላዊ ፍላጎት መጫን ከሞከሩ መጀመሪያ ከህዝብ የሚባረሩት የየክልሉ ካድሬዎች ናቸው ። ለምሳሌ የጉራጌ ብልጽኛዎች በግልጽ ይህን ያውቃሉ ። አለያም አቢይ 54 ብሄሮችን በሚሊታሪ ገነንነት በሃይል ለመግዛት መዘጋጀት ይኖርበታል ። ለምሳሌ ጉራጌን በመሳሪያ አስገድዶ ሆሳዕና እንዲገበይ ማድረግ! ቀልዴን አይደለም!

ማለትም አዲስ የታሰቡት ከልስተሮችም ስራ ላይ አይውሉም ። አሁን ያለውም ደቡብ አይፈርስም ። የደቡብ ዋና ከተማም ከአዋሳ አይነአም ። ማለትም የሲዳማ ክልልነት እራሱ ፌክ ሆኖ ይቀራል ።

አሁን ይህን በምንልበት ሰዓት ከመንግስት ፕሮጀክቶች በስተቀር አንድም ባለ ሃብት ከራሱ ክልል ውጭ ኢንቬስትመንት የሚያደርግ የለም ።

ስለዚህ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ኢኮኖሚና የብሂራዊ ከበርቴ እንቅስቃሴ የሚባል ነገር ቆሞዋል! ይህ ይቀጥላል!

Re: አቢይና ብልጽግና ለገቡበት የክልሎች ቀውስ ያለው ብቸኛ መፍትሄ

Posted: 11 Jul 2022, 02:34
by Horus
ጉራጌ ሆሳዕና አይሄም ! ጉራጌ ቡታጀራ ይሄዳል! ወልቂጤ ይሄዳል! እምድብር ይሄዳል ! ቡዬ (ቡኢ) ይሄዳል! ጉራጌ 12 የሚልያለማቸው ከተሞች አሉት !!!

Re: አቢይና ብልጽግና ለገቡበት የክልሎች ቀውስ ያለው ብቸኛ መፍትሄ

Posted: 11 Jul 2022, 11:42
by ethiopianunity
የደቡብ ክልልን ማፈራረስ ባሁኑ ሰኣት ኣሁንም የሚጠቅመ ግዙፍ ለሆኑ ክልሎች እንደነ ኦሮሚያ የሚጠቅምና የተፈረካከሱ ክፍለ ሃገሮች ላይ ኦሮሚያ ክልል በቀላሉ ተጽእኖ እንዲደረግባቸው መጋበዝ ነው።

ጤናማ በኦነ ሁኔታ ክፍለ ሃገር ለመፍጠር በድንቁርና በዘር የማዳላት ሳይሆን ረጋ ባለ መንፈስ ህዝብ ቁጭ ብሎ እንዲወያይበት ማድረግ ነው። ይህ ውጤታማ የሚሆነው ህዝብ በጎ መንፈስ፣ ሰላም ሁኔታ ላይ ሲሆን የ ከፍለ ሃገር መስረትም ፕሮጀክቶች ትክክል ይሆናል። ህገመንግስቱን እውቀት ባላቸው ኮሚቴዎች ከህዝብ ጋር ሆኖ ሁሉም በተሳተፈበት ክፍለ ሃገርን በሚመለክት ህግ ማውጣት ነው። ነጻውጪዎች በሚስጥር ያያደረጉት ክልል፣ ለነሱ የከፋፍለህ ግዝ ቅኝገዢነት ዘዴ ስለሆነና ህዝብን ስለሚጎዳ ነው።

ዓለበለዝያ ይህ የደቡብ መፈራረስ፣ ህዝቦቹን የማዳከም ዘዴ ነው ኦሮሞም፣ ኣማራም ክልሎች ካልፈራረሱ። በዛሬው ሁኔታ ኣገር ኣሁንም ኣንድ ካልሆነ የክልሎችም መፍረስም ሊጎዳ ይችላል። ለህዋሃትም በጣም ጠቃሚ ይሆናል ኣሁን ግዙፍ ኣማራ ክልል ኣጠገቡ ስለሌለ። ለዚህም ነው በርግጠኝንት ትግራየም ተከፋፍላ ትንሽ መሆን ኣለባት።ሕውህዋሃትና ሻብያ እንዳይጠገን ኣድርገው ነው ክልሉን የተከሉት ግን በበጎና እውቀት ካለው መንግስትና ሕዝብ ሊጠገን ይይችላል።

Re: አቢይና ብልጽግና ለገቡበት የክልሎች ቀውስ ያለው ብቸኛ መፍትሄ

Posted: 11 Jul 2022, 12:49
by ZEMEN
Horus wrote:
11 Jul 2022, 01:58
አንድ፣
የደቡብ 54 ጎሳዎች ፍላጎትና ወሳኔ ታሳቢ ያላደረገው የሲዳማ ቶሎ ቶሎ ሩጫ የኦሮሞ ፖለቲከኞችን ቅርቃር ውስጥ ቀርቅሯል ። ለምሳሌ ሲዳማ ክልል ነኝ ይላል እንጂ የደቡብ ዋና ከተማ አሁንም አዋሳ ነው።

ሁለት
አንድ ባንድ እየቆረሱ ይህን ክልል ያን ክልል የሚለው ቅጥ አልባ ጨረባ ፖለቲካ ውጤቱ ችግር መፍታት ሳይሆን መላ ደቡብ ካቢይ መንግስት ጋራ እያጋጨው ነው ።

ሶስት፣
አቢይና አባዱላ መሬት ላይ የሌለ የፖለቲካ ምናብ ትተው ክልልነት ለጠየቁት ወደ 10 ለሚጠጉት ብሄሮች መብታቸውን ማክበር ። በልዩ ዞንነት ራስ ገዝ ሆነው ከሌላ ክልል ጋር አብሮ መኖር የመረጡትን ምርጫውን አክብሮ በአንድ አገር አቀፍ ምርጫ የሁሉንም ክልሎች ጉዳይ መፍታትና ደቡብን ማፍረስ ነው ።

አራት፣
ይህም ቢያንስ 20 ክልሎች ይኖራሉ ማለት ነው ።

አምስት፣
ከዚያም በኢትዮጵያ የዘር ፖለቲካ ለማጥፋት እና ዘመናዊ ፖለቲካ ለመፍጠር አገር አቀፍ ለውጥና ሪፎርም ላይ መላ ኢትዮጵያዊን ሲስማሙ እነዚህ 20 የክልል ድምበሮች በመሻር አዲስ ክለስተር በመቅረጽ በጂኦግራፊና ኢኮኖሚ እና ታሪክዊ ት ስ ስር ላይ የተመሰረተ ጠ/ግዛት ወይም ክፍለ ሃገር ወይም ክልል እስትራክቸር መፍጠር ነው። ቁም ነገሩ ስሙ አይደለል፣ ይዘቱ ነው ።

ስድስት፣
ይህ ሳሆን ቀርቶ አቢይና አባዱላ የነሱን ግላዊ ፍላጎት መጫን ከሞከሩ መጀመሪያ ከህዝብ የሚባረሩት የየክልሉ ካድሬዎች ናቸው ። ለምሳሌ የጉራጌ ብልጽኛዎች በግልጽ ይህን ያውቃሉ ። አለያም አቢይ 54 ብሄሮችን በሚሊታሪ ገነንነት በሃይል ለመግዛት መዘጋጀት ይኖርበታል ። ለምሳሌ ጉራጌን በመሳሪያ አስገድዶ ሆሳዕና እንዲገበይ ማድረግ! ቀልዴን አይደለም!

ማለትም አዲስ የታሰቡት ከልስተሮችም ስራ ላይ አይውሉም ። አሁን ያለውም ደቡብ አይፈርስም ። የደቡብ ዋና ከተማም ከአዋሳ አይነአም ። ማለትም የሲዳማ ክልልነት እራሱ ፌክ ሆኖ ይቀራል ።

አሁን ይህን በምንልበት ሰዓት ከመንግስት ፕሮጀክቶች በስተቀር አንድም ባለ ሃብት ከራሱ ክልል ውጭ ኢንቬስትመንት የሚያደርግ የለም ።

ስለዚህ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ኢኮኖሚና የብሂራዊ ከበርቴ እንቅስቃሴ የሚባል ነገር ቆሞዋል! ይህ ይቀጥላል!

horus let me ask you two questions i couldn't find an answer. One, why not kill the poisonous and the source of all problem the constitution and the second one is , why go back to kiflehager system as it was in Mengistu Hailmriam time? please help.

Re: አቢይና ብልጽግና ለገቡበት የክልሎች ቀውስ ያለው ብቸኛ መፍትሄ

Posted: 11 Jul 2022, 13:28
by Horus
ZEMEN

ከሁለተኛው ጥያቄ ልጀምር ። እኔ ወይም ማንም የጎሳ ክልል ተቃዋሚ ያለን ጠብ ከስሙ አይደለም ። ከላይ ብያለሁ፤ ያገሪቱ ፌዴራል እስቴቶች ከጎሳ ክልልነት ወጥተው በሌላ ማንኛውም ሳይንሳዊ መስፈር፣ ለምሳሌ ጂኦግራፊ፣ ያየር ጠባይ፣ ኢኮኖሚ፣ ታሪክ፣ ገበያ ውዘተ መሰረት ተከልለው የአድሚኒስትሬሽን ቅልጥፍና እስካመጡ ድረስ ማንም ሰው በስም ላይ ጠብ የለውም። ክፍለ ሃገር የአገር አከፋፈል ማለትም እስቴት ማለት ነው ። ጠ/ግዛት ማለት ያው ነው ። ግዛት ማለት አስተዳደር ማለት ነው። ከተፈለገ ክልል፣ ሪጅን ወይም ቃል ተፈልጎ ሊሰየም ይችላል ። ግ ን አንድን አገር በዘር መሰረት መከፋፈል ውጤቱን ለ30 አመት አይተሃል ። አይሰራል አደገኛ ነው ። እንዲያውም ካሁን የባሰ ጂኖሳይድ ያስከትላል ።

አንደኛ ጥያቄ ላስከተል።
የእኔን አቋም ማወቅ ከፈለክ ላለፈው 30 አመት የጻፍኩትን አንብብ። የዘር ክልል በመቃውም የህዝቤን ባህልና ቋንቋ እስኪጠፋ የታገልኩ ሰው ነኝ ። ስለዚህ ነገ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተስማምቶ ከዛሬ ጀምሮ የጎሳ ክልሎች ይፍረሱ ካለ መጀምሪያ የድጋፍ ሰልፍ የሚወጣው ጉራጌ ነው ። ነገር ግን እየሆነ ያለው ይህ አይደለም ። በጎሳ የተደራጁ የማዕከላዊ መንግስት ስልጣን ይዘው (state capture) ይባላል በሌሎች ታክስና በትናንሽ ብሄሮች እውቀትና ጉልበት እርሳቸውን እያለሙ ትናንሾቹ ቋንቋቸው እንዲሞት፣ ባህላቸው እንዲጠፋ፣ አለንጹ ውሃ እንዲበታተኑ፣ ማርጂናላይዘድ እንዲሆኑ እየተደረገ ነው ።

ይህ መቆም አለበት ። ከላይ እንዳልኩት እጅግ ቀላል በሆነ የአንድ ቀን ብሄራዊ ምርጫ ሁሉም ብሄረሰብ የጠየቀውን ህጋዊ መብቱ (አሁን ባለ ህገ መንግስት ባለው መብቱ) ተከብሮለት ከዚያ በኋላ መላ ኢትዮጵያ ስትለወጥ ሁላችንም አብረን እነለወጥ ። ይህ ብቻ ነው ፍትህ ማለት! ይህ ብቻ ነው መፍትሄ ማለት! ከዚያ ውጭ ያለ ዘረኘነት፣ የበላይነት፣ ንቀት፣ አምባገነነት፣ ብልጠት ነው ። አይሆንም! አይሰራም!

Re: አቢይና ብልጽግና ለገቡበት የክልሎች ቀውስ ያለው ብቸኛ መፍትሄ

Posted: 11 Jul 2022, 14:31
by ZEMEN
Horus wrote:
11 Jul 2022, 13:28

Thanks for your time. So, i don't get it, do you support the constitution. I do believe the sources of the problem in Ethiopia is the constitution. However; Abiy will take Ethiopia to her deepest never before. The man is self centered, narcissist and the only thing he cares is about his power.

Re: አቢይና ብልጽግና ለገቡበት የክልሎች ቀውስ ያለው ብቸኛ መፍትሄ

Posted: 11 Jul 2022, 14:56
by Horus
ZEMEN
የእኔን ሃሳብ ጽሁፌ ውስጥ ታገኘዋለህ ። ያንተን ሃሳብ አንጎልህ ውስጥ ታገኘዋለህ ። ይብቃን ሰላም ።

Re: አቢይና ብልጽግና ለገቡበት የክልሎች ቀውስ ያለው ብቸኛ መፍትሄ

Posted: 14 Jul 2022, 19:28
by Horus
የዛሬ 3 ቀን ይህን ሃሳብ አቅርቤ ነበር ። ዛሬ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሙሉ ሪፖርት አውጇል ።

30 የክክል፣ አስተዳደር እና ማንነት ጥያቄዎች ለውሳኔ ቀርበዋል ብለዋል። ከነዚህ 30 ህገ መንግሳትዊ ጥያቄዎች 6 የማንነት ጉዳይ ናቸው ። ለምሳሌ እንደ ወልቃይት አንድ ሕዝብ አማራ ነው? አፋር ነው? ኦሮሞ ነው? ወዘተ ብሎ መወስ ማለት ነው ።

24ቱ ክልልና አስተዳደር ናቸው ። ልዩ ዞን ወይም ወረዳ፣ አውራጃ የሚባሉት ብዙ ይመስሉኛል ።

ክልል ለመሆን በዞናቸው ምክር ቤትና በህዝባቸው ግፊት የቀረቡ (1) ጉራጌ፣ (2) ስልጤ፣ (3) ሃዲያ፣ (4) ወላይታ፣ (5) ጋሞ እያለ እስከ 11 የሚደርሱ መሰልኝ።

ይህ ምክር ቤት የህዝባችንን ፈቃድና ጥያቄ በመጣስ ብክለስተር ተጨፍለቁ ምናምን የሚለው ደባ አምጥቷል ! ይህ ፈጽሞ ፈጽሞ የማይሆ ነገር ነው።

ከላይ እንዳልኩት ክልል ለጠየቁ መብታቸውን ማክበር ፣ ዞን መሆን ለጠየቁ መብታቸውን ማክበር፣ ልዩ ዞነ መሆን ለጠየቁ መብታቸውን ማክበር ነው።

ከዚያ ባለፈ አንድ ሆነው ክለስተር መሆን ለጠየቁ በህዝብ ድምጽ መብታቸው ማክበር ነው።

በመጨረሻም ክልሎች ሁሉ ይፍረሱ ከተባለ ሕዝቡ በድምጹ እንዲወስን ማድረግ ነው ።

ለምሳሌ ጉራጌ በፍጹም በፍጹም ክለሰተር ውስጥ መጨፍለቅ አይፈልግም፣ በጉልበት ቢጫንበት እንኳ አይቀበልም ።

ጉራጌ የራሱ ከተማ (ከተሞች) ያለት ክልል ነው!

ጉራጌ ሁሉንም የሌላ ጎሳ ዞኖችች፣ ክልሎች፣ ወዘተ ያከብራል፣ ከማንኛውም ክልልና ዞን ጋር በፍቅርና ሰላም ይሰራል ። ነገር ግን ከማንም ሌላ ዞን ጋር መጨፍለቅ አይፈልግም። የማይታሰብ ነው ።

የጉራጌ መሪዎች ይህን የህዝባችን ፍላጎትና መብት እንዲያስከብሩ መገን በጉራጌ ሴራ ብለናል ። የፌዴሬሽን ምክር ቤት ይህን የህዝባችን ፍላጎትና መብት እንዲያክበር እንጠይቃለን !

የሰላም መንገድና መፍትሄ ይህ ብቻ ነው!

Re: አቢይና ብልጽግና ለገቡበት የክልሎች ቀውስ ያለው ብቸኛ መፍትሄ

Posted: 14 Jul 2022, 20:07
by Horus