የአብይ ዉሀ አምጡ ቆሻሻ ይጣላል ፖለቲካ _ የአዲስ አበባ ተወካይ የከርስና የፈርስ ንግግር ፟...። ሊሴ ገብረማሪያም ፈረንሳይኛ ይዘመራል / ጀርመን ትምህርት ቤት ጀርመንኛ ይዘመራል ፤ ባለፈው ደግሞ የኢትዮጵያ ፖለቲካ የኔ የኔ ነው ያንተ የኛ ፖለቲካ ነው ፤ ይህንን ንግግር ከጀዋር ፤ ከአራርሳ፤ ደጋግመን ስንሰማው ነበረ አሁን መጨረሻ ላይ አብይ በማያስፈራ ቁጣው ፓላማ ላይ የተናገረው "ኦሮሞ ጠል አዲስ አበባ ፖለቲካ " የዚሁ ፖለቲካ ቅጣይ ነው ፡ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ _ የሀገሪቱን 61% የሆነውን ኢኮኖሚ የኦሮሞ ነው ብለን ልንውጥ ስንሞክር አትንፈራገጡ ኢትዮጵያን አይናችሁ እያየ ኦሮምያ እናደርጋት አይን ያወጣ የጅብ ቀንድ ነካሽ ፖለቲካ ነው፡፡ አብይ ያልተረዳው ነገር ቢኖር በሌላው ላይ የተረተው " በሬ ሆይ ሳሩን አይተህ ገደሉን ሳታይ ተረት " በሬው እርሱ የሚያስበው ሳይሆን እራሱ እንደሚሆን አጢኖ ቢያስበው መልካም ነው ፤ አታልዋለሁ ብሎ ከሚያስበው ህብረተሰብ የበለጠ አታልለታለሁ ብሎ የሚያስበውን ህዝብ ነው የሚግዳው ልክ ወያኔ የትግሬ ህዝብን አጭበርብሬ እጠቅማለሁ ብሉ ከሚወድው ከሚወዱት ወንድምና እህት ህዝቦች አቃርኖ ቁርሾ አሳድሮ ፤ ጠላቶቹን አብዝቶ እንደተውው ሁሉ ፤ የአብይ የምትወዱትን እየነገርኳችሁ ገድል እከታችኋለሁ ፖለቲካ መድረሻው የሚሆነው ወያኔዎች ሰፈር ነው፡ ሁሉንም ነገር በንጹህ መንፈስ ፤ በወንድማማችነት ፤ በፊትህ ፤ እግዚያብሄርን በመፍራት ሰላምና ብልጽግናን ማምጣት ሲቻል ፤ በተንኮል ቁማር ህዝብን ወደ ደም ማፋሰስ ፤ ጥላቻ መውሰድ በተለይንም ደግሞ ከህዝብ ጀርባ በመዶለት የሚሰሩ ዶለታዎች ፤ ሁሉንም አይጠቅምም፡
እንደሚባለውም "እብደት ማለት ተመሳሳይ ነገርን ደጋግሞ በመስራት የተለይ ውጤት መጠበቅ ነው" ከወያኔ በተማሩት የወያኔን እብደት ፤ ትእቢት ፤ ብልጠት ተመሳሳይ የጎሳ አሻጥር ሰርተው የተለየ ውጤት መጠበቅ የጎሰኞች እብደት ነው፡