Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

ሀጫሉ ሁንዴሳ የሙዚቃ አዋርድ ሰኔ 22 ይካሄዳል

Post by sarcasm » 15 Jun 2022, 08:12

ሀጫሉ ሁንዴሳ የተሰኜ አዋርድ ሊካሄድ ነው።

በሀገራተችን በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅ የነበረውና በሞት የተለዬን በድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ስም የተቋቋመው ሀጫሉ ፋውንዴሽን ሰኔ 22/2014 ዓ/ም አዋርድ ሊያካሂድለት ነው።

በእዚህ የመጀመሪያው የሀጫሉ አዋርድ መወዳደር የሚችሉት አፋን ኦሮምኛ ዘፋኞች ብቻ ሲሆኑ በሚቀጥለው የሀጫሉ አዋርድ ደግሞ አፍሪካዊን ድምጻዊያኖችን ለማካተት ታቅዷል ብላለች ባለቤቱ ፋንቱ ደምሰው።

አሸናፊዎች የሚለዩት 70% በዳኞች እና 30% በSMS አጭር ቁጥር እንደሆነ ተገልጧል።

የሀጫሉ ሁንዴሳ የምርጫን ሂደት መከታተል የምትፈልጉ በራሱ ስም በተከፈተው ፌስቡክ ፔጅና ዌብሳይት መከታተልና መጠቆም ትችላላችሁ ተብሏል።

Via ዋልተንጉስ ዘሸገር