Page 1 of 1

HOROR is for real?

Posted: 09 Jul 2022, 12:13
by Ethoash
Everyone in here u know Horor day and day out telling ክልል መፈረስ አለበት፣ የወያኔ ሕገመንግስት መቀዳደድ አለበት ፣ አብይ ኢትዬዽያን መምራት ከፈለገ የዘር ፈደራሊዝም ማፍረስ አለበት፣ እሱን ካላፈረስ ስላም እናገኝም ብሎ ከተራራ ላይ ቆሞ ጡሩምባ ሲነፋ እድር ሲጠራ ከርሞ ዛሬ ጉራጌዎች ክልል ማሆን አለባቸው ይለናል። በምን ሕገመንግስት ሕግ መንግስቱ ይቀደድ ብለህ ተቀዶዋል። ክልል ፈርሶዋል፣ የዘር ፈድራሊዝም አክትሞዋል ታድያ እንዴት ተደርጎ ነው ጉራጌ ክልል እንዴት ሆኖ ነው የሚሆነው በምን ሕግ መንግስት ወይ መጀመሪያ መለስ የሕግመንግስቱ አባት እግር ስር ወድቀህ ይቅርታ ጠይቀህ ከዚያ በኋላ ምናልባት እንስማህ ይሆናል ። ከአዱ ዛፍ ወድ ሌላው ዛፍ እንጣጥ እንጣጥ ማለት የለም። በሁለት ቢላዋም መብላት ማቆም አለብህ ምን አይነት አይነደረቅነት ነው አይንህን በጨው ታጥበህ ክልል እንሆን ትንሽ አስቀጥጥህም ወይ።

እንዲህ አይነቱ አክሮፓስቲክ የምትችል አልመስለኝም ። ይህንን ጥይቄ ካልመለስክ መልሱ ገባኝ ሁለተኛ የዘር ፈደራልዚም ብለህ ብት ዘፍን ማንም አይስማህም ። ይቅርታ ትንሽ ብሽቅ ስላረግኸኝ ነው ። እንጂ እኔ ላንተ ያለኝ ክብር ታላቅ ነው ። ግን ያለፍሬቻ ግራ የምትጠመዘዝ መስለህ ወድ ቀኝ ስትታጠፍ ነው ያናደድከኝ አሁንም መጥተህ ይቅርታ በል ።

Re: HOROR is for real?

Posted: 09 Jul 2022, 12:24
by Horus
ኢቶአሽ የምትባል፣ ኤዱካተር ሂድና ለ30 አመት የጻፍኩትን አንብብ። ካሻህ ደሞ ማንኛውንም ጉራጌ መንገድ አስኩመህ ጠይቅ! አቋማችን አንድ ነው ። ኢትዮጵያ በፍጹም በዘር፣ በጎሳ ፌዴሬሽን ሆነ ሌላ ትራይባል ሲስተም አትመራ የሚለው የእያንዳንዱ ጉራጌ አቋም ነው ። ያ ሳይሆን ቀርቶ ኢትዮጵያ በዘር፣ በጎሳ፣ በብሄር ክልል እስከ ተደራጀች ድረስ ጉራጌ ልክ እንደ ትግሬ። ልክ እንደ አማራ። ልክ እነ አፋር፣ ልክ እንደ ኦሮሞ። ልክ እንደ ሱማሌ፤ ልከ እንደ ሲዳማ የራሱ የጉራጌ ብሄር ክልል መፈለግ ሳሆን አሁን ባለው ህገ መንግስት መብቱ ነው ።

እርግጥ የነዚህ ሁለት ሃሳቦች ልዩነት የማይገባቸው ብዙ የወያኔ መሃይሞች እዚህ ፎረም ላይ አሉ! ግና የነሱ ባዶ የምቀኛ ጫጫታ ፋይዳ የለውም!

አመድ በዱቄት ይስቃል አሉ! ወያኔ ስለሚበላው ስንዴ ቢጨነቅ ያምርበታል! የጉራጌውን ለጉራጌ ትቶ!

Re: HOROR is for real?

Posted: 09 Jul 2022, 13:31
by Ethoash
Horus wrote:
09 Jul 2022, 12:24
ኢቶአሽ የምትባል፣ ኤዱካተር ሂድና ለ30 አመት የጻፍኩትን አንብብ። ካሻህ ደሞ ማንኛውንም ጉራጌ መንገድ አስኩመህ ጠይቅ! አቋማችን አንድ ነው ። ኢትዮጵያ በፍጹም በዘር፣ በጎሳ ፌዴሬሽን ሆነ ሌላ ትራይባል ሲስተም አትመራ የሚለው የእያንዳንዱ ጉራጌ አቋም ነው ።
ሁሉም ስለሚስርቅ እኔም መስረቅ አለብኝ ብሎ ሎጂክ በወንድማችን ሆረር ሲቃኝ ፣


Re: HOROR is for real?

Posted: 09 Jul 2022, 14:56
by eden
Horus

Since you claim multinational federation is bad, don’t you think keeping the numbers of the regions less is better? How is multiplying a bad thing good?

Re: HOROR is for real?

Posted: 09 Jul 2022, 15:16
by Horus
eden wrote:
09 Jul 2022, 14:56
Horus

Since you claim multinational federation is bad, don’t you think keeping the numbers of the regions less is better? How does multiplying a bad thing good?
eden,
Bad for whom? good for whom? Buddy, every person, every group, every ethnic has its own existential, cultural, developmental and political needs. As I said else where, until all Ethiopian ethnics choose and decide to eradicate ethnocracy, those without killil must not be subjected to extinction and cultural death. It is immoral and an historical injustice. On what just ground do you permit the flourishing of all these kilils and deny the same to Gurage and others who demand it. Gurage is demanding its rights under the existing law (however defective) to be respected . That is all. The PP or Abiy's gov. or any other person has no just and moral ground to deny the Gurage nationality its right to its own region call it killil or province. And, if and when Ethiopians decide to eradicate killilism, Gurage will the 1st to dissolve its killil. Too many or few kills is not the argument. 5 kills are not more just than 7 killils, and so no. If people think killils are bad things, then let us get rid of them all together. Justice, Justice, Fairness, Fairness !!!!

Re: HOROR is for real?

Posted: 09 Jul 2022, 16:42
by Horus
eden,
ለጥፈህ መልሰህ የዘረዝከው የተሳሳተ ሃሳብና ኢንፎርሜሽን ጥሩ አደረክ! ለዚያ የጻፍኩት መልስ እነሆ! ለሌሎች ትምህርት እንዲሆን ....

"የኔ ወንድም የሌለ ክርክር አትፍጠር! መስቃን አይደለም ጉራጌ ቡታጀራ የጉራጌ ዋና ከተማ ነው ። ጉራጌ የሚለው ቃል ሲነሳ መስቆ፣ ክስቶ፣ ሰባትቤት ካላለ ቃሉ ራሱ ትርጉም የለውም። ማረቆና መስቃን ስላላቸው የድንበር ቀበሊዎች ጉዳይ እራሱ የመስቃና ማረቆ ሽማግሎች ከወያኔ ውጭ የፈቱት ጉዳይ ነው ከታች የምለጥፈውን ቪዲዮ ተመልከት! እኔ እናቴ ግማሽ ወለኔ ናት ። እኔ ቤት መስቃን ጉራጌ፣ ክስታኔ ጉራጌ፣ ሰባት ቤት ጉራጌ አክሊል ጉርጌ፣ ጉመር ጉራጌ፣ ስልጤ ጉራጌ እየትባለ የጎጃም አማራ፣ የወሎ አማራ፣ የጎደር አማራ እንደ ሚባለው ሳድግ የማውቀው ። ዛሬ ወለኔ አይ እኔ የራሴን ክልል ነው ምፈልገው ካለ መብቱ ነው ። የጉራጌ ክልልነት መብት በቀቤና ወይም በሌላ ጎሳ ፍላጎት አይወሰንም ። ልብ በል ኦነግ አዲሳባ እስከ ገባ ድረስ ዛሬ ጂዳ ኦሮሞ ነን ያሉት የግርማ ብሩ ዘሮች ጉራጌዎች ነበሩ ። ዛሬም ሙሉ ህይወታቸው እንደ ጉራጌ እየኖሩ ኦሮሞ ነን ብለዋል! ግ ን አንድ ነገር ልንገርህ ከዚህ በኋላ የጉራጌን ማንነት ማጥፋት አይቻልም!

ለምሳሌነት ጉራጌም እንጠቀም ለሚሉ መልሱ አው እንዲያውም ጉራጌን የራሱ ክልል ይሰጠውና እንዴት ከሌሎች በሻለ መልክና ፍትነት እንዲያድግ ይታይ ነው የሚባለው እንጂ ኦሮሞን ወይም ትግሬን ኢትዮጵያዊነት ለማስተማር የጉራጌን ዘር እናጥፋና እንዴት ኢትዮጵያዊ ዘር እንደ ሚሆን የጊኒ ፒግ የሙከራ እንሰሳ እናድረገው የማለትን ያህል ነው። ያ ደሞ አይታሰብም!

በአዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች ብቻ ከ2 እስከ 3 ሚሊዮን ጉራጌ አለ! ጉራጌ ክልል ነው! ሰብኛ ማለቅ ዬሁን!

የመስቃና ማረቆ እርቅ
https://www.youtube.com/watch?v=nG3F7kwrlKE

Re: HOROR is for real?

Posted: 09 Jul 2022, 16:57
by Abere
አደሬ (ሀራሪ) እንደት ክልል እንደ ሆነ ታውቃላችሁ?
አደሬ ክልል የሆነችው በአንድት የአደሬ ቆንጆ ምክንያት ነው። የወያኔ ወታደር(ጦር) መሪ ሀረር በደረሰ ጊዜ አንድ ብልጥ አደሬ ለወያኔው መቀበያ ትሆን ዘንድ ቆንጆ አደሬ ተፈልጋ እንድታስተናግደው ተደረገ። ከዚያ በኋላ የአደሬ ጉዳይ የግል ጉዳይ ተደርጎ በወያኔዎች ተወሰደ እና ክልል ሆነ አረፈች።ተጽእኖ ፈጣሪ ወያኔ ስለነበር። ይህ እውነት ነው - የዋዛ የቀልድ አይደለም። ትክክለኛ መረጃ ነው። አደሬ በሴት የተገኘ ክልል ነው። ክልል እርባና አለው ካላችሁ። እኔ ግን ጉራጌ ለምን ክልል ሳይሆን ቀረ? ደግሞ የሚገርመው በአፍላ የወያኔ የክልል ድልድል ጊዜ ድ/ር ፈቃዱ ገዳሙ (ጉራጌ ናቸው) ምክትል ፕሬዚዳንት ነበሩ ለምን እንዳልጠየቁ ለእኔ እራሱ እንቆቅልሽ። ምክንያቱም ጉራጌ ከትግራይ ህዝብ ይበልጣል በቁጥር የሚል ግምት አለኝ።