ይህ እጅግ አስደናቂ ፕሮግራም ነው! የጉራጌኛ ቋንቋ ዲያሌክቶች ሁሉ አንድ እየሆኑ ነው!
Posted: 27 Jun 2022, 00:16
አምደ ገብራኤል በሰባት ቤት ሲናገር ክስታኔው ያሬድ ስለሚገባው መልሱን በስታኔኛ ይመልሳል! ያ ደሞ ክስታኔኛው ስለሚገባው መልሱን በሰባት ቤት ይመልሳል! እጹብ ድንቅ ! ግን ክስታኔኛ ተናጋሪው የከተማ ሰው ስለሆነ በጣም ተራ የሆኑ የክስታኔኛ ስህተቶችን ይሰራል ። ለምሳሌ 'አንደኛ' ይላል 'ቃሉ ግን 'አትለኛ' ነው ። 'ተነጋግረን' ያላል ቃሉ ግን አንዱ 'አወረርነም ' ወይም ተመካክረን ለማለት 'ተቱጋገትነም ' ነው። ጥሩ ሙከራ ነው ። ቀስ በቀስ ይጠራል !!
ለምሳሌ እኔ አፈ የፈታሁት በክስታኔኛ ነው ። ነገር ግን ሙሉ በሙል በሚባል ድረጃ መስቃንኛ እሰማለሁ፣ ይገባኛል ። ቢያንስ 6 ወር እንኳ ቡታጀራ ብኖር በመስቃንኛ መመለስ እችላለሁ ማለት ነው ። ማለትም በአጭር ግዜ ውስጥ አንድ ግዙፍ ጉራጌኛ ቋንቋ ማደጉ አያጠራጥም ።
ለምሳሌ እኔ አፈ የፈታሁት በክስታኔኛ ነው ። ነገር ግን ሙሉ በሙል በሚባል ድረጃ መስቃንኛ እሰማለሁ፣ ይገባኛል ። ቢያንስ 6 ወር እንኳ ቡታጀራ ብኖር በመስቃንኛ መመለስ እችላለሁ ማለት ነው ። ማለትም በአጭር ግዜ ውስጥ አንድ ግዙፍ ጉራጌኛ ቋንቋ ማደጉ አያጠራጥም ።